Vertaling van de betekenissen Edele Qur'an - De Amhaarse vertaling - Afrika Academie

Pagina nummer:close

external-link copy
137 : 26

إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا خُلُقُ ٱلۡأَوَّلِينَ

137. «(ያለንበትን አንለቅም)። ይህ የፊተኞቹ ሰዎች መንገድ እንጂ ሌላ አይደለም። info
التفاسير:

external-link copy
138 : 26

وَمَا نَحۡنُ بِمُعَذَّبِينَ

138. «እኛም የምንቀጣ አይደለንም።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
139 : 26

فَكَذَّبُوهُ فَأَهۡلَكۡنَٰهُمۡۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ

139. አስተባበሉትም፤ አጠፋናቸዉም፤ በዚህም ውስጥ እርግጠኛ ግሣጼም አለበት:: አብዛኞቻቸዉም ምዕምናን አልነበሩም:: info
التفاسير:

external-link copy
140 : 26

وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ

140. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊውና አዛኙ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
141 : 26

كَذَّبَتۡ ثَمُودُ ٱلۡمُرۡسَلِينَ

141. የሰሙድ ህዝቦች መልዕክተኞችን አስተባበሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
142 : 26

إِذۡ قَالَ لَهُمۡ أَخُوهُمۡ صَٰلِحٌ أَلَا تَتَّقُونَ

142. ወንድማቸው ሷሊህ ለእነርሱ ባላቸው ጊዜ: «አትጠነቀቁምን? info
التفاسير:

external-link copy
143 : 26

إِنِّي لَكُمۡ رَسُولٌ أَمِينٞ

143. «እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ። info
التفاسير:

external-link copy
144 : 26

فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ

144. «አላህን ፍሩ ታዘዙኝም። info
التفاسير:

external-link copy
145 : 26

وَمَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ أَجۡرٍۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

145. «በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልለምናችሁም:: ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ ብቻ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም። info
التفاسير:

external-link copy
146 : 26

أَتُتۡرَكُونَ فِي مَا هَٰهُنَآ ءَامِنِينَ

146. «በዚያ እዚህ ባለው ጸጋ ውስጥ የረካችሁ ሆናችሁ ትቀራላችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
147 : 26

فِي جَنَّٰتٖ وَعُيُونٖ

147. «በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ info
التفاسير:

external-link copy
148 : 26

وَزُرُوعٖ وَنَخۡلٖ طَلۡعُهَا هَضِيمٞ

148. «በአዝመራዎችም ፍሬዋ የበሰለ በሆነች ዘንባባም ውስጥ ትቀራላችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
149 : 26

وَتَنۡحِتُونَ مِنَ ٱلۡجِبَالِ بُيُوتٗا فَٰرِهِينَ

149. «ብልሆች ሆናችሁ ከጋራዎች ቤቶችንም ትጠርባላችሁ። info
التفاسير:

external-link copy
150 : 26

فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ

150. «አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም። info
التفاسير:

external-link copy
151 : 26

وَلَا تُطِيعُوٓاْ أَمۡرَ ٱلۡمُسۡرِفِينَ

151. «የወሰን አላፊዎችንም ትዕዛዝ አትከተሉ። info
التفاسير:

external-link copy
152 : 26

ٱلَّذِينَ يُفۡسِدُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَا يُصۡلِحُونَ

152. «የእነዚያን በምድር ላይ የሚያጠፉትንና የማያበጁትን (ትዕዛዝ አትከተሉ)።» (አለ) info
التفاسير:

external-link copy
153 : 26

قَالُوٓاْ إِنَّمَآ أَنتَ مِنَ ٱلۡمُسَحَّرِينَ

153. እነርሱም አሉ: «አንተ በብዙ ከተደገመባቸው ሰዎች ብቻ ነህ። info
التفاسير:

external-link copy
154 : 26

مَآ أَنتَ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُنَا فَأۡتِ بِـَٔايَةٍ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ

154. «አንተ ብጤያችን ሰው እንጂ ሌላ አይደለህም። ከእውነተኞችም ከሆንክ ተዐምርን አምጣ።» (አሉ) info
التفاسير:

external-link copy
155 : 26

قَالَ هَٰذِهِۦ نَاقَةٞ لَّهَا شِرۡبٞ وَلَكُمۡ شِرۡبُ يَوۡمٖ مَّعۡلُومٖ

155. እርሱም አለ: «ይህች ግመል ናት:: ለእርሷ የመጠጥ ፋንታ አላት:: ለእናንተም የታወቀ ቀን ፋንታ አላችሁ፤ info
التفاسير:

external-link copy
156 : 26

وَلَا تَمَسُّوهَا بِسُوٓءٖ فَيَأۡخُذَكُمۡ عَذَابُ يَوۡمٍ عَظِيمٖ

156. «በክፉም አትንኳት የታላቅ ቀን ቅጣት ይይዛችኋልና።» info
التفاسير:

external-link copy
157 : 26

فَعَقَرُوهَا فَأَصۡبَحُواْ نَٰدِمِينَ

157. ወጓትም:: ወዲያው ተጸፃቾች ሆነው አነጉ:: info
التفاسير:

external-link copy
158 : 26

فَأَخَذَهُمُ ٱلۡعَذَابُۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ

158. ቅጣትም ያዛቸው በዚህም ውስጥ አያሌ ግሣጼ አለበት:: አብዛኞቻቸዉም አማኞች አልነበሩም:: info
التفاسير:

external-link copy
159 : 26

وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ

159. ጌታህም እርሱ በእርግጥ ሁሉን አሸናፊውና አዛኙ ነው። info
التفاسير: