Vertaling van de betekenissen Edele Qur'an - De Amhaarse vertaling - Afrika Academie

አል ሒጅር

external-link copy
1 : 15

الٓرۚ تِلۡكَ ءَايَٰتُ ٱلۡكِتَٰبِ وَقُرۡءَانٖ مُّبِينٖ

1. አሊፍ፤ ላም፤ ራ፤ እነዚህ አናቅጽ ከመጽሐፍ አናቅጽና ገላጭ ከሆነው ቁርኣን ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
2 : 15

رُّبَمَا يَوَدُّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَوۡ كَانُواْ مُسۡلِمِينَ

2.እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች በትንሳኤ ቀን ሙስሊሞች በሆኑ ኖሮ ብለው በብዛት ይመኛሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 15

ذَرۡهُمۡ يَأۡكُلُواْ وَيَتَمَتَّعُواْ وَيُلۡهِهِمُ ٱلۡأَمَلُۖ فَسَوۡفَ يَعۡلَمُونَ

3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን ተዋቸው:: ይብሉ ይጠቀሙም:: ተስፋም ያዘናጋቸው:: በእርግጥም መጥፎ ፍጻሜያቸውን ያውቃሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 15

وَمَآ أَهۡلَكۡنَا مِن قَرۡيَةٍ إِلَّا وَلَهَا كِتَابٞ مَّعۡلُومٞ

4. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ማንኛይቱንም ከተማ ለእርሷ የተወሰነ መጽሐፍ ጊዜያት ያላት ሆና እንጂ አላጠፋንም:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 15

مَّا تَسۡبِقُ مِنۡ أُمَّةٍ أَجَلَهَا وَمَا يَسۡتَـٔۡخِرُونَ

5. ማንኛይቱም ሕዝብ የመጥፊያ ጊዜዋን በምንም ዘዴ አትቀድምም:: ከእርሱም በማንም ሀይል አትዘገይምም:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 15

وَقَالُواْ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِي نُزِّلَ عَلَيۡهِ ٱلذِّكۡرُ إِنَّكَ لَمَجۡنُونٞ

6. እነዚያ የመካ ከሓዲያን አሉ: «አንተ ያ በእርሱ ላይ ቁርኣን የተወረደለት ሆይ! አንተ በእርግጥ እብድ ነህ። info
التفاسير:

external-link copy
7 : 15

لَّوۡمَا تَأۡتِينَا بِٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ

7. «ከእውነተኞቹ እንደ ሆንክ መስካሪ መላዕክት ለምን አታመጣልንም?» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
8 : 15

مَا نُنَزِّلُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةَ إِلَّا بِٱلۡحَقِّ وَمَا كَانُوٓاْ إِذٗا مُّنظَرِينَ

8. መላእክትን ደግሞ በእውነት በቅጣት እንጂ አናወርድም:: ያን ጊዜም የሚቆዩ ጊዜ የሚሰጣቸው አይደሉም:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 15

إِنَّا نَحۡنُ نَزَّلۡنَا ٱلذِّكۡرَ وَإِنَّا لَهُۥ لَحَٰفِظُونَ

9. እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው:: እኛም ጠባቂዎቹ ነን:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 15

وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا مِن قَبۡلِكَ فِي شِيَعِ ٱلۡأَوَّلِينَ

10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተም በፊት በነበሩት በመጀመሪያዎቹ ሕዝቦች ውስጥ መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 15

وَمَا يَأۡتِيهِم مِّن رَّسُولٍ إِلَّا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ

11. ማንኛዉም መልዕክተኛ በእርሱ የሚያላግጡበት ሆነው እንጂ አይመጣላቸዉም ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 15

كَذَٰلِكَ نَسۡلُكُهُۥ فِي قُلُوبِ ٱلۡمُجۡرِمِينَ

12. ልክ እንደዚሁ ማስተባበልን በአመጸኞች ልቦች ውስጥ እናስገባዋለን:: info
التفاسير:

external-link copy
13 : 15

لَا يُؤۡمِنُونَ بِهِۦ وَقَدۡ خَلَتۡ سُنَّةُ ٱلۡأَوَّلِينَ

13. በእርሱ አያምኑበትም፤ የቀድሞዎቹም ድርጊት በእርግጥ አልፋለች (እንደጠፉ ይጠፋሉ):: info
التفاسير:

external-link copy
14 : 15

وَلَوۡ فَتَحۡنَا عَلَيۡهِم بَابٗا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ فَظَلُّواْ فِيهِ يَعۡرُجُونَ

14. በእነርሱም ላይ ከሰማይ ደጃፍን በከፈትንላቸውና በእርሱ ሲወጡ ቢውሉም info
التفاسير:

external-link copy
15 : 15

لَقَالُوٓاْ إِنَّمَا سُكِّرَتۡ أَبۡصَٰرُنَا بَلۡ نَحۡنُ قَوۡمٞ مَّسۡحُورُونَ

15. «የተዘጉ ዓይኖቻችን ተጭበርብረው ነው:: እንዲያዉም እኛ የተደገመብን ሰዎች ነን።» ባሉ ነበር። info
التفاسير: