Vertaling van de betekenissen Edele Qur'an - De Amhaarse vertaling - Afrika Academie

Pagina nummer:close

external-link copy
6 : 13

وَيَسۡتَعۡجِلُونَكَ بِٱلسَّيِّئَةِ قَبۡلَ ٱلۡحَسَنَةِ وَقَدۡ خَلَتۡ مِن قَبۡلِهِمُ ٱلۡمَثُلَٰتُۗ وَإِنَّ رَبَّكَ لَذُو مَغۡفِرَةٖ لِّلنَّاسِ عَلَىٰ ظُلۡمِهِمۡۖ وَإِنَّ رَبَّكَ لَشَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ

6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ በፊት የመሰሎቻቸው ቅጣቶች በእርግጥ ያለፉ ሲሆኑ ከመልካሙ በፊት በመጥፎ ያስቸኩሉሃል! ጌታህም ለሰዎች ሁሉ ከመበደላቸው ጋር በእርግጥ የምህረት ባለቤት ነው:: ጌታህ በእርግጥ ቅጣተ ብርቱም ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 13

وَيَقُولُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَوۡلَآ أُنزِلَ عَلَيۡهِ ءَايَةٞ مِّن رَّبِّهِۦٓۗ إِنَّمَآ أَنتَ مُنذِرٞۖ وَلِكُلِّ قَوۡمٍ هَادٍ

7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች «በእርሱ ላይ ከጌታው ተአምር ለምን አልተወረደለትም?» ይላሉ:: አንተ አስፈራሪ ብቻ ነህ፤ ለሕዝብም ሁሉ መሪ አለላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
8 : 13

ٱللَّهُ يَعۡلَمُ مَا تَحۡمِلُ كُلُّ أُنثَىٰ وَمَا تَغِيضُ ٱلۡأَرۡحَامُ وَمَا تَزۡدَادُۚ وَكُلُّ شَيۡءٍ عِندَهُۥ بِمِقۡدَارٍ

8. አላህ ሴት ሁሉ የምታረግዘውን ጽንስ ሁሉ ጠንቅቆ ያውቃል:: ማሕጸኖች የሚያጎድሉትንም ሆነ የሚጨምሩትን ያውቃል:: ነገሩ ሁሉ እርሱ ዘንድ በልክ የተወሰነ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 13

عَٰلِمُ ٱلۡغَيۡبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ ٱلۡكَبِيرُ ٱلۡمُتَعَالِ

9. ሩቁንና ቅርቡን አዋቂ የሆነ ታላቅና የላቀ ጌታ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 13

سَوَآءٞ مِّنكُم مَّنۡ أَسَرَّ ٱلۡقَوۡلَ وَمَن جَهَرَ بِهِۦ وَمَنۡ هُوَ مُسۡتَخۡفِۭ بِٱلَّيۡلِ وَسَارِبُۢ بِٱلنَّهَارِ

10. ከናንተ ውስጥ ቃሉን ዝቅ ያደረገ፤ በእርሱ የጮኸም፤ እርሱ በሌሊት ተደባቂም በቀን ተገልፆ ሂያጅም የሆነ ሁሉ (እርሱ አላህ ዘንድ) እኩል ነው (አላህ ያውቀዋል)። info
التفاسير:

external-link copy
11 : 13

لَهُۥ مُعَقِّبَٰتٞ مِّنۢ بَيۡنِ يَدَيۡهِ وَمِنۡ خَلۡفِهِۦ يَحۡفَظُونَهُۥ مِنۡ أَمۡرِ ٱللَّهِۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُغَيِّرُ مَا بِقَوۡمٍ حَتَّىٰ يُغَيِّرُواْ مَا بِأَنفُسِهِمۡۗ وَإِذَآ أَرَادَ ٱللَّهُ بِقَوۡمٖ سُوٓءٗا فَلَا مَرَدَّ لَهُۥۚ وَمَا لَهُم مِّن دُونِهِۦ مِن وَالٍ

11. ለእርሱ ለሰው በስተፊቱም ከኋላዉም በአላህ ትዕዛዝ ከክፉ የሚጠብቁት ተተካኪዎች መላዕክት አሉት:: አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን (ጸጋ) በነፍሶቻቸው ያለውን (ሁኔታ) እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም:: አላህም በሰዎች ላይ ክፉን በሻ ጊዜ ለእርሱ መመለስ የለዉም:: ለእነርሱም ከእርሱ ሌላ ምንም ተከላካይ የላቸዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 13

هُوَ ٱلَّذِي يُرِيكُمُ ٱلۡبَرۡقَ خَوۡفٗا وَطَمَعٗا وَيُنشِئُ ٱلسَّحَابَ ٱلثِّقَالَ

12. እርሱ ያ የምትፈሩና የምትከጅሉም ስትሆኑ ብልጭታን የሚያሳያችሁ ከባዶች ደመናዎችንም የሚያስገኝ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
13 : 13

وَيُسَبِّحُ ٱلرَّعۡدُ بِحَمۡدِهِۦ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ مِنۡ خِيفَتِهِۦ وَيُرۡسِلُ ٱلصَّوَٰعِقَ فَيُصِيبُ بِهَا مَن يَشَآءُ وَهُمۡ يُجَٰدِلُونَ فِي ٱللَّهِ وَهُوَ شَدِيدُ ٱلۡمِحَالِ

13. ነጎድጓድም አላህን በማመስገን ያጠራል:: መላዕክትም እርሱን ከመፍራት ያጠሩታል፤ መብረቆችም ይልካል። እነርሱም (ከሓዲያን) በአላህ የሚከራከሩ ሲሆኑ በእርሷ የሚሻውን ሰው ይመታል:: እርሱም ሀይለ ብርቱ ነው:: info
التفاسير: