Vertaling van de betekenissen Edele Qur'an - Amhaarse vertaling - Mohammed Sadiq

Pagina nummer:close

external-link copy
32 : 39

۞ فَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّن كَذَبَ عَلَى ٱللَّهِ وَكَذَّبَ بِٱلصِّدۡقِ إِذۡ جَآءَهُۥٓۚ أَلَيۡسَ فِي جَهَنَّمَ مَثۡوٗى لِّلۡكَٰفِرِينَ

በአላህም ላይ ከዋሸ እውነቱንም በመጣለት ጊዜ ከአስተባበለ ሰው ይበልጥ በዳይ ማን ነው? ገሀነም ውስጥለከሃዲዎች መኖሪያ የለምን? (አለ)። info
التفاسير:

external-link copy
33 : 39

وَٱلَّذِي جَآءَ بِٱلصِّدۡقِ وَصَدَّقَ بِهِۦٓ أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُتَّقُونَ

ያም በእውነት የመጣው በእርሱ ያመነውም እነዚያ እነርሱ አላህን ፊሪዎች ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
34 : 39

لَهُم مَّا يَشَآءُونَ عِندَ رَبِّهِمۡۚ ذَٰلِكَ جَزَآءُ ٱلۡمُحۡسِنِينَ

ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ የሚሹት ሁሉ አልላቸው፡፡ ይህ የበጎ አድራጊዎች ምንዳ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
35 : 39

لِيُكَفِّرَ ٱللَّهُ عَنۡهُمۡ أَسۡوَأَ ٱلَّذِي عَمِلُواْ وَيَجۡزِيَهُمۡ أَجۡرَهُم بِأَحۡسَنِ ٱلَّذِي كَانُواْ يَعۡمَلُونَ

አላህ ያንን (በስሕተት) የሠሩትን መጥፎ ሥራ ከእነርሱ ሊሰርይላቸው በዚያም ይሠሩት በነበሩት በመልካሙ ሥራ ምንዳቸውን ሊመነዳቸው (ይህንን አደረገ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
36 : 39

أَلَيۡسَ ٱللَّهُ بِكَافٍ عَبۡدَهُۥۖ وَيُخَوِّفُونَكَ بِٱلَّذِينَ مِن دُونِهِۦۚ وَمَن يُضۡلِلِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِنۡ هَادٖ

አላህ ባሪያውን በቂ አይደለምን? በእነዚያ ከእርሱ ሌላ በኾኑትም (ጣዖታት) ያስፈራሩሃል፡፡ አላህ የሚያጠመውም ሰው ለርሱ ምንም አቅኚ የለውም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
37 : 39

وَمَن يَهۡدِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِن مُّضِلٍّۗ أَلَيۡسَ ٱللَّهُ بِعَزِيزٖ ذِي ٱنتِقَامٖ

አላህ የሚያቀናውም ሰው ለእርሱ ምንም አጥማሚ የለውም፡፡ አላህ አሸናፊ የመበቀል ባለቤት አይደለምን? info
التفاسير:

external-link copy
38 : 39

وَلَئِن سَأَلۡتَهُم مَّنۡ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ لَيَقُولُنَّ ٱللَّهُۚ قُلۡ أَفَرَءَيۡتُم مَّا تَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ إِنۡ أَرَادَنِيَ ٱللَّهُ بِضُرٍّ هَلۡ هُنَّ كَٰشِفَٰتُ ضُرِّهِۦٓ أَوۡ أَرَادَنِي بِرَحۡمَةٍ هَلۡ هُنَّ مُمۡسِكَٰتُ رَحۡمَتِهِۦۚ قُلۡ حَسۡبِيَ ٱللَّهُۖ عَلَيۡهِ يَتَوَكَّلُ ٱلۡمُتَوَكِّلُونَ

ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ማን እንደ ኾነ ብትጠይቃቸው «አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸውን (ጣዖታት) አያችሁን? (ንገሩኝ) አላህ በጉዳት ቢፈልገኝ እነርሱ ጉዳቱን ገላጮች ናቸውን? ወይስ በችሮታው ቢፈቅደኝ እነርሱ ችሮታውን አጋጆች ናቸውን?» በላቸው፡፡ «አላህ በቂዬ ነው፡፡ በእርሱ ላይ ተመኪዎች ይመካሉ» በል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
39 : 39

قُلۡ يَٰقَوۡمِ ٱعۡمَلُواْ عَلَىٰ مَكَانَتِكُمۡ إِنِّي عَٰمِلٞۖ فَسَوۡفَ تَعۡلَمُونَ

(ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው «ሕዝቦቼ ሆይ! ባላችሁበት ኹኔታ ላይ ሥሩ፡፡ እኔ ሠሪ ነኝና፡፡ ወደፊትም ታውቃላችሁ፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
40 : 39

مَن يَأۡتِيهِ عَذَابٞ يُخۡزِيهِ وَيَحِلُّ عَلَيۡهِ عَذَابٞ مُّقِيمٌ

ያንን የሚያሳፍረው ቅጣት የሚመጠበትንና በእርሱ ላይ ዘውታሪ ቅጣት የሚሰፍርበትን (ታውቃላችሁ) info
التفاسير: