وه‌رگێڕانی ماناكانی قورئانی پیرۆز - وەرگێڕاوی ئەمهەری - ئەکادیمیای ئەفریقا

ژمارەی پەڕە:close

external-link copy
105 : 7

حَقِيقٌ عَلَىٰٓ أَن لَّآ أَقُولَ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلۡحَقَّۚ قَدۡ جِئۡتُكُم بِبَيِّنَةٖ مِّن رَّبِّكُمۡ فَأَرۡسِلۡ مَعِيَ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ

105. «በአላህ ላይ ከእውነት በስተቀር አለመናገር ተገቢዬ ነው:: ከጌታችሁ ተዓምር ይዤ መጥቻለሁና የኢስራኢል ልጆችን ከእኔ ጋር ልቀቅ።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
106 : 7

قَالَ إِن كُنتَ جِئۡتَ بِـَٔايَةٖ فَأۡتِ بِهَآ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ

106. ፈርዖንም፡ «በተዓምር የመጣህ ከሆንክና ከእውነተኞቹ ከሆንክ እስቲ አምጣት።» አለው። info
التفاسير:

external-link copy
107 : 7

فَأَلۡقَىٰ عَصَاهُ فَإِذَا هِيَ ثُعۡبَانٞ مُّبِينٞ

107. ሙሳም ዘንጉን ምድር ላይ ጣለ:: እርሷም ወዲያውኑ ግልጽ እባብ ሆነች:: info
التفاسير:

external-link copy
108 : 7

وَنَزَعَ يَدَهُۥ فَإِذَا هِيَ بَيۡضَآءُ لِلنَّٰظِرِينَ

108. እጁንም አወጣ:: እርሷም ወዲያውኑ ለተመልካቾች ነጭ ሆነች:: info
التفاسير:

external-link copy
109 : 7

قَالَ ٱلۡمَلَأُ مِن قَوۡمِ فِرۡعَوۡنَ إِنَّ هَٰذَا لَسَٰحِرٌ عَلِيمٞ

109. ከፈርዖን ሰዎች መማክርቶቹም አሉ፡ «ይህ በእርግጥ አዋቂ ድግምተኛ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
110 : 7

يُرِيدُ أَن يُخۡرِجَكُم مِّنۡ أَرۡضِكُمۡۖ فَمَاذَا تَأۡمُرُونَ

110. «ከምድራችሁ ሊያወጣችሁ ይሻል።» አሉ። (ፊርዓውንም) «ታዲያ ምን? ታዛላችሁ?» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
111 : 7

قَالُوٓاْ أَرۡجِهۡ وَأَخَاهُ وَأَرۡسِلۡ فِي ٱلۡمَدَآئِنِ حَٰشِرِينَ

111. እነርሱም አሉ: «እርሱንና ወንድሙን አቆያቸው:: ወደ ከተሞቹ ሁሉ ሰብሳቢዎችን ላክ:: info
التفاسير:

external-link copy
112 : 7

يَأۡتُوكَ بِكُلِّ سَٰحِرٍ عَلِيمٖ

112. «አዋቂ ድግምተኞችን ሁሉ ያመጡልሃልና።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
113 : 7

وَجَآءَ ٱلسَّحَرَةُ فِرۡعَوۡنَ قَالُوٓاْ إِنَّ لَنَا لَأَجۡرًا إِن كُنَّا نَحۡنُ ٱلۡغَٰلِبِينَ

113. ድግምተኞቹም ወደ ፈርዖን መጡና «እኛ አሸናፊዎች ብንሆን ለኛ ክፍያ አለን?» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
114 : 7

قَالَ نَعَمۡ وَإِنَّكُمۡ لَمِنَ ٱلۡمُقَرَّبِينَ

114. ፈርዖንም: «አዎን። እናንተ እኔ ዘንድ ከባለሟሎቹ ትሆናላችሁ።» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
115 : 7

قَالُواْ يَٰمُوسَىٰٓ إِمَّآ أَن تُلۡقِيَ وَإِمَّآ أَن نَّكُونَ نَحۡنُ ٱلۡمُلۡقِينَ

115. እነርሱም «ሙሳ ሆይ! ዘንግህን በፊት ትጥላለህ ወይስ ፊት ጣዮቹ እኛ እንሁን?» አሉት። info
التفاسير:

external-link copy
116 : 7

قَالَ أَلۡقُواْۖ فَلَمَّآ أَلۡقَوۡاْ سَحَرُوٓاْ أَعۡيُنَ ٱلنَّاسِ وَٱسۡتَرۡهَبُوهُمۡ وَجَآءُو بِسِحۡرٍ عَظِيمٖ

116. ሙሳም «በፊት እናንተ ጣሉ።» አላቸው:: ከዚያም ገመዶቻቸውን በጣሉ ጊዜ የሰዎቹን ዓይኖች ደገሙባቸውና አስፈራሯቸው:: ትልቅ ድግምትንም አመጡ:: info
التفاسير:

external-link copy
117 : 7

۞ وَأَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ أَنۡ أَلۡقِ عَصَاكَۖ فَإِذَا هِيَ تَلۡقَفُ مَا يَأۡفِكُونَ

117. ወደ ሙሳም «ዘንግህን ጣል» ስንል ላክንበት (ጣላትም) ወዲውኑም የሚቀጣጥፉትን ማታለያ ሁሉ መዋጥ ጀመረች:: info
التفاسير:

external-link copy
118 : 7

فَوَقَعَ ٱلۡحَقُّ وَبَطَلَ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ

118. እውነቱም ተገለጸ:: ይሠሩት የነበሩት ድግምትም ተበላሸ:: info
التفاسير:

external-link copy
119 : 7

فَغُلِبُواْ هُنَالِكَ وَٱنقَلَبُواْ صَٰغِرِينَ

119. እዚያ ላይ ተሸነፉና ወራዶች ሆነው ተመለሱ:: info
التفاسير:

external-link copy
120 : 7

وَأُلۡقِيَ ٱلسَّحَرَةُ سَٰجِدِينَ

120. ድግምተኞቹም ሰጋጆች ሆነው ሱጁድ ወረዱ:: info
التفاسير: