وه‌رگێڕانی ماناكانی قورئانی پیرۆز - وەرگێڕاوی ئەمهەری - ئەکادیمیای ئەفریقا

ژمارەی پەڕە:close

external-link copy
88 : 7

۞ قَالَ ٱلۡمَلَأُ ٱلَّذِينَ ٱسۡتَكۡبَرُواْ مِن قَوۡمِهِۦ لَنُخۡرِجَنَّكَ يَٰشُعَيۡبُ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مَعَكَ مِن قَرۡيَتِنَآ أَوۡ لَتَعُودُنَّ فِي مِلَّتِنَاۚ قَالَ أَوَلَوۡ كُنَّا كَٰرِهِينَ

88. ከህዝቦቹ መካከል እነዚያ የኮሩት መሪዎችም፡- «ሹዐይብ ሆይ! አንተንና እነዚያን ካንተ ጋር ያመኑትን ከከተማችን እናወጣችኋለን ወይም ወደ ሃይማኖታችን መመለስ አለባችሁ።» አሉ:: እርሱም አላቸው: «የጠላንም ብንሆን? info
التفاسير:

external-link copy
89 : 7

قَدِ ٱفۡتَرَيۡنَا عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا إِنۡ عُدۡنَا فِي مِلَّتِكُم بَعۡدَ إِذۡ نَجَّىٰنَا ٱللَّهُ مِنۡهَاۚ وَمَا يَكُونُ لَنَآ أَن نَّعُودَ فِيهَآ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُ رَبُّنَاۚ وَسِعَ رَبُّنَا كُلَّ شَيۡءٍ عِلۡمًاۚ عَلَى ٱللَّهِ تَوَكَّلۡنَاۚ رَبَّنَا ٱفۡتَحۡ بَيۡنَنَا وَبَيۡنَ قَوۡمِنَا بِٱلۡحَقِّ وَأَنتَ خَيۡرُ ٱلۡفَٰتِحِينَ

89. «አላህ ከእርሷ ከአዳንን በኋላ ወደ ሃይማኖታችሁ ብንመለስ በአላህ ላይ ውሸትን ቀጠፍን:: አላህ ጌታችን ካልሻም በስተቀር ወደ እርሷ ልንመለስ አይገባንም:: የጌታችን እውቀቱ ከሁሉ ሰፋ:: በአላህ ላይ ብቻ ተመካን:: ጌታችን ሆይ! በእኛና በወገኖቻችን መካከል ፍረድ:: አንተም ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ነህና።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
90 : 7

وَقَالَ ٱلۡمَلَأُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِن قَوۡمِهِۦ لَئِنِ ٱتَّبَعۡتُمۡ شُعَيۡبًا إِنَّكُمۡ إِذٗا لَّخَٰسِرُونَ

90. ከወገኖቹም መካከል እነዚያ በአላህ የካዱት መሪዎች ለሕዝቡ «ሹዐይብን ብትከተሉ እናንተ ያኔ ከሳሪዎች ናችሁ።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
91 : 7

فَأَخَذَتۡهُمُ ٱلرَّجۡفَةُ فَأَصۡبَحُواْ فِي دَارِهِمۡ جَٰثِمِينَ

91. ወዲያውኑ የምድር መንቀጥቀጥ ያዘቻቸው:: በየቤታቸው ውስጥ ተደፍተው አደሩ:: info
التفاسير:

external-link copy
92 : 7

ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ شُعَيۡبٗا كَأَن لَّمۡ يَغۡنَوۡاْ فِيهَاۚ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ شُعَيۡبٗا كَانُواْ هُمُ ٱلۡخَٰسِرِينَ

92. እነዚያ ሹዓይብን ያስተባበሉት ሰዎች በእርሷ እንዳልነበሩባት ሆኑ:: እነዚያ ሹዓይብን ያስተባበሉት ከሳሪዎቹ እነርሱው ሆኑ:: info
التفاسير:

external-link copy
93 : 7

فَتَوَلَّىٰ عَنۡهُمۡ وَقَالَ يَٰقَوۡمِ لَقَدۡ أَبۡلَغۡتُكُمۡ رِسَٰلَٰتِ رَبِّي وَنَصَحۡتُ لَكُمۡۖ فَكَيۡفَ ءَاسَىٰ عَلَىٰ قَوۡمٖ كَٰفِرِينَ

93. ሹዐይብም ትቷቸው ከእነርሱ ዞረና «ወገኖቼ ሆይ! የጌታዬን መልእክቶች በእርግጥ አደረስኩላችሁ። ለእናንተም መከርኩ:: ታዲያ በከሃዲ ሰዎች ላይ እንዴት አዝናለሁ?» አለ:: info
التفاسير:

external-link copy
94 : 7

وَمَآ أَرۡسَلۡنَا فِي قَرۡيَةٖ مِّن نَّبِيٍّ إِلَّآ أَخَذۡنَآ أَهۡلَهَا بِٱلۡبَأۡسَآءِ وَٱلضَّرَّآءِ لَعَلَّهُمۡ يَضَّرَّعُونَ

94. በየትኛዉም ከተማ ለአላህ ይተናነሱ ዘንድ በድህነትና በችግር የያዝናቸው ብንሆን እንጂ አንድንም ነብይ አልላክንም:: info
التفاسير:

external-link copy
95 : 7

ثُمَّ بَدَّلۡنَا مَكَانَ ٱلسَّيِّئَةِ ٱلۡحَسَنَةَ حَتَّىٰ عَفَواْ وَّقَالُواْ قَدۡ مَسَّ ءَابَآءَنَا ٱلضَّرَّآءُ وَٱلسَّرَّآءُ فَأَخَذۡنَٰهُم بَغۡتَةٗ وَهُمۡ لَا يَشۡعُرُونَ

95.ከዚያም እስከበዙና «አባቶቻችንን ድህነትና በሺታ በእርግጥ ነክቷቸዋል፡፡ (ይኽም የጊዜ ልማድ ነው)» እስካሉ ድረስ በመጥፎው ስፍራ በጎውን ለወጥን፡፡ ወዲያውም እነርሱ የማያውቁ ኾነው በድንገት ያዝናቸው፡፡ info
التفاسير: