وه‌رگێڕانی ماناكانی قورئانی پیرۆز - وەرگێڕاوی ئەمهەری - ئەکادیمیای ئەفریقا

ژمارەی پەڕە:close

external-link copy
71 : 5

وَحَسِبُوٓاْ أَلَّا تَكُونَ فِتۡنَةٞ فَعَمُواْ وَصَمُّواْ ثُمَّ تَابَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِمۡ ثُمَّ عَمُواْ وَصَمُّواْ كَثِيرٞ مِّنۡهُمۡۚ وَٱللَّهُ بَصِيرُۢ بِمَا يَعۡمَلُونَ

71. በእነርሱ ላይ ፈተና አለመኖሩዋን ጠረጠሩምና ታወሩ ደነቆሩም:: ከዚያም አላህ ከእነርሱ ላይ ጸጸትን ተቀበለ:: ከዚያም ከእነርሱ ብዙዎቹ እንደገና ታወሩ ደነቆሩ:: አላህ የሚሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
72 : 5

لَقَدۡ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُوٓاْ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلۡمَسِيحُ ٱبۡنُ مَرۡيَمَۖ وَقَالَ ٱلۡمَسِيحُ يَٰبَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمۡۖ إِنَّهُۥ مَن يُشۡرِكۡ بِٱللَّهِ فَقَدۡ حَرَّمَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِ ٱلۡجَنَّةَ وَمَأۡوَىٰهُ ٱلنَّارُۖ وَمَا لِلظَّٰلِمِينَ مِنۡ أَنصَارٖ

72. እነዚያ «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲህ ነው።» ያሉ በእርግጥ በአላህ ካዱ:: አል መሲህም አለ፡- «የኢስራኢል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ብቻ ተገዙ:: እነሆ በአላህ የሚያጋራ ሰው ሁሉ አላህ በእርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ:: መኖሪያዉም እሳት ናት:: ለበዳዩችም ምንም ረዳቶች የሏቸዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
73 : 5

لَّقَدۡ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُوٓاْ إِنَّ ٱللَّهَ ثَالِثُ ثَلَٰثَةٖۘ وَمَا مِنۡ إِلَٰهٍ إِلَّآ إِلَٰهٞ وَٰحِدٞۚ وَإِن لَّمۡ يَنتَهُواْ عَمَّا يَقُولُونَ لَيَمَسَّنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِنۡهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٌ

73. እነዚያ «አላህ የሶስት ሶስተኛ ነው።» ያሉ በእርግጥ ሁሉ ካዱ። ከአምላክም አንድ አምላክ ብቻ እንጂ ሌላ አምላክ የለም:: ከሚሉትም ነገር ካልተከለከሉ እነዚያን የካዱትን ሁሉ አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ይነካቸዋል። info
التفاسير:

external-link copy
74 : 5

أَفَلَا يَتُوبُونَ إِلَى ٱللَّهِ وَيَسۡتَغۡفِرُونَهُۥۚ وَٱللَّهُ غَفُورٞ رَّحِيمٞ

74. ለመሆኑ እንደነዚህ አይነቶች ወደ አላህ አይመለሱምና ምህረትን አይለምኑትምን? አላህ መሀሪና አዛኝ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
75 : 5

مَّا ٱلۡمَسِيحُ ٱبۡنُ مَرۡيَمَ إِلَّا رَسُولٞ قَدۡ خَلَتۡ مِن قَبۡلِهِ ٱلرُّسُلُ وَأُمُّهُۥ صِدِّيقَةٞۖ كَانَا يَأۡكُلَانِ ٱلطَّعَامَۗ ٱنظُرۡ كَيۡفَ نُبَيِّنُ لَهُمُ ٱلۡأٓيَٰتِ ثُمَّ ٱنظُرۡ أَنَّىٰ يُؤۡفَكُونَ

75. የመርየም ልጅ አልመሲህ ከበፊቱ ብዙ መልዕክተኞች የቀደሙት መልዕክተኛ እንጂ ሌላ አይደለም:: እናቱም በጣም እውነተኛ አማኝ ናት:: ሁለቱም ምግብን የሚበሉ ነበሩ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አናቅጽን ለከሓዲያን እንዴት እንደምናብራራና ከዚያ እነርሱ ከእውነት እንዴት እንደሚመለሱ ተመልከት:: info
التفاسير:

external-link copy
76 : 5

قُلۡ أَتَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَمۡلِكُ لَكُمۡ ضَرّٗا وَلَا نَفۡعٗاۚ وَٱللَّهُ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ

76. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከአላህ ሌላ ለእናንተ መጉዳትንና መጥቀምን የማይችልን ትገዛላችሁን? አላህ እርሱ ሁሉን ሰሚና ሁሉን አዋቂ ነው።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
77 : 5

قُلۡ يَٰٓأَهۡلَ ٱلۡكِتَٰبِ لَا تَغۡلُواْ فِي دِينِكُمۡ غَيۡرَ ٱلۡحَقِّ وَلَا تَتَّبِعُوٓاْ أَهۡوَآءَ قَوۡمٖ قَدۡ ضَلُّواْ مِن قَبۡلُ وَأَضَلُّواْ كَثِيرٗا وَضَلُّواْ عَن سَوَآءِ ٱلسَّبِيلِ

77. (መልዕክተኛች ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ከእውነት ውጭ ወሰንን አትለፉ:: ፊትም የተሳሳቱትንና ብዙዎቹን ህዝቦች ያሳሳቱትን ከቀጥተኛው መንገድም አሁን የተሳሳቱትን ህዝቦች ከንቱ ዝንባሌዎች (ስሜቶች) አትከተሉ።» በላቸው:: info
التفاسير: