وه‌رگێڕانی ماناكانی قورئانی پیرۆز - وەرگێڕاوی ئەمهەری - ئەکادیمیای ئەفریقا

ژمارەی پەڕە:close

external-link copy
42 : 5

سَمَّٰعُونَ لِلۡكَذِبِ أَكَّٰلُونَ لِلسُّحۡتِۚ فَإِن جَآءُوكَ فَٱحۡكُم بَيۡنَهُمۡ أَوۡ أَعۡرِضۡ عَنۡهُمۡۖ وَإِن تُعۡرِضۡ عَنۡهُمۡ فَلَن يَضُرُّوكَ شَيۡـٔٗاۖ وَإِنۡ حَكَمۡتَ فَٱحۡكُم بَيۡنَهُم بِٱلۡقِسۡطِۚ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلۡمُقۡسِطِينَ

42. እነርሱ ውሸትን አድማጮች፤ እርም የሆኑ ነገሮችን በላተኞች ናቸው:: እናም ለዳኝነት ወደ አንተ ዘንድ ከመጡ በመካከላቸው በትክክል ፍረድ። ወይም ተዋቸው:: ብትተዋቸው በምንም አይጎዱሁም:: ከፈረድክ ግን በመካከላቸው በትክክል ፍረድ:: አላህ በትክክል ፈራጆችን ይወዳልና:: info
التفاسير:

external-link copy
43 : 5

وَكَيۡفَ يُحَكِّمُونَكَ وَعِندَهُمُ ٱلتَّوۡرَىٰةُ فِيهَا حُكۡمُ ٱللَّهِ ثُمَّ يَتَوَلَّوۡنَ مِنۢ بَعۡدِ ذَٰلِكَۚ وَمَآ أُوْلَٰٓئِكَ بِٱلۡمُؤۡمِنِينَ

43. እነርሱ ዘንድ በውስጧ የአላህ ፍርድ ያለባት ተውራት እያለ እንዴት ያስፈርዱሃል? ከዚያ በኋላ ይሸሻሉ። እነዚያ በፍጹም ትክክለኛ አማኞች አይደሉም:: info
التفاسير:

external-link copy
44 : 5

إِنَّآ أَنزَلۡنَا ٱلتَّوۡرَىٰةَ فِيهَا هُدٗى وَنُورٞۚ يَحۡكُمُ بِهَا ٱلنَّبِيُّونَ ٱلَّذِينَ أَسۡلَمُواْ لِلَّذِينَ هَادُواْ وَٱلرَّبَّٰنِيُّونَ وَٱلۡأَحۡبَارُ بِمَا ٱسۡتُحۡفِظُواْ مِن كِتَٰبِ ٱللَّهِ وَكَانُواْ عَلَيۡهِ شُهَدَآءَۚ فَلَا تَخۡشَوُاْ ٱلنَّاسَ وَٱخۡشَوۡنِ وَلَا تَشۡتَرُواْ بِـَٔايَٰتِي ثَمَنٗا قَلِيلٗاۚ وَمَن لَّمۡ يَحۡكُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡكَٰفِرُونَ

44. ተውራትን በውስጡ ለሰዎች መመሪያና ብርሃን ያለባት ሲሆን አወረድነው:: እነዚያ ትዕዛዙን የተቀበሉት ነብያት በአይሁዳውያን ላይ በእርሱ ይፈርዳሉ:: ሊቃውንቱና አዋቂዎቹም ከአላህ መጽሐፍን እንዲጠብቁ በተደረጉትና በእርሱ ላይ መስካሪዎቹ በመሆናቸው እንዲሁ በሱ ይፈርዳሉ:: እናም ሰዎችን አትፍሩ:: እኔን ብቻ ፍሩኝ:: በአንቀፆቼም አነስተኛን ዋጋ አትለውጡ አትግዙ:: እነዚያ አላህ ባወረደው መመሪያ ያልፈረዱ ሁሉ ከሓዲያን ማለት እነርሱው ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
45 : 5

وَكَتَبۡنَا عَلَيۡهِمۡ فِيهَآ أَنَّ ٱلنَّفۡسَ بِٱلنَّفۡسِ وَٱلۡعَيۡنَ بِٱلۡعَيۡنِ وَٱلۡأَنفَ بِٱلۡأَنفِ وَٱلۡأُذُنَ بِٱلۡأُذُنِ وَٱلسِّنَّ بِٱلسِّنِّ وَٱلۡجُرُوحَ قِصَاصٞۚ فَمَن تَصَدَّقَ بِهِۦ فَهُوَ كَفَّارَةٞ لَّهُۥۚ وَمَن لَّمۡ يَحۡكُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ

45. በእነርሱም ላይ በውስጡ ነፍስን በነፍስ፤ አይንን በአይን፤ አፍንጫን በአፍንጫ፤ ጆሮን በጆሮ፤ ጥርስን በጥርስ፤ ይያዛል:: ቁስሎችንም ማመሳሰል አለባቸው ብለን ደነገግን:: ይህንን መብቱን ይቅር ያለ ሁሉ እርሱ ለኃጢአቱ ማሰረዣው ነው:: አላህ ባወረደው መመሪያ የማይፈርዱ ሁሉ እነዚያ በደለኞቹ ማለት እነርሱ ናቸው:: info
التفاسير: