وه‌رگێڕانی ماناكانی قورئانی پیرۆز - وەرگێڕاوی ئەمهەری - ئەکادیمیای ئەفریقا

ژمارەی پەڕە:close

external-link copy
36 : 33

وَمَا كَانَ لِمُؤۡمِنٖ وَلَا مُؤۡمِنَةٍ إِذَا قَضَى ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥٓ أَمۡرًا أَن يَكُونَ لَهُمُ ٱلۡخِيَرَةُ مِنۡ أَمۡرِهِمۡۗ وَمَن يَعۡصِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ فَقَدۡ ضَلَّ ضَلَٰلٗا مُّبِينٗا

36. አላህና መልዕክተኛው በአንድ ነገር ላይ በወሰኑ ጊዜ ለምዕምናንና ለምዕመናት ከተነገራቸው ከመቀበል ዉጭ ምንም ምርጫ ሊኖራቸው አይገባም:: የአላህንና የመልክተኛውን ትእዛዝ የጣሰ ሰው ሁሉ ግልጽ የሆነን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ:: info
التفاسير:

external-link copy
37 : 33

وَإِذۡ تَقُولُ لِلَّذِيٓ أَنۡعَمَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِ وَأَنۡعَمۡتَ عَلَيۡهِ أَمۡسِكۡ عَلَيۡكَ زَوۡجَكَ وَٱتَّقِ ٱللَّهَ وَتُخۡفِي فِي نَفۡسِكَ مَا ٱللَّهُ مُبۡدِيهِ وَتَخۡشَى ٱلنَّاسَ وَٱللَّهُ أَحَقُّ أَن تَخۡشَىٰهُۖ فَلَمَّا قَضَىٰ زَيۡدٞ مِّنۡهَا وَطَرٗا زَوَّجۡنَٰكَهَا لِكَيۡ لَا يَكُونَ عَلَى ٱلۡمُؤۡمِنِينَ حَرَجٞ فِيٓ أَزۡوَٰجِ أَدۡعِيَآئِهِمۡ إِذَا قَضَوۡاْ مِنۡهُنَّ وَطَرٗاۚ وَكَانَ أَمۡرُ ٱللَّهِ مَفۡعُولٗا

37. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለዚያም አላህ በእርሱ ላይ ለለገሰለትና አንተም (ነጻ በማውጣት) በእርሱ ላይ ለለገስክለት ሰው አላህ ገላጩ የሆነን ነገር በነፍስህ ውስጥ የምትደብቅና አላህን ልትፈራው ይልቅ የተገባው ሲሆን ሰዎችን የምትፈራ ሆነህ «ሚስትህን ያዝ:: አላህንም ፍራ» በምትል ጊዜ (የሆነዉን አስታውስ):: ዘይድም ከእርሷ ጉዳዩን በፈጸመ ጊዜ በምዕመኖች ላይ ልጅ አድርገው ባስጠጓቸው ሰዎች ሚስቶች ከእነርሱ ጉዳይን በፈጸሙ ጊዜ በማግባት ችግር እንዳይደርስባቸው እርሷን አጋባንህ (ዳርንህ):: የአላህም ትእዛዝ ተፈጻሚ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
38 : 33

مَّا كَانَ عَلَى ٱلنَّبِيِّ مِنۡ حَرَجٖ فِيمَا فَرَضَ ٱللَّهُ لَهُۥۖ سُنَّةَ ٱللَّهِ فِي ٱلَّذِينَ خَلَوۡاْ مِن قَبۡلُۚ وَكَانَ أَمۡرُ ٱللَّهِ قَدَرٗا مَّقۡدُورًا

38. በነብዩ ላይ አላህ ለእርሱ በፈረደው ነገር ምንም ችግር ሊኖርበት አይገባም:: በእነዚያ ከዚያ በፊት ባለፉት ነብያት አላህ ደነገገው። የአላህም ትእዛዝ የተፈረደ ፍርድ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
39 : 33

ٱلَّذِينَ يُبَلِّغُونَ رِسَٰلَٰتِ ٱللَّهِ وَيَخۡشَوۡنَهُۥ وَلَا يَخۡشَوۡنَ أَحَدًا إِلَّا ٱللَّهَۗ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ حَسِيبٗا

39. ለእነዚያ የአላህን መልዕክቶች ለሚያደርሱና ለሚፈሩት ከአላህ በስተቀርም አንድንም ለማይፈሩት ተደነገገ። ተቆጣጣሪነትም በአላህ በቃ:: info
التفاسير:

external-link copy
40 : 33

مَّا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَآ أَحَدٖ مِّن رِّجَالِكُمۡ وَلَٰكِن رَّسُولَ ٱللَّهِ وَخَاتَمَ ٱلنَّبِيِّـۧنَۗ وَكَانَ ٱللَّهُ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٗا

40. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንዱም ሰው አባት አይደለም:: ግን የአላህ መልዕክተኛና የነብያት መደምደሚያ ነው:: አላህ በነገሩ ሁሉ አዋቂ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
41 : 33

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱذۡكُرُواْ ٱللَّهَ ذِكۡرٗا كَثِيرٗا

41. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ብዙ ማውሳትን አውሱት:: info
التفاسير:

external-link copy
42 : 33

وَسَبِّحُوهُ بُكۡرَةٗ وَأَصِيلًا

42. በቀኑ መጀመሪያና መጨረሻም አጥሩት:: info
التفاسير:

external-link copy
43 : 33

هُوَ ٱلَّذِي يُصَلِّي عَلَيۡكُمۡ وَمَلَٰٓئِكَتُهُۥ لِيُخۡرِجَكُم مِّنَ ٱلظُّلُمَٰتِ إِلَى ٱلنُّورِۚ وَكَانَ بِٱلۡمُؤۡمِنِينَ رَحِيمٗا

43. እርሱ ያ በእናንተ ላይ እዝነትን የሚያወርድ ነው:: መላእክቶችም እንደዚሁ ምህረትን የሚለምኑላችሁ ናቸው:: ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣችሁ ዘንድ (ያዝንላችኋል):: ለትክክለኛ አማኞችም በጣም አዛኝ ነው:: info
التفاسير: