وه‌رگێڕانی ماناكانی قورئانی پیرۆز - وەرگێڕاوی ئەمهەری - ئەکادیمیای ئەفریقا

ژمارەی پەڕە:close

external-link copy
16 : 33

قُل لَّن يَنفَعَكُمُ ٱلۡفِرَارُ إِن فَرَرۡتُم مِّنَ ٱلۡمَوۡتِ أَوِ ٱلۡقَتۡلِ وَإِذٗا لَّا تُمَتَّعُونَ إِلَّا قَلِيلٗا

16. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከሞት ወይም ከመገደል ብትሸሹ መሸሻችሁ ፈጽሞ አይጠቅማችሁም:: ያን ጊዜም ጥቂትን እንጂ የምትጣቀሙ አትደረጉም።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
17 : 33

قُلۡ مَن ذَا ٱلَّذِي يَعۡصِمُكُم مِّنَ ٱللَّهِ إِنۡ أَرَادَ بِكُمۡ سُوٓءًا أَوۡ أَرَادَ بِكُمۡ رَحۡمَةٗۚ وَلَا يَجِدُونَ لَهُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ وَلِيّٗا وَلَا نَصِيرٗا

17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (ሙስሊምቸ ሆይ!) «አላህ በእናንተ ላይ ክፉን ነገር ቢሻ ያ ከአላህ የሚጠብቃችሁ ማን ነው? ወይም ለእናንተ እዝነትን ቢፈልግ ክፉ የሚያመጣባችሁ ማን ነው?» በላቸው። ከአላህም ሌላ ለእነርሱ ወዳጅም ሆነ ረዳት አያገኙም። info
التفاسير:

external-link copy
18 : 33

۞ قَدۡ يَعۡلَمُ ٱللَّهُ ٱلۡمُعَوِّقِينَ مِنكُمۡ وَٱلۡقَآئِلِينَ لِإِخۡوَٰنِهِمۡ هَلُمَّ إِلَيۡنَاۖ وَلَا يَأۡتُونَ ٱلۡبَأۡسَ إِلَّا قَلِيلًا

18. ከናንተ ውስጥ የሚያደናቅፉትን ለወንድሞቻቸዉም «ወደ እኛ ኑ» የሚሉትን፤ ውጊያንም ጥቂትን እንጂ የማይመጡትን በእርግጥ አላህ ያውቃቸዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
19 : 33

أَشِحَّةً عَلَيۡكُمۡۖ فَإِذَا جَآءَ ٱلۡخَوۡفُ رَأَيۡتَهُمۡ يَنظُرُونَ إِلَيۡكَ تَدُورُ أَعۡيُنُهُمۡ كَٱلَّذِي يُغۡشَىٰ عَلَيۡهِ مِنَ ٱلۡمَوۡتِۖ فَإِذَا ذَهَبَ ٱلۡخَوۡفُ سَلَقُوكُم بِأَلۡسِنَةٍ حِدَادٍ أَشِحَّةً عَلَى ٱلۡخَيۡرِۚ أُوْلَٰٓئِكَ لَمۡ يُؤۡمِنُواْ فَأَحۡبَطَ ٱللَّهُ أَعۡمَٰلَهُمۡۚ وَكَانَ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرٗا

19. (አማኞች ሆይ!) በእናንተ ላይ እርዳታን የነፈጉ ሆነው እንጂ የማይመጡትን፤ ሽብሩም በመጣ ጊዜ እንደዚያ ከሞት መከራ በእርሱ ላይ የሚሸፍን አደጋ እንደ ወደቀበት ዓይኖቻቸው ወዲያና ወዲህ የምትንከራተት ሆና ወደ አንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ:: ሽብሩም በሄደ ጊዜ በገንዘብ ላይ የሚሳሱ ሆነው በተቡ ምላሶች ይነድፏችኋል:: እነዚያ አላመኑም:: ስለዚህ አላህ ስራዎቻቸውን አበላሸ:: ይህም በአላህ ላይ ገር ነው። info
التفاسير:

external-link copy
20 : 33

يَحۡسَبُونَ ٱلۡأَحۡزَابَ لَمۡ يَذۡهَبُواْۖ وَإِن يَأۡتِ ٱلۡأَحۡزَابُ يَوَدُّواْ لَوۡ أَنَّهُم بَادُونَ فِي ٱلۡأَعۡرَابِ يَسۡـَٔلُونَ عَنۡ أَنۢبَآئِكُمۡۖ وَلَوۡ كَانُواْ فِيكُم مَّا قَٰتَلُوٓاْ إِلَّا قَلِيلٗا

20. (መናፍቆች) አህዛብን አልሄዱም ብለው ያስባሉ አህዛቦችም ቢመጡ እነርሱ በዘላኖች ውስጥ በገጠር የራቁ ሊሆኑ ይመኛሉ:: (ከዚያም) ከወሬዎቻችሁ ይጠይቃሉ:: በእናንተ ውስጥ በነበሩም ኖሮ ጥቂትን እንጂ አይዋጉም ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 33

لَّقَدۡ كَانَ لَكُمۡ فِي رَسُولِ ٱللَّهِ أُسۡوَةٌ حَسَنَةٞ لِّمَن كَانَ يَرۡجُواْ ٱللَّهَ وَٱلۡيَوۡمَ ٱلۡأٓخِرَ وَذَكَرَ ٱللَّهَ كَثِيرٗا

21. (አማኞች ሆይ!) ከናንተ መካከል አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነና አላህንም በብዙ ለሚያወሳ ሰው ሁሉ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
22 : 33

وَلَمَّا رَءَا ٱلۡمُؤۡمِنُونَ ٱلۡأَحۡزَابَ قَالُواْ هَٰذَا مَا وَعَدَنَا ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥ وَصَدَقَ ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥۚ وَمَا زَادَهُمۡ إِلَّآ إِيمَٰنٗا وَتَسۡلِيمٗا

22. አማኞችም አህዛብን ባዩ ጊዜ «ይህ አላህና መልዕክተኛው የቀጠሩን ነው:: አላህና መልዕክተኛዉም እውነትን ተናገሩ።» አሉ:: ይህ እምነትንና መታዘዝንም እንጂ ሌላን አልጨመረላቸዉም:: info
التفاسير: