ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿ

ಪುಟ ಸಂಖ್ಯೆ:close

external-link copy
102 : 4

وَإِذَا كُنتَ فِيهِمۡ فَأَقَمۡتَ لَهُمُ ٱلصَّلَوٰةَ فَلۡتَقُمۡ طَآئِفَةٞ مِّنۡهُم مَّعَكَ وَلۡيَأۡخُذُوٓاْ أَسۡلِحَتَهُمۡۖ فَإِذَا سَجَدُواْ فَلۡيَكُونُواْ مِن وَرَآئِكُمۡ وَلۡتَأۡتِ طَآئِفَةٌ أُخۡرَىٰ لَمۡ يُصَلُّواْ فَلۡيُصَلُّواْ مَعَكَ وَلۡيَأۡخُذُواْ حِذۡرَهُمۡ وَأَسۡلِحَتَهُمۡۗ وَدَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَوۡ تَغۡفُلُونَ عَنۡ أَسۡلِحَتِكُمۡ وَأَمۡتِعَتِكُمۡ فَيَمِيلُونَ عَلَيۡكُم مَّيۡلَةٗ وَٰحِدَةٗۚ وَلَا جُنَاحَ عَلَيۡكُمۡ إِن كَانَ بِكُمۡ أَذٗى مِّن مَّطَرٍ أَوۡ كُنتُم مَّرۡضَىٰٓ أَن تَضَعُوٓاْ أَسۡلِحَتَكُمۡۖ وَخُذُواْ حِذۡرَكُمۡۗ إِنَّ ٱللَّهَ أَعَدَّ لِلۡكَٰفِرِينَ عَذَابٗا مُّهِينٗا

102.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ) በጦርነት ላይ በመካከላቸው በሆንክና ሶላትን ለእነርሱ ባሰገድካቸው ጊዜ ከእነርሱ አንዱ ቡድን ካንተ ጋር ይቁም:: መሳሪያዎቻቸውንም ይያዙ:: ሱጁድ ባደረጉ ጊዜ ከበስተኋላችሁ ይሁኑ:: ከዚያም እነዚያ ቡድኖች ወደ ግንባር ይሂዱና ያልሰገዱት ሌሎች ቡድኖች ይምጡ :: ከዚያም ካንተ ጋር ይስገዱ:: ጥንቃቄያቸውንና መሳሪያዎቻቸውንም ይያዙ:: እነዚያ በአላህ የካዱት ከትጥቅና ስንቃችሁ ብትዘናጉና በአንድ ጊዜ ቢወሯችሁ ይመኛሉ:: ዝናብ አውኳችሁ ወይም በሽተኛ ሆናችሁ ትጥቃችሁን ብታስቀምጡ በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም:: ጥንቃቄ አድርጉ:: አላህ ለካሐዲያን ሁሉ አዋራጅን ቅጣት አዘጋጀ:: info
التفاسير:

external-link copy
103 : 4

فَإِذَا قَضَيۡتُمُ ٱلصَّلَوٰةَ فَٱذۡكُرُواْ ٱللَّهَ قِيَٰمٗا وَقُعُودٗا وَعَلَىٰ جُنُوبِكُمۡۚ فَإِذَا ٱطۡمَأۡنَنتُمۡ فَأَقِيمُواْ ٱلصَّلَوٰةَۚ إِنَّ ٱلصَّلَوٰةَ كَانَتۡ عَلَى ٱلۡمُؤۡمِنِينَ كِتَٰبٗا مَّوۡقُوتٗا

103. ሶላትንም በፈጸማችሁ (በጨረሳችሁ) ጊዜ ቆማችሁ፣ ተቀምጣችሁና በጎኖቻችሁም ተጋድማችሁ አላህን አውሱ:: በተረጋጋችሁ ጊዜ ግን ሶላትን ደንቧን አሟልታችሁ ስገዱ:: ሶላት በአማኞች ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና:: info
التفاسير:

external-link copy
104 : 4

وَلَا تَهِنُواْ فِي ٱبۡتِغَآءِ ٱلۡقَوۡمِۖ إِن تَكُونُواْ تَأۡلَمُونَ فَإِنَّهُمۡ يَأۡلَمُونَ كَمَا تَأۡلَمُونَۖ وَتَرۡجُونَ مِنَ ٱللَّهِ مَا لَا يَرۡجُونَۗ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا

104.ሰዎቹንም ከመፈለግ አትስነፉ:: ስትቆስሉ የምትታመሙ ብትሆኑም እናንተ እንደምትታመሙ ሁሉ እነርሱም ይታመማሉ:: እናንተ ግን እነርሱ የማይከጅሉትን ከአላህ ትከጅላላችሁ:: አላህም ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
105 : 4

إِنَّآ أَنزَلۡنَآ إِلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ بِٱلۡحَقِّ لِتَحۡكُمَ بَيۡنَ ٱلنَّاسِ بِمَآ أَرَىٰكَ ٱللَّهُۚ وَلَا تَكُن لِّلۡخَآئِنِينَ خَصِيمٗا

105. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በሰዎች መካከል አላህ ባሳወቀህ ልትፈርድ ወደ አንተ መጽሐፉን በእውነት አወረድን:: እናም ለከዳተኞች ተከራካሪ አትሁን:: info
التفاسير: