ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿ

ಪುಟ ಸಂಖ್ಯೆ:close

external-link copy
60 : 4

أَلَمۡ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ يَزۡعُمُونَ أَنَّهُمۡ ءَامَنُواْ بِمَآ أُنزِلَ إِلَيۡكَ وَمَآ أُنزِلَ مِن قَبۡلِكَ يُرِيدُونَ أَن يَتَحَاكَمُوٓاْ إِلَى ٱلطَّٰغُوتِ وَقَدۡ أُمِرُوٓاْ أَن يَكۡفُرُواْ بِهِۦۖ وَيُرِيدُ ٱلشَّيۡطَٰنُ أَن يُضِلَّهُمۡ ضَلَٰلَۢا بَعِيدٗا

60. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ «ባንተ ላይ በተወረደውና ካንተ በፊትም በተወረደው አምነናል።» ወደ ሚሉት አላየህምን? በእርሱ እንዲክዱ በእርግጥ የታዘዙ ሲሆኑ ወደ ጣኦት መፋረድን ይፈልጋሉ:: ሰይጣንም ከእውነት የራቀን መሳሳት ሊያሳስታቸው ይፈልጋል። info
التفاسير:

external-link copy
61 : 4

وَإِذَا قِيلَ لَهُمۡ تَعَالَوۡاْ إِلَىٰ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ وَإِلَى ٱلرَّسُولِ رَأَيۡتَ ٱلۡمُنَٰفِقِينَ يَصُدُّونَ عَنكَ صُدُودٗا

61. ለእነርሱም፡- «አላህ ወደ አወረደው ቁርኣንና ወደ መልዕክተኛው ኑ።» በተባሉ ጊዜ አስመሳዮችን ካንተ በሀይል ሲሸሹ ታያቸዋለህ። info
التفاسير:

external-link copy
62 : 4

فَكَيۡفَ إِذَآ أَصَٰبَتۡهُم مُّصِيبَةُۢ بِمَا قَدَّمَتۡ أَيۡدِيهِمۡ ثُمَّ جَآءُوكَ يَحۡلِفُونَ بِٱللَّهِ إِنۡ أَرَدۡنَآ إِلَّآ إِحۡسَٰنٗا وَتَوۡفِيقًا

62. እጆቻቸዉም ባስቀደሙት ጥፋት ምክንያት መከራ በደረሰባቸውና ከዚያ «ደግን ሀሳብና ማስማማትን እንጂ ሌላን አልፈለግንም።» በማለት በአላህ የሚምሉ ሆነው ወደ አንተ በመጡ ጊዜ እንዴት ይሆናል? info
التفاسير:

external-link copy
63 : 4

أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ يَعۡلَمُ ٱللَّهُ مَا فِي قُلُوبِهِمۡ فَأَعۡرِضۡ عَنۡهُمۡ وَعِظۡهُمۡ وَقُل لَّهُمۡ فِيٓ أَنفُسِهِمۡ قَوۡلَۢا بَلِيغٗا

63. እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅባቸው ናቸው:: ከእነርሱ ራስህን አግልል:: ገስፃቸዉም:: ለእነርሱም በነፍሶቻቸው ውስጥ ጠልቆ የሚገባ ጠንካራ ቃል ተናገራቸው። info
التفاسير:

external-link copy
64 : 4

وَمَآ أَرۡسَلۡنَا مِن رَّسُولٍ إِلَّا لِيُطَاعَ بِإِذۡنِ ٱللَّهِۚ وَلَوۡ أَنَّهُمۡ إِذ ظَّلَمُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ جَآءُوكَ فَٱسۡتَغۡفَرُواْ ٱللَّهَ وَٱسۡتَغۡفَرَ لَهُمُ ٱلرَّسُولُ لَوَجَدُواْ ٱللَّهَ تَوَّابٗا رَّحِيمٗا

64. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ማንንም መልዕክተኛ በአላህ ፈቃድ ሊታዘዙት እንጂ አልላክንም:: እነርሱም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ ወደ አንተ መጥተው አላህን ምህረት በለመኑና መልዕክተኛዉም ለእነርሱ ምህረትን በለመነላቸው ኖሮ አላህን ጸጸትን ተቀባይና አዛኝ ሆኖ ባገኙት ነበር። info
التفاسير:

external-link copy
65 : 4

فَلَا وَرَبِّكَ لَا يُؤۡمِنُونَ حَتَّىٰ يُحَكِّمُوكَ فِيمَا شَجَرَ بَيۡنَهُمۡ ثُمَّ لَا يَجِدُواْ فِيٓ أَنفُسِهِمۡ حَرَجٗا مِّمَّا قَضَيۡتَ وَيُسَلِّمُواْ تَسۡلِيمٗا

65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጉዳዩ እነርሱ እንዳሉት አይደለም:: በጌታህ እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ የሚያስፈርዱህ ሆነው ከዚያ ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከማያገኙና ፍጹም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ ድረስ አማኝ አይሆኑም:: info
التفاسير: