ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
36 : 28

فَلَمَّا جَآءَهُم مُّوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَا بَيِّنَٰتٖ قَالُواْ مَا هَٰذَآ إِلَّا سِحۡرٞ مُّفۡتَرٗى وَمَا سَمِعۡنَا بِهَٰذَا فِيٓ ءَابَآئِنَا ٱلۡأَوَّلِينَ

36. ሙሳም ተዓምራቶቻችንም ግልጽ ሆነው በመጣባቸው ጊዜ “ይህ የተቀጠፈ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም:: ይህንንም በመጀመሪያዎች አባቶቻችን ውስጥ አልሰማንም” አሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
37 : 28

وَقَالَ مُوسَىٰ رَبِّيٓ أَعۡلَمُ بِمَن جَآءَ بِٱلۡهُدَىٰ مِنۡ عِندِهِۦ وَمَن تَكُونُ لَهُۥ عَٰقِبَةُ ٱلدَّارِۚ إِنَّهُۥ لَا يُفۡلِحُ ٱلظَّٰلِمُونَ

37. ሙሳም “ጌታዬ ከእርሱ ዘንድ በቀጥታው መንገድ የመጣውን ምስጉኒትም አገር ለእርሱ የምትሆንለትን ሰው አዋቂ ነው:: እነሆ በደለኞች አይድኑም” አለ። info
التفاسير:

external-link copy
38 : 28

وَقَالَ فِرۡعَوۡنُ يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡمَلَأُ مَا عَلِمۡتُ لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرِي فَأَوۡقِدۡ لِي يَٰهَٰمَٰنُ عَلَى ٱلطِّينِ فَٱجۡعَل لِّي صَرۡحٗا لَّعَلِّيٓ أَطَّلِعُ إِلَىٰٓ إِلَٰهِ مُوسَىٰ وَإِنِّي لَأَظُنُّهُۥ مِنَ ٱلۡكَٰذِبِينَ

38. ፈርዖንም “እናንተ ቡድኖች ሆይ! ከእኔ ሌላ ለእናንተ አምላክን ምንም አላውቅም:: ሃማን ሆይ! ጭቃ ለእኔ አቃጥልልኝ:: ጡብ ስራልኝ:: ለእኔም ከፍተኛ ህንጻን ስራልኝ:: ወደ ሙሳ አምላክ ልወጣ እከጅላለሁና:: እኔም ከውሸታሞች መሆኑን እጠረጥረዋለሁ” አለ። info
التفاسير:

external-link copy
39 : 28

وَٱسۡتَكۡبَرَ هُوَ وَجُنُودُهُۥ فِي ٱلۡأَرۡضِ بِغَيۡرِ ٱلۡحَقِّ وَظَنُّوٓاْ أَنَّهُمۡ إِلَيۡنَا لَا يُرۡجَعُونَ

39. እርሱም ሰራዊቶቹም በምድር ላይ ያለ አግባብ ኮሩ:: እነርሱም ወደእኛ የማይመለሱ መሆናቸውን ጠረጠሩ:: info
التفاسير:

external-link copy
40 : 28

فَأَخَذۡنَٰهُ وَجُنُودَهُۥ فَنَبَذۡنَٰهُمۡ فِي ٱلۡيَمِّۖ فَٱنظُرۡ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلظَّٰلِمِينَ

40. እርሱንም ሰራዊቱንም በጥብቅ ያዝናቸው:: በባህርም ውስጥ ጣልናቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የበደለኞች መጨረሻም እንዴት እንደነበረ ተመልከት:: info
التفاسير:

external-link copy
41 : 28

وَجَعَلۡنَٰهُمۡ أَئِمَّةٗ يَدۡعُونَ إِلَى ٱلنَّارِۖ وَيَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ لَا يُنصَرُونَ

41. ወደ እሳት የሚጠሩ መሪዎችም አደረግናቸው:: በትንሳኤም ቀን አይረዱም:: info
التفاسير:

external-link copy
42 : 28

وَأَتۡبَعۡنَٰهُمۡ فِي هَٰذِهِ ٱلدُّنۡيَا لَعۡنَةٗۖ وَيَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ هُم مِّنَ ٱلۡمَقۡبُوحِينَ

42. በዚችም በቅርቢቱ ዓለም ውስጥ እርግማንን አስከተልናቸው:: በትንሳኤም ቀን እነርሱ ከሚባረሩት ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
43 : 28

وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ مِنۢ بَعۡدِ مَآ أَهۡلَكۡنَا ٱلۡقُرُونَ ٱلۡأُولَىٰ بَصَآئِرَ لِلنَّاسِ وَهُدٗى وَرَحۡمَةٗ لَّعَلَّهُمۡ يَتَذَكَّرُونَ

43. የፊተኞቹን የክፍለ ዘመናት ህዝቦችንም ከአጠፋን በኋላ ለሰዎች የልብ ብርሃን መሪም እዝነትም ሲሆን ይገሠጹ ዘንድ ለሙሳ መጽሐፉን በእርግጥ ሰጠነው:: info
التفاسير: