ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
85 : 28

إِنَّ ٱلَّذِي فَرَضَ عَلَيۡكَ ٱلۡقُرۡءَانَ لَرَآدُّكَ إِلَىٰ مَعَادٖۚ قُل رَّبِّيٓ أَعۡلَمُ مَن جَآءَ بِٱلۡهُدَىٰ وَمَنۡ هُوَ فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ

85. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያ ቁርኣንን የተከፋፈለ ሆኖ ባንተ ላይ ያወረደውና ህግጋቱን እንድትትገበር ግድ ያደረግብህ አምላክ ወደ መመለሻ (ወደ መካ) በእርግጥ መላሽህ ነው። «ጌታዬ በቅን መንገድ የመጣውንና እርሱም በግልጽ ስህተት ውስጥ የሆነውን አዋቂ ነው» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
86 : 28

وَمَا كُنتَ تَرۡجُوٓاْ أَن يُلۡقَىٰٓ إِلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبُ إِلَّا رَحۡمَةٗ مِّن رَّبِّكَۖ فَلَا تَكُونَنَّ ظَهِيرٗا لِّلۡكَٰفِرِينَ

86.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መጽሐፉ ወደ አንተ መወረዱን ተስፋ የምታደርግ አልነበርክም :: ግን ከጌታህ ችሮታ ተወረደልህ:: ለከሓዲያን በፍጹም ረዳት አትሁን:: info
التفاسير:

external-link copy
87 : 28

وَلَا يَصُدُّنَّكَ عَنۡ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ بَعۡدَ إِذۡ أُنزِلَتۡ إِلَيۡكَۖ وَٱدۡعُ إِلَىٰ رَبِّكَۖ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ

87.(መልዕክተኛችንሙሐመድ ሆይ!) ከአላህም አናቅጽ ወደ አንተ ከተወረዱ በኋላ አያግዱህ:: ወደ ጌታህም ሰዎችን ጥራ:: ከአጋሪዎችም አትሁን:: info
التفاسير:

external-link copy
88 : 28

وَلَا تَدۡعُ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَۘ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۚ كُلُّ شَيۡءٍ هَالِكٌ إِلَّا وَجۡهَهُۥۚ لَهُ ٱلۡحُكۡمُ وَإِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ

88. ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትገዛ:: ከእርሱም በቀር አምላክ የለም። ከእርሱ በስተቀር ሁሉም ጠፊ ነው:: ፍርዱ የእርሱ ብቻ ነው:: ሁላችሁም ወደ እርሱ ትመለሳላችሁ:: info
التفاسير: