ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
71 : 28

قُلۡ أَرَءَيۡتُمۡ إِن جَعَلَ ٱللَّهُ عَلَيۡكُمُ ٱلَّيۡلَ سَرۡمَدًا إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ مَنۡ إِلَٰهٌ غَيۡرُ ٱللَّهِ يَأۡتِيكُم بِضِيَآءٍۚ أَفَلَا تَسۡمَعُونَ

71. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አያችሁን? (እስቲ ንገሩኝ) አላህ በእናንተ ላይ ሌሊትን እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ዘውታሪ ቢያደርገው ከአላህ ሌላ ብርሃንን የሚያመጣላችሁ አምላክ ማነው? አትሰሙምን?» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
72 : 28

قُلۡ أَرَءَيۡتُمۡ إِن جَعَلَ ٱللَّهُ عَلَيۡكُمُ ٱلنَّهَارَ سَرۡمَدًا إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ مَنۡ إِلَٰهٌ غَيۡرُ ٱللَّهِ يَأۡتِيكُم بِلَيۡلٖ تَسۡكُنُونَ فِيهِۚ أَفَلَا تُبۡصِرُونَ

72. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አያችሁን? አላህ በእናንተ ላይ ቀንን እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ዘውታሪ ቢያደርገው ከአላህ ሌላ በውስጡ የምታርፉበትን ሌሊት የሚያመጣላችሁ አምላክ ማን ነው? አታስተውሉምን?» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
73 : 28

وَمِن رَّحۡمَتِهِۦ جَعَلَ لَكُمُ ٱلَّيۡلَ وَٱلنَّهَارَ لِتَسۡكُنُواْ فِيهِ وَلِتَبۡتَغُواْ مِن فَضۡلِهِۦ وَلَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ

73. ከችሮታዉም ለእናንተ ሌሊትንና ቀንን በውስጡ ልታርፉበት ከትሩፋቱም ልትፈልጉበት አመስጋኞችም ልትሆኑ አደረገላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
74 : 28

وَيَوۡمَ يُنَادِيهِمۡ فَيَقُولُ أَيۡنَ شُرَكَآءِيَ ٱلَّذِينَ كُنتُمۡ تَزۡعُمُونَ

74. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሚጠራባቸውንም ቀንና «እነዚያ ተጋሪዎቼ ትሉዋቸው የነበራችሁት የት ናቸው?» የሚልበትን ቀን አስታውስ:: info
التفاسير:

external-link copy
75 : 28

وَنَزَعۡنَا مِن كُلِّ أُمَّةٖ شَهِيدٗا فَقُلۡنَا هَاتُواْ بُرۡهَٰنَكُمۡ فَعَلِمُوٓاْ أَنَّ ٱلۡحَقَّ لِلَّهِ وَضَلَّ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَفۡتَرُونَ

75. ከህዝቦችም ሁሉ መስካሪን እናወጣና «ማስረጃችሁን አምጡ» እንላለን። ያን ጊዜ እውነተኛዉም አምላክነት ለአላህ ብቻ መሆኑን ያውቃሉ:: ይቀጣጥፉት የነበሩትም ከእነርሱ ይጠፋባቸዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
76 : 28

۞ إِنَّ قَٰرُونَ كَانَ مِن قَوۡمِ مُوسَىٰ فَبَغَىٰ عَلَيۡهِمۡۖ وَءَاتَيۡنَٰهُ مِنَ ٱلۡكُنُوزِ مَآ إِنَّ مَفَاتِحَهُۥ لَتَنُوٓأُ بِٱلۡعُصۡبَةِ أُوْلِي ٱلۡقُوَّةِ إِذۡ قَالَ لَهُۥ قَوۡمُهُۥ لَا تَفۡرَحۡۖ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ ٱلۡفَرِحِينَ

76. ቃሩን ከሙሳ ነገዶች አንዱ ነበር:: በእነርሱም ላይ አመጸ:: ከድልቦችም ያንን መክፈቻዎቹ ብቻ የኃይል ባለቤቶች የሆኑ ቡድኖችን ሸክሙ የሚከብድን ሰጠነው:: ወገኖቹ ለእርሱ ባሉትም ጊዜ አስታውስ: «አትኩራ አላህ ኩራተኞችን አይወድምና። info
التفاسير:

external-link copy
77 : 28

وَٱبۡتَغِ فِيمَآ ءَاتَىٰكَ ٱللَّهُ ٱلدَّارَ ٱلۡأٓخِرَةَۖ وَلَا تَنسَ نَصِيبَكَ مِنَ ٱلدُّنۡيَاۖ وَأَحۡسِن كَمَآ أَحۡسَنَ ٱللَّهُ إِلَيۡكَۖ وَلَا تَبۡغِ ٱلۡفَسَادَ فِي ٱلۡأَرۡضِۖ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ ٱلۡمُفۡسِدِينَ

77. «አላህም በሰጠህ ሀብት የመጨረሻይቱን አገር ፈልግ:: ሆኖም ከቅርቢቱ አለምም ፈንታህን አትርሳ:: አላህ ወደ አንተ መልካምን እንዳደረገልህ መልካምን አድርግ:: በምድርም ውስጥ ማጥፋትን አትፈልግ:: አላህ አጥፊዎችን አይወድምና።» አሉት። info
التفاسير: