ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
52 : 19

وَنَٰدَيۡنَٰهُ مِن جَانِبِ ٱلطُّورِ ٱلۡأَيۡمَنِ وَقَرَّبۡنَٰهُ نَجِيّٗا

52. ከጡር ጋራ በስተቀኝ ጎን በኩልም ጠራነው። በሚስጥር ያነጋገርነውም ስንሆን አቀረብነው። info
التفاسير:

external-link copy
53 : 19

وَوَهَبۡنَا لَهُۥ مِن رَّحۡمَتِنَآ أَخَاهُ هَٰرُونَ نَبِيّٗا

53. ከእዝነታችንም (ከችሮታችንም) ወንድሙን ሃሩንን ነብይ አደረግንለት። info
التفاسير:

external-link copy
54 : 19

وَٱذۡكُرۡ فِي ٱلۡكِتَٰبِ إِسۡمَٰعِيلَۚ إِنَّهُۥ كَانَ صَادِقَ ٱلۡوَعۡدِ وَكَانَ رَسُولٗا نَّبِيّٗا

54. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመጽሐፉ ውስጥ ኢስማዒልንም አውሳ:: እርሱ ቀጠሮን አክባሪ ነበርና። መልዕክተኛ ነብይም ነበር። info
التفاسير:

external-link copy
55 : 19

وَكَانَ يَأۡمُرُ أَهۡلَهُۥ بِٱلصَّلَوٰةِ وَٱلزَّكَوٰةِ وَكَانَ عِندَ رَبِّهِۦ مَرۡضِيّٗا

55. ቤተሰቦቹንም በሶላትና በዘካ ያዝ ነበር:: በጌታዉም ዘንድ ተወዳጅ ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
56 : 19

وَٱذۡكُرۡ فِي ٱلۡكِتَٰبِ إِدۡرِيسَۚ إِنَّهُۥ كَانَ صِدِّيقٗا نَّبِيّٗا

56. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመጽሐፉ ውስጥ ኢድሪስንም አውሳ:: እርሱ እውነተኛ ነብይ ነበርና:: info
التفاسير:

external-link copy
57 : 19

وَرَفَعۡنَٰهُ مَكَانًا عَلِيًّا

57. (ኢድሪስን) ወደ ከፍተኛም ስፍራ አነሳነው:: info
التفاسير:

external-link copy
58 : 19

أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ أَنۡعَمَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِم مِّنَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ مِن ذُرِّيَّةِ ءَادَمَ وَمِمَّنۡ حَمَلۡنَا مَعَ نُوحٖ وَمِن ذُرِّيَّةِ إِبۡرَٰهِيمَ وَإِسۡرَٰٓءِيلَ وَمِمَّنۡ هَدَيۡنَا وَٱجۡتَبَيۡنَآۚ إِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتُ ٱلرَّحۡمَٰنِ خَرُّواْۤ سُجَّدٗاۤ وَبُكِيّٗا۩

58. እነዚህ (አሥሩ) እነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ ችሮታውን የለገሰላቸው ከነብያት ከአዳም ዘር ከኑሕ ጋር በመርከቢቱ ላይ ከጫንናቸዉም ዘሮች ከኢብራሂምና ከኢስራኢልም ዘሮች ከመራናቸውና ከመረጥናቸዉም የሆኑት የአር-ረህማን አናቅጽ በእነርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ ሰጋጆችና አልቃሾች ሆነው ወደ መሬት የሚወድቁ (የሚደፉ) ናቸው። {1} info

{1} እዚህ ሱጁዱ ትላዋ ይደረጋል።

التفاسير:

external-link copy
59 : 19

۞ فَخَلَفَ مِنۢ بَعۡدِهِمۡ خَلۡفٌ أَضَاعُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَٱتَّبَعُواْ ٱلشَّهَوَٰتِۖ فَسَوۡفَ يَلۡقَوۡنَ غَيًّا

59. ከእነርሱም በኋላ ሶላትን ያጎደሉ ከንቱ ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ትውልዶች ተተኩ:: «ገይ» የሚባልን የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
60 : 19

إِلَّا مَن تَابَ وَءَامَنَ وَعَمِلَ صَٰلِحٗا فَأُوْلَٰٓئِكَ يَدۡخُلُونَ ٱلۡجَنَّةَ وَلَا يُظۡلَمُونَ شَيۡـٔٗا

60. ግና ከእነርሱ የተጸጸቱ በአላህ ያመኑ በጎንም ስራ የሰሩ ሰዎች ወደ ገነት ይገባሉ:: አንዳችንም አይበደሉም:: info
التفاسير:

external-link copy
61 : 19

جَنَّٰتِ عَدۡنٍ ٱلَّتِي وَعَدَ ٱلرَّحۡمَٰنُ عِبَادَهُۥ بِٱلۡغَيۡبِۚ إِنَّهُۥ كَانَ وَعۡدُهُۥ مَأۡتِيّٗا

61. የመኖሪያን ገነቶች ያችን አር-ረህማን ለባሮቹ በሩቅ ሆነው ሳሉ ተስፋ ቃል የገባላቸውን ይገባሉ:: እርሱ ተስፋው ሁልጊዜም ተፈጻሚ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
62 : 19

لَّا يَسۡمَعُونَ فِيهَا لَغۡوًا إِلَّا سَلَٰمٗاۖ وَلَهُمۡ رِزۡقُهُمۡ فِيهَا بُكۡرَةٗ وَعَشِيّٗا

62. በእርሷ ሰላምን እንጂ ውድቅን ነገር አይሰሙም:: ለእነርሱም በእርሷ ውስጥ ጧትም ማታም ሲሳያቸው አላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
63 : 19

تِلۡكَ ٱلۡجَنَّةُ ٱلَّتِي نُورِثُ مِنۡ عِبَادِنَا مَن كَانَ تَقِيّٗا

63. ይህ ያቺ ከባሮቻችን ጥንቁቆች ለሆኑት ሁሉ የምናወርሳት ገነት ናት:: info
التفاسير:

external-link copy
64 : 19

وَمَا نَتَنَزَّلُ إِلَّا بِأَمۡرِ رَبِّكَۖ لَهُۥ مَا بَيۡنَ أَيۡدِينَا وَمَا خَلۡفَنَا وَمَا بَيۡنَ ذَٰلِكَۚ وَمَا كَانَ رَبُّكَ نَسِيّٗا

64. (ጂብሪልም ለነቢዩ) «በጌታህ ትእዛዝ እንጂ አንወርድም:: በፊታችን፤ በኋላችንና በዚህም መካከል ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: ጌታህም ረሺ አይደለም።» አለ። info
التفاسير: