ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
26 : 19

فَكُلِي وَٱشۡرَبِي وَقَرِّي عَيۡنٗاۖ فَإِمَّا تَرَيِنَّ مِنَ ٱلۡبَشَرِ أَحَدٗا فَقُولِيٓ إِنِّي نَذَرۡتُ لِلرَّحۡمَٰنِ صَوۡمٗا فَلَنۡ أُكَلِّمَ ٱلۡيَوۡمَ إِنسِيّٗا

26. «ብይ፤ ጠጭም። ተደሰችም ከሰዎች አንድንም ብታይ እኔ ለአዛኙ አምላክ ዝምታን ተስያለሁ:: እናም ዛሬ ማንንም ሰው በፍጹም አላነጋግርም በይ።» አላት። info
التفاسير:

external-link copy
27 : 19

فَأَتَتۡ بِهِۦ قَوۡمَهَا تَحۡمِلُهُۥۖ قَالُواْ يَٰمَرۡيَمُ لَقَدۡ جِئۡتِ شَيۡـٔٗا فَرِيّٗا

27. እርሱን ተሸክማው ወደ ዘመዶቿ መጣች (እንዲህም) አሏት: «መርየም ሆይ! ከባድ ነገርን በእርግጥ ፈጸምሽ። info
التفاسير:

external-link copy
28 : 19

يَٰٓأُخۡتَ هَٰرُونَ مَا كَانَ أَبُوكِ ٱمۡرَأَ سَوۡءٖ وَمَا كَانَتۡ أُمُّكِ بَغِيّٗا

28. «አንቺ የሃሩን እህት ሆይ! አባትሽ መጥፎ ሰው አልነበረም:: እናትሽም አመንዝራ ዝሙተኛ አልነበረችም።» አሏት። info
التفاسير:

external-link copy
29 : 19

فَأَشَارَتۡ إِلَيۡهِۖ قَالُواْ كَيۡفَ نُكَلِّمُ مَن كَانَ فِي ٱلۡمَهۡدِ صَبِيّٗا

29. እርሷም ወደ ህፃኑ አመለከተች:: እነርሱም «በአንቀልባ ያለን ህፃን እንዴት እናናግራለን?» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
30 : 19

قَالَ إِنِّي عَبۡدُ ٱللَّهِ ءَاتَىٰنِيَ ٱلۡكِتَٰبَ وَجَعَلَنِي نَبِيّٗا

30. ህፃኑም አለ: «እኔ የአላህ አገልጋይ ነኝ፤ መጽሐፍን ሰጥቶኛል። ነብይም አድርጎኛል። info
التفاسير:

external-link copy
31 : 19

وَجَعَلَنِي مُبَارَكًا أَيۡنَ مَا كُنتُ وَأَوۡصَٰنِي بِٱلصَّلَوٰةِ وَٱلزَّكَوٰةِ مَا دُمۡتُ حَيّٗا

31. «በየትም ስፍራ ብሆን የተባረኩኝ አድርጎኛል። በህይወትም እስካለሁ ሶላትንና ዘካን አዞኛል። info
التفاسير:

external-link copy
32 : 19

وَبَرَّۢا بِوَٰلِدَتِي وَلَمۡ يَجۡعَلۡنِي جَبَّارٗا شَقِيّٗا

32. «ለእናቴም ታዛዥ አድርጎኛል:: ትዕቢተኛ እድለቢስ አላደረገኝም። info
التفاسير:

external-link copy
33 : 19

وَٱلسَّلَٰمُ عَلَيَّ يَوۡمَ وُلِدتُّ وَيَوۡمَ أَمُوتُ وَيَوۡمَ أُبۡعَثُ حَيّٗا

33. «በተወለድሁበት ቀን በምሞትበት ቀንና ሕያው ሆኜ በምቀሰቀስበትም ቀን ሰላም በእኔ ላይ ይስፈን።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
34 : 19

ذَٰلِكَ عِيسَى ٱبۡنُ مَرۡيَمَۖ قَوۡلَ ٱلۡحَقِّ ٱلَّذِي فِيهِ يَمۡتَرُونَ

34. የመርየም ልጅ ዒሳ ይሀው ነው፤ ያ በእርሱ የሚጠራጠሩበት እውነተኛ ቃል ይህ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
35 : 19

مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٖۖ سُبۡحَٰنَهُۥٓۚ إِذَا قَضَىٰٓ أَمۡرٗا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ

35. ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባዉም:: ከጉድለት ሁሉ ጠራ:: አንድን ነገር በወሰነ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ሁን» ብቻ ነው:: ወዲያዉም ይሆናል። info
التفاسير:

external-link copy
36 : 19

وَإِنَّ ٱللَّهَ رَبِّي وَرَبُّكُمۡ فَٱعۡبُدُوهُۚ هَٰذَا صِرَٰطٞ مُّسۡتَقِيمٞ

36. ዒሳ ለህዝቦቹ «አላህ የእኔም ጌታዬ የእናንተም ጌታችሁ ነውና ተገዙት:: ይህ ቀጥተኛው መንገድ ነው።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
37 : 19

فَٱخۡتَلَفَ ٱلۡأَحۡزَابُ مِنۢ بَيۡنِهِمۡۖ فَوَيۡلٞ لِّلَّذِينَ كَفَرُواْ مِن مَّشۡهَدِ يَوۡمٍ عَظِيمٍ

37. ከመካከላቸዉም አንጃዎች በእርሱ ነገር ላይ ተለያዩ:: ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ከታላቁ ቀን መጋፈጥ ክስተት ወዮላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
38 : 19

أَسۡمِعۡ بِهِمۡ وَأَبۡصِرۡ يَوۡمَ يَأۡتُونَنَا لَٰكِنِ ٱلظَّٰلِمُونَ ٱلۡيَوۡمَ فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ

38. ወደ እኛ በሚመጡ ቀን ምን ያህል ሰሚ ምን ያህል ተመልካች አደረጋቸው:: ግን አመጸኞች በዳዮች ዛሬ በዚህች ዓለም በግልጽ ስህተትና ጥመት ውስጥ ናቸው:: info
التفاسير: