ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
12 : 19

يَٰيَحۡيَىٰ خُذِ ٱلۡكِتَٰبَ بِقُوَّةٖۖ وَءَاتَيۡنَٰهُ ٱلۡحُكۡمَ صَبِيّٗا

12. «የሕያ ሆይ! መጽሐፉን በጥብቅ ያዝ።» አልነው:: ጥበብንም በሕጻንነቱ ሰጠነው። info
التفاسير:

external-link copy
13 : 19

وَحَنَانٗا مِّن لَّدُنَّا وَزَكَوٰةٗۖ وَكَانَ تَقِيّٗا

13. ከእኛም የሆነን ርህራሄና ንጽህናንም (ሰጠነው):: ጥንቁቅም ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
14 : 19

وَبَرَّۢا بِوَٰلِدَيۡهِ وَلَمۡ يَكُن جَبَّارًا عَصِيّٗا

14. ለወላጆቹም በጎ ሠሪ ነበር:: ትዕቢተኛና አመጸኛም አልነበረም:: info
التفاسير:

external-link copy
15 : 19

وَسَلَٰمٌ عَلَيۡهِ يَوۡمَ وُلِدَ وَيَوۡمَ يَمُوتُ وَيَوۡمَ يُبۡعَثُ حَيّٗا

15. በተወለደበት ቀንና በሚሞትበት ቀን ህያው ሆኖ በሚነሳበትም ቀን ሰላም በእሱ ላይ ይሁን :: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 19

وَٱذۡكُرۡ فِي ٱلۡكِتَٰبِ مَرۡيَمَ إِذِ ٱنتَبَذَتۡ مِنۡ أَهۡلِهَا مَكَانٗا شَرۡقِيّٗا

16. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መርየም ከቤተሰቧ ወደ ምስራቃዊ ስፍራ በተለየች ጊዜ የሆነውን ታሪኳን በመጽሐፉ ውስጥ አውሳ:: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 19

فَٱتَّخَذَتۡ مِن دُونِهِمۡ حِجَابٗا فَأَرۡسَلۡنَآ إِلَيۡهَا رُوحَنَا فَتَمَثَّلَ لَهَا بَشَرٗا سَوِيّٗا

17. ከእነርሱም መጋረጃን አደረገች:: መንፈሳችንንም (መልዐኩ ጂብሪልን) ወደ እርሷ ላክን:: ለእርሷም ትክክለኛ ሰው ሆኖ ተመሰለላት:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 19

قَالَتۡ إِنِّيٓ أَعُوذُ بِٱلرَّحۡمَٰنِ مِنكَ إِن كُنتَ تَقِيّٗا

18. «ካንተ በአር-ረህማን እጠበቃለሁ። ጌታህን ፈሪ ከሆንክ (አትቅረበኝ)።» አለች። info
التفاسير:

external-link copy
19 : 19

قَالَ إِنَّمَآ أَنَا۠ رَسُولُ رَبِّكِ لِأَهَبَ لَكِ غُلَٰمٗا زَكِيّٗا

19. «እኔ ንጹሕ የሆነን ልጅ ላንቺ ልሰጥ የመጣሁ የጌታሽ መልዕክተኛ ነኝ።» አላት። info
التفاسير:

external-link copy
20 : 19

قَالَتۡ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي غُلَٰمٞ وَلَمۡ يَمۡسَسۡنِي بَشَرٞ وَلَمۡ أَكُ بَغِيّٗا

20. «በጋብቻ አንድም ሰው ያልነካኝ ሆኜ አመንዝራ ዝሙትኛ ሳልሆን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል!» አለች። info
التفاسير:

external-link copy
21 : 19

قَالَ كَذَٰلِكِ قَالَ رَبُّكِ هُوَ عَلَيَّ هَيِّنٞۖ وَلِنَجۡعَلَهُۥٓ ءَايَةٗ لِّلنَّاسِ وَرَحۡمَةٗ مِّنَّاۚ وَكَانَ أَمۡرٗا مَّقۡضِيّٗا

21. (መልአኩም) «ነገሩ ልክ እንደዚሁ ነው የሚፈጸመው። ጌታሽ ‹እርሱ በእኔ ላይ ገር ነው:: ለሰዎችም ተዓምር ከእኛም ችሮታ ልናደርገው ይህንን ሰራን፤ ነገሩ የተወሰነም ነው።› ብሏል።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
22 : 19

۞ فَحَمَلَتۡهُ فَٱنتَبَذَتۡ بِهِۦ مَكَانٗا قَصِيّٗا

22. ወዲያውኑም አረገዘችው:: እርሱንም በሆድዋ ይዛው ወደ ሩቅ ስፍራ ገለል አለች:: info
التفاسير:

external-link copy
23 : 19

فَأَجَآءَهَا ٱلۡمَخَاضُ إِلَىٰ جِذۡعِ ٱلنَّخۡلَةِ قَالَتۡ يَٰلَيۡتَنِي مِتُّ قَبۡلَ هَٰذَا وَكُنتُ نَسۡيٗا مَّنسِيّٗا

23. ምጡ ወደ ዘንባባይቱ ግንድ አስጠጋት:: እርሷም «ወይኔ! ምነው ከዚህ በፊት በሞትኩና የተረሳሁ በሆንኩ።» አለች። info
التفاسير:

external-link copy
24 : 19

فَنَادَىٰهَا مِن تَحۡتِهَآ أَلَّا تَحۡزَنِي قَدۡ جَعَلَ رَبُّكِ تَحۡتَكِ سَرِيّٗا

24. ከበታቿም እንዲህ ሲል ጠራት: «አትዘኝ። ጌታሽ ከበታችሽ ትንሽን ወንዝ በእርግጥ አድርጓልና። info
التفاسير:

external-link copy
25 : 19

وَهُزِّيٓ إِلَيۡكِ بِجِذۡعِ ٱلنَّخۡلَةِ تُسَٰقِطۡ عَلَيۡكِ رُطَبٗا جَنِيّٗا

25. «የዘምባባይቱን ግንድ ወደ አንቺ ወዝውዢው:: በአንቺ ላይ የበሰለን የተምር እሸት ያረግፍልሻልና። info
التفاسير: