ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
24 : 48

وَهُوَ ٱلَّذِي كَفَّ أَيۡدِيَهُمۡ عَنكُمۡ وَأَيۡدِيَكُمۡ عَنۡهُم بِبَطۡنِ مَكَّةَ مِنۢ بَعۡدِ أَنۡ أَظۡفَرَكُمۡ عَلَيۡهِمۡۚ وَكَانَ ٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرًا

እርሱም ያ በመካ ውስጥ በእነርሱ ላይ ካስቻለችሁ በኋላ እጆቻቸውን ከእናንተ ላይ እጆቻችሁንም ከእነርሱ ላይ የከለከለ ነው፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
25 : 48

هُمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَصَدُّوكُمۡ عَنِ ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡحَرَامِ وَٱلۡهَدۡيَ مَعۡكُوفًا أَن يَبۡلُغَ مَحِلَّهُۥۚ وَلَوۡلَا رِجَالٞ مُّؤۡمِنُونَ وَنِسَآءٞ مُّؤۡمِنَٰتٞ لَّمۡ تَعۡلَمُوهُمۡ أَن تَطَـُٔوهُمۡ فَتُصِيبَكُم مِّنۡهُم مَّعَرَّةُۢ بِغَيۡرِ عِلۡمٖۖ لِّيُدۡخِلَ ٱللَّهُ فِي رَحۡمَتِهِۦ مَن يَشَآءُۚ لَوۡ تَزَيَّلُواْ لَعَذَّبۡنَا ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِنۡهُمۡ عَذَابًا أَلِيمًا

እነርሱ እነዚያ የካዱ፣ ከተከበረው መስጊድም የከለከሏችሁ፣ መስዋእቱንም የታሰረ ሲኾን በስፍራው እንዳይደርስ (የከለከሉ) ናቸው፡፡ የማታውቋቸው የኾኑ ምእመናን ወንዶችና ምእምናት ሴቶች (ከከሓዲዎቹ ጋር) ባልነበሩ ያለ ዕውቀት እነርሱን መርገጣችሁና ከእነርሱ (በኩል) መከፋት የሚነካችሁ ባልኾነ ኖሮ (እጆቻችሁን ባላገድን ነበር) አላህ የሚሻውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያገባ ዘንድ (እጆቻችሁን አገደ)፡፡ በተለዩ ኖሮ እነዚያን ከእነርሱ ውስጥ የካዱትን አሳማሚን ቅጣት በቀጣናቸው ነበር፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
26 : 48

إِذۡ جَعَلَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فِي قُلُوبِهِمُ ٱلۡحَمِيَّةَ حَمِيَّةَ ٱلۡجَٰهِلِيَّةِ فَأَنزَلَ ٱللَّهُ سَكِينَتَهُۥ عَلَىٰ رَسُولِهِۦ وَعَلَى ٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَأَلۡزَمَهُمۡ كَلِمَةَ ٱلتَّقۡوَىٰ وَكَانُوٓاْ أَحَقَّ بِهَا وَأَهۡلَهَاۚ وَكَانَ ٱللَّهُ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٗا

እነዚያ የካዱት ደራይቱን የመሀይምነቲቱን ደራ በልቦቻቸው ውስጥ ባደረጉ ጊዜ (በቀጣናቸው ነበር)፡፡ አላህም በመልክተኛው ላይና በምእምናኖቹ ላይ እርጋታውን አወረደ፡፡ መጥጠበቂያይቱንም ቃል አስያዛቸው፡፡ በእርሷም ተገቢዎች ባለቤቶችዋም ነበሩ፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
27 : 48

لَّقَدۡ صَدَقَ ٱللَّهُ رَسُولَهُ ٱلرُّءۡيَا بِٱلۡحَقِّۖ لَتَدۡخُلُنَّ ٱلۡمَسۡجِدَ ٱلۡحَرَامَ إِن شَآءَ ٱللَّهُ ءَامِنِينَ مُحَلِّقِينَ رُءُوسَكُمۡ وَمُقَصِّرِينَ لَا تَخَافُونَۖ فَعَلِمَ مَا لَمۡ تَعۡلَمُواْ فَجَعَلَ مِن دُونِ ذَٰلِكَ فَتۡحٗا قَرِيبًا

አላህ ለመልክተኛው ሕልሙን እውነተኛ ሲኾን አላህ የሻ እንደ ኾነ ጸጥተኞች ኾናችሁ ራሶቻችሁን ላጭታችሁ፣ አሳጥራችሁም የማትፈሩ ስትኾኑ የተከበረውን መስጊድ በእርግጥ ትገባላችሁ፤ ያለውን በእርግጥ እውነት አደረገለት፡፡ (ከእርቁ) ያላወቃችሁትንም ነገር ዐወቀ፡፡ ከዚህም በፊት ቅርብን መክፈት አደረገ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
28 : 48

هُوَ ٱلَّذِيٓ أَرۡسَلَ رَسُولَهُۥ بِٱلۡهُدَىٰ وَدِينِ ٱلۡحَقِّ لِيُظۡهِرَهُۥ عَلَى ٱلدِّينِ كُلِّهِۦۚ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ شَهِيدٗا

እርሱ ያ መልክተኛውን በመሪ መጽሐፍና በእውነተኛ ሃይማኖት በሃይማኖት ሁሉ ላይ ሊያልቀው የላከ ነው፡፡ መስካሪም በአላህ በቃ፡፡ info
التفاسير: