ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

አል ፈትህ

external-link copy
1 : 48

إِنَّا فَتَحۡنَا لَكَ فَتۡحٗا مُّبِينٗا

እኛ ላንተ ግልጽ የኾነን መክፈት ከፈትንልህ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 48

لِّيَغۡفِرَ لَكَ ٱللَّهُ مَا تَقَدَّمَ مِن ذَنۢبِكَ وَمَا تَأَخَّرَ وَيُتِمَّ نِعۡمَتَهُۥ عَلَيۡكَ وَيَهۡدِيَكَ صِرَٰطٗا مُّسۡتَقِيمٗا

አላህ ከኃጢአትህ ያለፈውንና የሚመጣውን ላንተ ሊምር ጸጋውንም ባንተ ላይ ሊሞላ ቀጥተኛውንም መንገድ ሊመራህ (ከፈተልህ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
3 : 48

وَيَنصُرَكَ ٱللَّهُ نَصۡرًا عَزِيزًا

አላህ ብርቱን እርዳታ ሊረዳህም (ከፈተልህ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
4 : 48

هُوَ ٱلَّذِيٓ أَنزَلَ ٱلسَّكِينَةَ فِي قُلُوبِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ لِيَزۡدَادُوٓاْ إِيمَٰنٗا مَّعَ إِيمَٰنِهِمۡۗ وَلِلَّهِ جُنُودُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمٗا

እርሱ ያ በምእምናን ልቦች ውስጥ ከእምነታቸው ጋር እምነትን ይጨምሩ ዘንድ እርጋታን ያወረደ ነው፡፡ ለአላህም የሰማያትና የምድር ሰራዊቶች አልሉት፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 48

لِّيُدۡخِلَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتِ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا وَيُكَفِّرَ عَنۡهُمۡ سَيِّـَٔاتِهِمۡۚ وَكَانَ ذَٰلِكَ عِندَ ٱللَّهِ فَوۡزًا عَظِيمٗا

ምእምናንንና ምእምናትን ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ ሊያገባቸው ከነርሱም ኃጢአቶቻቸውን ሊያብስላቸው (በትግል አዘዛቸው)፡፡ ይህም ከአላህ ዘንድ የኾነ ታላቅ ማግኘት ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
6 : 48

وَيُعَذِّبَ ٱلۡمُنَٰفِقِينَ وَٱلۡمُنَٰفِقَٰتِ وَٱلۡمُشۡرِكِينَ وَٱلۡمُشۡرِكَٰتِ ٱلظَّآنِّينَ بِٱللَّهِ ظَنَّ ٱلسَّوۡءِۚ عَلَيۡهِمۡ دَآئِرَةُ ٱلسَّوۡءِۖ وَغَضِبَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِمۡ وَلَعَنَهُمۡ وَأَعَدَّ لَهُمۡ جَهَنَّمَۖ وَسَآءَتۡ مَصِيرٗا

በአላህም ክፉ ጥርጣሬን ተጠራጣሪዎቹን መናፍቃንና መናፍቃትን፣ ወንዶች አጋሪዎቻችንና ሴቶች አጋሪዎችንም ያሰቃይ ዘንድ (በትግል አዘዘ)፡፡ በእነርሱ ላይ ክፉ ከባቢ አለባቸው፡፡ በእነርሱም ላይ አላህ ተቆጣባቸው፡፡ ረገማቸውም፡፡ ለእነርሱም ገሀነምን አዘጋጀላቸው፡፡ መመለሻነትዋም ከፋች፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
7 : 48

وَلِلَّهِ جُنُودُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمًا

ለአላህም የሰማያትና የምድር ሰራዊቶች አልሉት፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
8 : 48

إِنَّآ أَرۡسَلۡنَٰكَ شَٰهِدٗا وَمُبَشِّرٗا وَنَذِيرٗا

እኛ መስካሪ አብሳሪና አስፈራሪም አድርገን በእርግጥ ላክንህ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
9 : 48

لِّتُؤۡمِنُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَتُعَزِّرُوهُ وَتُوَقِّرُوهُۚ وَتُسَبِّحُوهُ بُكۡرَةٗ وَأَصِيلًا

በአላህ ልታምኑ፣ በመልክተኛውም (ልታምኑ)፣ ልትረዱትም፣ ልታከብሩትም፣ (አላህን) በጧትና ከቀትር በኋላ ልታወድሱትም (ላክነው)፡፡ info
التفاسير: