ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
16 : 48

قُل لِّلۡمُخَلَّفِينَ مِنَ ٱلۡأَعۡرَابِ سَتُدۡعَوۡنَ إِلَىٰ قَوۡمٍ أُوْلِي بَأۡسٖ شَدِيدٖ تُقَٰتِلُونَهُمۡ أَوۡ يُسۡلِمُونَۖ فَإِن تُطِيعُواْ يُؤۡتِكُمُ ٱللَّهُ أَجۡرًا حَسَنٗاۖ وَإِن تَتَوَلَّوۡاْ كَمَا تَوَلَّيۡتُم مِّن قَبۡلُ يُعَذِّبۡكُمۡ عَذَابًا أَلِيمٗا

ከአዕራቦች ወደ ኋላ ለቀሩት በላቸው፡- «የብርቱ ጭካኔ ባለቤት ወደ ኾኑ ሕዝቦች (ውጊያ) ወደ ፊት ትጥጠራላችሁ፡፡ ትጋደሏቸዋላችሁ፤ ወይም ይሰልማሉ፡፡ ብትታዘዙም አላህ መልካም ምንዳን ይሰጣችኋል፡፡ ከአሁን በፊት እንደ ሸሻችሁ ብትሸሹም አሳማሚን ቅጣት ይቀጣችኋል፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
17 : 48

لَّيۡسَ عَلَى ٱلۡأَعۡمَىٰ حَرَجٞ وَلَا عَلَى ٱلۡأَعۡرَجِ حَرَجٞ وَلَا عَلَى ٱلۡمَرِيضِ حَرَجٞۗ وَمَن يُطِعِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ يُدۡخِلۡهُ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُۖ وَمَن يَتَوَلَّ يُعَذِّبۡهُ عَذَابًا أَلِيمٗا

በዕውር ላይ (ከዘመቻ በመቅቱ) ኃጢአት የለበትም፡፡ በአንካሳም ላይ ኃጢአት የለበትም፡፡ በበሽተኛም ላይ ኃጢአት የለበትም፡፡ አላህንና መልክተኛውንም የሚታዘዝ ሰው ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ያገባዋል፡፡ የሚሸሸውንም ሰው አሳማሚውን ቅጣት ይቀጣዋል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
18 : 48

۞ لَّقَدۡ رَضِيَ ٱللَّهُ عَنِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ إِذۡ يُبَايِعُونَكَ تَحۡتَ ٱلشَّجَرَةِ فَعَلِمَ مَا فِي قُلُوبِهِمۡ فَأَنزَلَ ٱلسَّكِينَةَ عَلَيۡهِمۡ وَأَثَٰبَهُمۡ فَتۡحٗا قَرِيبٗا

ከምእምናኖቹ በዛፊቱ ሥር ቃል ኪዳን በሚጋቡህ ጊዜ አላህ በእርግጥ ወደደ፡፡ በልቦቻቸውም ውስጥ ያለውን ዐወቀ፡፡ በእነርሱም ላይ እርጋታን አወረደ፡፡ ቅርብ የኾነንም መክፈት መነዳቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
19 : 48

وَمَغَانِمَ كَثِيرَةٗ يَأۡخُذُونَهَاۗ وَكَانَ ٱللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمٗا

ብዙዎች ዘረፋዎችንም የሚወስዷቸው የኾኑን (መነዳቸው)፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
20 : 48

وَعَدَكُمُ ٱللَّهُ مَغَانِمَ كَثِيرَةٗ تَأۡخُذُونَهَا فَعَجَّلَ لَكُمۡ هَٰذِهِۦ وَكَفَّ أَيۡدِيَ ٱلنَّاسِ عَنكُمۡ وَلِتَكُونَ ءَايَةٗ لِّلۡمُؤۡمِنِينَ وَيَهۡدِيَكُمۡ صِرَٰطٗا مُّسۡتَقِيمٗا

አላህ ብዙዎችን ዘረፋዎች የምትወስዷቸው የኾኑን ተስፋ አደረገላችሁ፡፡ ይህችንም ለእናንተ አስቸኮለላችሁ፡፡ ከእናንተም የሰዎችን እጆች ከለከለላችሁ፡፡ (ልታመሰግኑትና) ለምእምናንም ምልክት እንድትኾን ቀጥተኛውን መንገድ ይመራችሁም ዘንድ (ይህንን ሠራላችሁ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
21 : 48

وَأُخۡرَىٰ لَمۡ تَقۡدِرُواْ عَلَيۡهَا قَدۡ أَحَاطَ ٱللَّهُ بِهَاۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٗا

ሌላይቱንም በእርሷ ላይ ገና ያልቻላችኋትን አላህ ያወቃትን (ለእናንተ አዘጋጃት)፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
22 : 48

وَلَوۡ قَٰتَلَكُمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَوَلَّوُاْ ٱلۡأَدۡبَٰرَ ثُمَّ لَا يَجِدُونَ وَلِيّٗا وَلَا نَصِيرٗا

እነዚያም የካዱት (የመካ ሰዎች በሑደይቢያ) በተወጉወችሁ ኖሮ ( ለሺሺት) ጀርባዎችን ባዞሩ ነበር፡፡ ከዚያም ዘመድም ረዳትም አያገኙም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
23 : 48

سُنَّةَ ٱللَّهِ ٱلَّتِي قَدۡ خَلَتۡ مِن قَبۡلُۖ وَلَن تَجِدَ لِسُنَّةِ ٱللَّهِ تَبۡدِيلٗا

አላህ ያችን ከዚህ በፊት በእርግጥ ያለፈችውን ልማድ ደነገገ፡፡ ለአላህም ልማድ ለውጥን አታገኝም፡፡ info
التفاسير: