ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
127 : 37

فَكَذَّبُوهُ فَإِنَّهُمۡ لَمُحۡضَرُونَ

አስተባበሉትም፡፡ ስለዚህ እነርሱ (ለቅጣት) የሚጣዱ ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
128 : 37

إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ

ንጹሕ የተደረጉት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
129 : 37

وَتَرَكۡنَا عَلَيۡهِ فِي ٱلۡأٓخِرِينَ

በእርሱ ላይም በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንለት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
130 : 37

سَلَٰمٌ عَلَىٰٓ إِلۡ يَاسِينَ

ሰላም በኢልያሲን ላይ ይሁን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
131 : 37

إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ

እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
132 : 37

إِنَّهُۥ مِنۡ عِبَادِنَا ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

እርሱ በእርግጥ ከምእመናን ባሮቻችን ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
133 : 37

وَإِنَّ لُوطٗا لَّمِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ

ሉጥም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
134 : 37

إِذۡ نَجَّيۡنَٰهُ وَأَهۡلَهُۥٓ أَجۡمَعِينَ

እርሱንና ቤተሰቦቹን ሁሉንም በአዳንናቸው ጊዜ (አስታውስ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
135 : 37

إِلَّا عَجُوزٗا فِي ٱلۡغَٰبِرِينَ

(በቅጣቱ ውስጥ) ከቀሪዎቹ የሆነችው አሮጊት ብቻ ስትቀር፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
136 : 37

ثُمَّ دَمَّرۡنَا ٱلۡأٓخَرِينَ

ከዚያም ሌሎቹን አጠፋን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
137 : 37

وَإِنَّكُمۡ لَتَمُرُّونَ عَلَيۡهِم مُّصۡبِحِينَ

እናንተም ያነጋችሁ ስትሆኑ በእነርሱ (መኖሪያዎች) ላይ (በቀን) ታልፋላችሁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
138 : 37

وَبِٱلَّيۡلِۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ

በሌሊትም (ታልፋላችሁ)፤ ልብም አታደርጉምን? info
التفاسير:

external-link copy
139 : 37

وَإِنَّ يُونُسَ لَمِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ

ዩኑስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
140 : 37

إِذۡ أَبَقَ إِلَى ٱلۡفُلۡكِ ٱلۡمَشۡحُونِ

ወደ ተመላው መርከብ በኮበለለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
141 : 37

فَسَاهَمَ فَكَانَ مِنَ ٱلۡمُدۡحَضِينَ

ዕጣም ተጣጣለ፡፡ ከተሸነፉትም ሆነ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
142 : 37

فَٱلۡتَقَمَهُ ٱلۡحُوتُ وَهُوَ مُلِيمٞ

እርሱም ተወቃሽ ሲሆን ዐሳው ዋጠው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
143 : 37

فَلَوۡلَآ أَنَّهُۥ كَانَ مِنَ ٱلۡمُسَبِّحِينَ

እርሱ ለጌታው ከአወዳሾቹ ባልሆነም ኖሮ፤ info
التفاسير:

external-link copy
144 : 37

لَلَبِثَ فِي بَطۡنِهِۦٓ إِلَىٰ يَوۡمِ يُبۡعَثُونَ

እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ በሆዱ ውስጥ በቆየ ነበር፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
145 : 37

۞ فَنَبَذۡنَٰهُ بِٱلۡعَرَآءِ وَهُوَ سَقِيمٞ

እርሱ በሽተኛ ሆኖ በቃይ በሌለው (በባሕር) ዳርቻ ላይ ጣልነውም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
146 : 37

وَأَنۢبَتۡنَا عَلَيۡهِ شَجَرَةٗ مِّن يَقۡطِينٖ

በእርሱም ላይ (በአጠገቡ) ከቅል የሆነችን ዛፍ አበቀልን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
147 : 37

وَأَرۡسَلۡنَٰهُ إِلَىٰ مِاْئَةِ أَلۡفٍ أَوۡ يَزِيدُونَ

ወደ መቶ ሺሕ ሰዎችም (ዳግመኛ) ላክነው፡፡ ከቶውንም ይጨምራሉ። info
التفاسير:

external-link copy
148 : 37

فَـَٔامَنُواْ فَمَتَّعۡنَٰهُمۡ إِلَىٰ حِينٖ

አመኑም፡፡ እስከ ጊዜ ድረስም አጣቀምናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
149 : 37

فَٱسۡتَفۡتِهِمۡ أَلِرَبِّكَ ٱلۡبَنَاتُ وَلَهُمُ ٱلۡبَنُونَ

ጠይቃቸውም፡፡ «ለጌታህ ሴቶች ልጆች ለእነርሱም ወንዶች ልጆች ይኖራልን?» info
التفاسير:

external-link copy
150 : 37

أَمۡ خَلَقۡنَا ٱلۡمَلَٰٓئِكَةَ إِنَٰثٗا وَهُمۡ شَٰهِدُونَ

ወይስ እኛ እነርሱ የተጣዱ ሆነው መላእክትን ሴቶች አድርገን ፈጠርን? info
التفاسير:

external-link copy
151 : 37

أَلَآ إِنَّهُم مِّنۡ إِفۡكِهِمۡ لَيَقُولُونَ

ንቁ! እነርሱ ከቅጥፈታቸው (የተነሳ) ይላሉ፡- info
التفاسير:

external-link copy
152 : 37

وَلَدَ ٱللَّهُ وَإِنَّهُمۡ لَكَٰذِبُونَ

«አላህ (መላእክትን) ወለደ፡፡» እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
153 : 37

أَصۡطَفَى ٱلۡبَنَاتِ عَلَى ٱلۡبَنِينَ

በወንዶች ልጆች ላይ ይልቅ ሴቶችን ልጆች መረጥን? info
التفاسير: