ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
25 : 37

مَا لَكُمۡ لَا تَنَاصَرُونَ

(ለእነርሱም) «የማትረዳዱት ለእናንተ ምን አላችሁ? (ይባላሉ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
26 : 37

بَلۡ هُمُ ٱلۡيَوۡمَ مُسۡتَسۡلِمُونَ

በእርግጥ እነርሱ ዛሬ እጃቸውን የሰጡ ወራዳዎች ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
27 : 37

وَأَقۡبَلَ بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖ يَتَسَآءَلُونَ

የሚወቃቀሱም ሆነው ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ይመጣሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
28 : 37

قَالُوٓاْ إِنَّكُمۡ كُنتُمۡ تَأۡتُونَنَا عَنِ ٱلۡيَمِينِ

(ለአስከታዮቹ) እናንተ ከስተቀኝ ትመጡብን ነበር ይላሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
29 : 37

قَالُواْ بَل لَّمۡ تَكُونُواْ مُؤۡمِنِينَ

(አስከታዮቹም) ይላሉ «አይደለም ፈጽሞ ምእምናን አልነበራችሁም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
30 : 37

وَمَا كَانَ لَنَا عَلَيۡكُم مِّن سُلۡطَٰنِۭۖ بَلۡ كُنتُمۡ قَوۡمٗا طَٰغِينَ

«ለእኛም በእናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልነበረንም፡፡ በእርግጥ እናንተ ጠማሞች ሕዝቦች ነበራችሁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
31 : 37

فَحَقَّ عَلَيۡنَا قَوۡلُ رَبِّنَآۖ إِنَّا لَذَآئِقُونَ

«በእኛም ላይ የጌታችን ቃል ተረጋገጠብን፤ እኛ (ሁላችንም ቅጣቱን) ቀማሾች ነን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
32 : 37

فَأَغۡوَيۡنَٰكُمۡ إِنَّا كُنَّا غَٰوِينَ

«ወደ ጥምመት ጠራናችሁም፡፡ እኛ ጠማሞች ነበርንና» (ይላሉ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
33 : 37

فَإِنَّهُمۡ يَوۡمَئِذٖ فِي ٱلۡعَذَابِ مُشۡتَرِكُونَ

ስለዚህ እነርሱ በዚያ ቀን በቅጣቱ ተጋሪዎች ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
34 : 37

إِنَّا كَذَٰلِكَ نَفۡعَلُ بِٱلۡمُجۡرِمِينَ

እኛ በአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሠራለን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
35 : 37

إِنَّهُمۡ كَانُوٓاْ إِذَا قِيلَ لَهُمۡ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا ٱللَّهُ يَسۡتَكۡبِرُونَ

እነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
36 : 37

وَيَقُولُونَ أَئِنَّا لَتَارِكُوٓاْ ءَالِهَتِنَا لِشَاعِرٖ مَّجۡنُونِۭ

እኛ ለዕብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው ነን? ይሉም ነበር፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
37 : 37

بَلۡ جَآءَ بِٱلۡحَقِّ وَصَدَّقَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ

አይደለም እውነቱን (ሃይማኖት) አመጣ፡፡ መልክተኞቹንም እውነተኛነታቸውን አረጋገጠ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
38 : 37

إِنَّكُمۡ لَذَآئِقُواْ ٱلۡعَذَابِ ٱلۡأَلِيمِ

እናንተ አሳማሚውን ቅጣት በእርግጥ ቀማሾች ናችሁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
39 : 37

وَمَا تُجۡزَوۡنَ إِلَّا مَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ

ትሠሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
40 : 37

إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ

ግን ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች (ቅጣትን አይቀምሱም)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
41 : 37

أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ رِزۡقٞ مَّعۡلُومٞ

እነዚያ ለእነርሱ የታወቀ ሲሳይ አላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
42 : 37

فَوَٰكِهُ وَهُم مُّكۡرَمُونَ

ፍራፍሬዎች (አሏቸው) እነርሱም የተከበሩ ናቸው፤ info
التفاسير:

external-link copy
43 : 37

فِي جَنَّٰتِ ٱلنَّعِيمِ

በድሎት ገነቶች ውስጥ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
44 : 37

عَلَىٰ سُرُرٖ مُّتَقَٰبِلِينَ

ፊት ለፊት የሚታያዩ ሲሆኑ በአልጋዎች ላይ (ይንፈላሰሳሉ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
45 : 37

يُطَافُ عَلَيۡهِم بِكَأۡسٖ مِّن مَّعِينِۭ

ከሚመነጭ ወይን ጠጅ በያዘ ብርጭቆ በእነርሱ ላይ ይዞርባቸዋል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
46 : 37

بَيۡضَآءَ لَذَّةٖ لِّلشَّٰرِبِينَ

ነጭ ለጠጪዎች ጣፋጭ ከኾነች፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
47 : 37

لَا فِيهَا غَوۡلٞ وَلَا هُمۡ عَنۡهَا يُنزَفُونَ

በእርሷ ውስጥም ምታት የለባትም፡፡ እነርሱም ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
48 : 37

وَعِندَهُمۡ قَٰصِرَٰتُ ٱلطَّرۡفِ عِينٞ

እነርሱም ዘንድ ዓይናቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች የኾኑ ዓይናማዎች አልሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
49 : 37

كَأَنَّهُنَّ بَيۡضٞ مَّكۡنُونٞ

እነርሱ ልክ የተሸፈነ (የሰጎን) ዕንቁላል ይመስላሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
50 : 37

فَأَقۡبَلَ بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖ يَتَسَآءَلُونَ

የሚጠያየቁም ሆነው ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ይመጣሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
51 : 37

قَالَ قَآئِلٞ مِّنۡهُمۡ إِنِّي كَانَ لِي قَرِينٞ

ከእነርሱ የሆነ ተናጋሪ ይላል «እኔ ጓደኛ ነበረኝ፡፡ info
التفاسير: