ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
103 : 37

فَلَمَّآ أَسۡلَمَا وَتَلَّهُۥ لِلۡجَبِينِ

ሁለቱም ትዕዛዙን በተቀበሉና በግንባሩም ጎን ላይ በጣለው ጊዜ (የሆነው ሆነ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
104 : 37

وَنَٰدَيۡنَٰهُ أَن يَٰٓإِبۡرَٰهِيمُ

ጠራነውም፤ (አልነው) «ኢብራሂም ሆይ! info
التفاسير:

external-link copy
105 : 37

قَدۡ صَدَّقۡتَ ٱلرُّءۡيَآۚ إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ

ራእይቱን በእውነት አረጋገጥክ፡፡» እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
106 : 37

إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلۡبَلَٰٓؤُاْ ٱلۡمُبِينُ

ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
107 : 37

وَفَدَيۡنَٰهُ بِذِبۡحٍ عَظِيمٖ

በታላቅ ዕርድም (መስዋዕት) ተቤዠነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
108 : 37

وَتَرَكۡنَا عَلَيۡهِ فِي ٱلۡأٓخِرِينَ

በእርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን አስቀረንለት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
109 : 37

سَلَٰمٌ عَلَىٰٓ إِبۡرَٰهِيمَ

ሰላም በኢብራሂም ላይ ይሁን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
110 : 37

كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ

እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
111 : 37

إِنَّهُۥ مِنۡ عِبَادِنَا ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

እርሱ በእርግጥ ካመኑት ባሮቻችን ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
112 : 37

وَبَشَّرۡنَٰهُ بِإِسۡحَٰقَ نَبِيّٗا مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ

በኢስሐቅም አበሰርነው፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
113 : 37

وَبَٰرَكۡنَا عَلَيۡهِ وَعَلَىٰٓ إِسۡحَٰقَۚ وَمِن ذُرِّيَّتِهِمَا مُحۡسِنٞ وَظَالِمٞ لِّنَفۡسِهِۦ مُبِينٞ

በእርሱና በኢስሐቅ ላይም ባረክን፡፡ ከሁለቱም ዘሮች በጎ ሠሪ አልለ፡፡ ለነፍሱ ግልጽ በዳይም አለ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
114 : 37

وَلَقَدۡ مَنَنَّا عَلَىٰ مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ

በሙሳና በሃሩን ላይም በእርግጥ ለገስን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
115 : 37

وَنَجَّيۡنَٰهُمَا وَقَوۡمَهُمَا مِنَ ٱلۡكَرۡبِ ٱلۡعَظِيمِ

እነርሱንም ሕዝቦቻቸውንም ከታላቅ ጭንቅ አዳንን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
116 : 37

وَنَصَرۡنَٰهُمۡ فَكَانُواْ هُمُ ٱلۡغَٰلِبِينَ

ረዳናቸውም፡፡ እነርሱም አሸናፊዎች ነበሩ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
117 : 37

وَءَاتَيۡنَٰهُمَا ٱلۡكِتَٰبَ ٱلۡمُسۡتَبِينَ

በጣም የተብራራውንም መጽሐፍ ሰጠናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
118 : 37

وَهَدَيۡنَٰهُمَا ٱلصِّرَٰطَ ٱلۡمُسۡتَقِيمَ

ቀጥተኛውንም መንገድ መራናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
119 : 37

وَتَرَكۡنَا عَلَيۡهِمَا فِي ٱلۡأٓخِرِينَ

በሁለቱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
120 : 37

سَلَٰمٌ عَلَىٰ مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ

ሰላም በሙሳና በሃሩን ላይ ይሁን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
121 : 37

إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ

እኛ እንደዚሁ በጎ አድራጊዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
122 : 37

إِنَّهُمَا مِنۡ عِبَادِنَا ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

ሁለቱም በእርግጥ ከአመኑት ባሮቻችን ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
123 : 37

وَإِنَّ إِلۡيَاسَ لَمِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ

ኢልያስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
124 : 37

إِذۡ قَالَ لِقَوۡمِهِۦٓ أَلَا تَتَّقُونَ

ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፤ አላህን አትፈሩምን? info
التفاسير:

external-link copy
125 : 37

أَتَدۡعُونَ بَعۡلٗا وَتَذَرُونَ أَحۡسَنَ ٱلۡخَٰلِقِينَ

በዕልን ትገዛላችሁን? ከሰዓሊዎቹ ሁሉ ይበልጥ በጣም አሳማሪ የሆነውንም አምላክ ትተዋላችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
126 : 37

ٱللَّهَ رَبَّكُمۡ وَرَبَّ ءَابَآئِكُمُ ٱلۡأَوَّلِينَ

አላህን ጌታችሁንና የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁን ጌታ (ትተዋላችሁን)? info
التفاسير: