ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
137 : 26

إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا خُلُقُ ٱلۡأَوَّلِينَ

«ይህ የፊተኞቹ ሰዎች ፀባይ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
138 : 26

وَمَا نَحۡنُ بِمُعَذَّبِينَ

«እኛም የምንቅቀጣ አይደለንም» (አሉ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
139 : 26

فَكَذَّبُوهُ فَأَهۡلَكۡنَٰهُمۡۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ

አስተባበሉትም፡፡ አጠፋናቸውም፡፡ በዚህም ውስጥ እርግጠኛ ግሳጼ አለበት፡፡ አብዛኞቻቸውም ምእመናን አልነበሩም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
140 : 26

وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ

ጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው አዛኙ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
141 : 26

كَذَّبَتۡ ثَمُودُ ٱلۡمُرۡسَلِينَ

ሰሙድ መልክተኞችን አስተባበለች፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
142 : 26

إِذۡ قَالَ لَهُمۡ أَخُوهُمۡ صَٰلِحٌ أَلَا تَتَّقُونَ

ወንድማቸው ሷሊህ ለእነርሱ ባላቸው ጊዜ «አትጠነቀቁምን ? info
التفاسير:

external-link copy
143 : 26

إِنِّي لَكُمۡ رَسُولٌ أَمِينٞ

«እኔ ለእናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
144 : 26

فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ

«አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
145 : 26

وَمَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ أَجۡرٍۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

«በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልለምናችሁም፡፡ ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
146 : 26

أَتُتۡرَكُونَ فِي مَا هَٰهُنَآ ءَامِنِينَ

«በዚያ እዚህ ባለው (ጸጋ) ውስጥ የረካችሁ ኾናችሁ ትተዋላችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
147 : 26

فِي جَنَّٰتٖ وَعُيُونٖ

«በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
148 : 26

وَزُرُوعٖ وَنَخۡلٖ طَلۡعُهَا هَضِيمٞ

«በአዝመራዎችም ፍሬዋ የበሰለ በኾነች ዘንባባም፤ (ውስጥ ትተዋላችሁን) info
التفاسير:

external-link copy
149 : 26

وَتَنۡحِتُونَ مِنَ ٱلۡجِبَالِ بُيُوتٗا فَٰرِهِينَ

«ብልሆች ኾናችሁ ከጋራዎች ቤቶችንም ትጠርባላችሁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
150 : 26

فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ

«አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
151 : 26

وَلَا تُطِيعُوٓاْ أَمۡرَ ٱلۡمُسۡرِفِينَ

«የወሰን አላፊዎችንም ትዕዛዝ አትከተሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
152 : 26

ٱلَّذِينَ يُفۡسِدُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَا يُصۡلِحُونَ

«የእነዚያን በምድር ላይ የሚያጠፉትንና የማያበጁትን፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
153 : 26

قَالُوٓاْ إِنَّمَآ أَنتَ مِنَ ٱلۡمُسَحَّرِينَ

(እነሱም) አሉ «አንተ በብዙ ከተደገመባቸው ሰዎች ብቻ ነህ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
154 : 26

مَآ أَنتَ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُنَا فَأۡتِ بِـَٔايَةٍ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ

«አንተ ብጤያችን ሰው እንጅ ሌላ አይደለህም፡፡ ከእውነተኞቹም እንደኾንክ ተዓምርን አምጣ፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
155 : 26

قَالَ هَٰذِهِۦ نَاقَةٞ لَّهَا شِرۡبٞ وَلَكُمۡ شِرۡبُ يَوۡمٖ مَّعۡلُومٖ

(እርሱም) አለ «ይህች ግመል ናት፡፡ ለእርሷ የመጠጥ ፋንታ አላት፡፡ ለእናንተም የታወቀ ቀን ፋንታ አላችሁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
156 : 26

وَلَا تَمَسُّوهَا بِسُوٓءٖ فَيَأۡخُذَكُمۡ عَذَابُ يَوۡمٍ عَظِيمٖ

«በክፉም አትንኳት፡፡ የታላቅ ቀን ቅጣት ይይዛችኋልና፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
157 : 26

فَعَقَرُوهَا فَأَصۡبَحُواْ نَٰدِمِينَ

ወጓትም፡፡ ወዲያውም ተጸጻቾች ኾነው አነጉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
158 : 26

فَأَخَذَهُمُ ٱلۡعَذَابُۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ

ቅጣቱም ያዛቸው፡፡ በዚህም ውስጥ ግሳፄ አልለበት፡፡ አብዛኞቻቸውም ምእመናን አልነበሩም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
159 : 26

وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ

ጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው አዛኙ ነው፡፡ info
التفاسير: