ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
207 : 26

مَآ أَغۡنَىٰ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يُمَتَّعُونَ

ይጣቀሙበት የነበሩት ሁሉ ከእነሱ ምንም አያብቃቃቸውም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
208 : 26

وَمَآ أَهۡلَكۡنَا مِن قَرۡيَةٍ إِلَّا لَهَا مُنذِرُونَ

አንዲትንም ከተማ ለእርሷ አስፈራሪዎች ያሏት (እና ያስተባበለች) ኾና እንጅ አላጠፋንም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
209 : 26

ذِكۡرَىٰ وَمَا كُنَّا ظَٰلِمِينَ

(ይህች) ግሳፄ ናት፡፡ በዳዮችም አልነበርንም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
210 : 26

وَمَا تَنَزَّلَتۡ بِهِ ٱلشَّيَٰطِينُ

ሰይጣናትም እርሱን (ቁርኣንን) አላወረዱትም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
211 : 26

وَمَا يَنۢبَغِي لَهُمۡ وَمَا يَسۡتَطِيعُونَ

ለእነርሱም አይገባቸውም፤ አይችሉምም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
212 : 26

إِنَّهُمۡ عَنِ ٱلسَّمۡعِ لَمَعۡزُولُونَ

እነርሱ (የመላእክትን ንግግር) ከመስማት ተከለከሉ ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
213 : 26

فَلَا تَدۡعُ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ فَتَكُونَ مِنَ ٱلۡمُعَذَّبِينَ

ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትግገዛ፤ ከሚቀጡት ትኾናለህና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
214 : 26

وَأَنذِرۡ عَشِيرَتَكَ ٱلۡأَقۡرَبِينَ

ቅርቦች ዘመዶችህንም አስጠንቅቅ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
215 : 26

وَٱخۡفِضۡ جَنَاحَكَ لِمَنِ ٱتَّبَعَكَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

ከምእምናንም ለተከተሉህ ሰዎች ክንፍህን ዝቅ አድርግ፤ (ልዝብ ኹን)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
216 : 26

فَإِنۡ عَصَوۡكَ فَقُلۡ إِنِّي بَرِيٓءٞ مِّمَّا تَعۡمَلُونَ

«እንቢ» ቢሉህም «እኔ ከምትሠሩት ንጹሕ ነኝ» በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
217 : 26

وَتَوَكَّلۡ عَلَى ٱلۡعَزِيزِ ٱلرَّحِيمِ

አሸናፊ አዛኝ በኾነው (ጌታህ) ላይም ተጠጋ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
218 : 26

ٱلَّذِي يَرَىٰكَ حِينَ تَقُومُ

በዚያ ለሶላት በምትቆም ጊዜ በሚያይህ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
219 : 26

وَتَقَلُّبَكَ فِي ٱلسَّٰجِدِينَ

በሰጋጆች ውስጥ መዘዋወርህንም (በሚያየው ጌታህ ላይ ተጠጋ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
220 : 26

إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ

እነሆ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
221 : 26

هَلۡ أُنَبِّئُكُمۡ عَلَىٰ مَن تَنَزَّلُ ٱلشَّيَٰطِينُ

ሰይጣናት በማን ላይ እንደሚወርዱ ልንገራችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
222 : 26

تَنَزَّلُ عَلَىٰ كُلِّ أَفَّاكٍ أَثِيمٖ

በውሸታም ኀጢአተኛ ሁሉ ላይ ይወርዳሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
223 : 26

يُلۡقُونَ ٱلسَّمۡعَ وَأَكۡثَرُهُمۡ كَٰذِبُونَ

የሰሙትን (ወደ ጠንቋዮች) ይጥላሉ፡፡ አብዛኞቻቸውም ውሸታሞች ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
224 : 26

وَٱلشُّعَرَآءُ يَتَّبِعُهُمُ ٱلۡغَاوُۥنَ

ባለ ቅኔዎችንም ጠማማዎቹ ይከተሉዋቸዋል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
225 : 26

أَلَمۡ تَرَ أَنَّهُمۡ فِي كُلِّ وَادٖ يَهِيمُونَ

እነርሱ በ(ንግግር) ሸለቆ ሁሉ የሚዋልሉ መኾናቸውን አታይምን? info
التفاسير:

external-link copy
226 : 26

وَأَنَّهُمۡ يَقُولُونَ مَا لَا يَفۡعَلُونَ

እነሱም የማይሠሩትን ነገር የሚናገሩ መኾናቸውን (አታይምን)፤ info
التفاسير:

external-link copy
227 : 26

إِلَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَذَكَرُواْ ٱللَّهَ كَثِيرٗا وَٱنتَصَرُواْ مِنۢ بَعۡدِ مَا ظُلِمُواْۗ وَسَيَعۡلَمُ ٱلَّذِينَ ظَلَمُوٓاْ أَيَّ مُنقَلَبٖ يَنقَلِبُونَ

እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ አላህንም በብዛት ያወሱ ከተበደሉም በኋላ (በቅኔ) የተከላከሉ ሲቀሩ፤ (እነርሱ አይወቀሱም)፡፡ እነዚያም የበደሉ (ከሞቱ በኋላ) እንዴት ያለን መመለስ እንደሚመለሱ በእርግጥ ያውቃሉ፡፡ info
التفاسير: