ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
112 : 26

قَالَ وَمَا عِلۡمِي بِمَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ

(እርሱም) አላቸው «ይሠሩት በነበሩት ነገር ምን ዕውቀት አለኝ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
113 : 26

إِنۡ حِسَابُهُمۡ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّيۖ لَوۡ تَشۡعُرُونَ

«ምርመራቸው በጌታዬ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም፡፡ ብታውቁ ኖሮ (ይህንን ትርረዱ ነበር)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
114 : 26

وَمَآ أَنَا۠ بِطَارِدِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

«እኔም አማኞችን አባራሪ አይደለሁም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
115 : 26

إِنۡ أَنَا۠ إِلَّا نَذِيرٞ مُّبِينٞ

«እኔ ግልጽ አስፈራሪ እንጅ ሌላ አይደለሁም፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
116 : 26

قَالُواْ لَئِن لَّمۡ تَنتَهِ يَٰنُوحُ لَتَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡمَرۡجُومِينَ

«ኑሕ ሆይ! (ከምትለው) ባትከለከል በእርግጥ ከሚወገሩት ትኾናለህ» አሉት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
117 : 26

قَالَ رَبِّ إِنَّ قَوۡمِي كَذَّبُونِ

(እርሱም) አለ «ጌታዬ ሆይ! ሕዝቦቼ አስተባበሉኝ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
118 : 26

فَٱفۡتَحۡ بَيۡنِي وَبَيۡنَهُمۡ فَتۡحٗا وَنَجِّنِي وَمَن مَّعِيَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

«በእኔና በእነርሱም መካከል (ተገቢ) ፍርድን ፍረድ፡፡ አድነኝም፡፡ ከእኔ ጋር ያሉትንም ምእምናን፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
119 : 26

فَأَنجَيۡنَٰهُ وَمَن مَّعَهُۥ فِي ٱلۡفُلۡكِ ٱلۡمَشۡحُونِ

እርሱንም ከእርሱ ጋር ያለውንም ሁሉ በተመላው መርከብ ውስጥ አዳን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
120 : 26

ثُمَّ أَغۡرَقۡنَا بَعۡدُ ٱلۡبَاقِينَ

ከዚያም በኋላ ቀሪዎቹን አሰጠምን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
121 : 26

إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ

በዚህ ውስጥ ታላቅ ግሳጼ አለበት፡፡ አብዛኞቻቸው አማኞች አልነበሩም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
122 : 26

وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ

ጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው አዛኙ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
123 : 26

كَذَّبَتۡ عَادٌ ٱلۡمُرۡسَلِينَ

ዓድ መልክተኞችን አስተባበለች፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
124 : 26

إِذۡ قَالَ لَهُمۡ أَخُوهُمۡ هُودٌ أَلَا تَتَّقُونَ

ወንድማቸው ሁድ ለነርሱ ባላቸው ጊዜ «አትጠነቀቁምን? info
التفاسير:

external-link copy
125 : 26

إِنِّي لَكُمۡ رَسُولٌ أَمِينٞ

«እኔ ለናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
126 : 26

فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ

«አላህንም ፍሩ ታዘዙኝም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
127 : 26

وَمَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ أَجۡرٍۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

«በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አለምናችሁም፡፡ ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
128 : 26

أَتَبۡنُونَ بِكُلِّ رِيعٍ ءَايَةٗ تَعۡبَثُونَ

«የምትጫወቱ ኾናችሁ በከፍተኛ ስፍራ ሁሉ ላይ ምልክትን ትገነባላችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
129 : 26

وَتَتَّخِذُونَ مَصَانِعَ لَعَلَّكُمۡ تَخۡلُدُونَ

«የውሃ ማጠራቀሚያዎችንና ሕንፃዎችንም ዘላለም መኖርን የምትከጅሉ ኾናችሁ ትሠራላችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
130 : 26

وَإِذَا بَطَشۡتُم بَطَشۡتُمۡ جَبَّارِينَ

«በቀጣችሁም ጊዜ ጨካኞች ኾናችሁ ትቀጣላችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
131 : 26

فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ

«አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
132 : 26

وَٱتَّقُواْ ٱلَّذِيٓ أَمَدَّكُم بِمَا تَعۡلَمُونَ

«ያንንም በምታውቁት (ጸጋ) ያጣቀማችሁን ፍሩ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
133 : 26

أَمَدَّكُم بِأَنۡعَٰمٖ وَبَنِينَ

«በእንስሳዎችና በልጆች ያጣቀማችሁን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
134 : 26

وَجَنَّٰتٖ وَعُيُونٍ

«በአትክልቶችና በምንጮችም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
135 : 26

إِنِّيٓ أَخَافُ عَلَيۡكُمۡ عَذَابَ يَوۡمٍ عَظِيمٖ

«እኔ በእናንተ ላይ የታላቅን ቀን ቅጣት እፈራለሁና፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
136 : 26

قَالُواْ سَوَآءٌ عَلَيۡنَآ أَوَعَظۡتَ أَمۡ لَمۡ تَكُن مِّنَ ٱلۡوَٰعِظِينَ

(እነርሱም) አሉ «ብትገስጽም ወይም ከገሳጮቹ ባትኾንም በእኛ ላይ እኩል ነው፤ (ያለንበትን አንለቅም)፡፡ info
التفاسير: