クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー

ページ番号:close

external-link copy
69 : 6

وَمَا عَلَى ٱلَّذِينَ يَتَّقُونَ مِنۡ حِسَابِهِم مِّن شَيۡءٖ وَلَٰكِن ذِكۡرَىٰ لَعَلَّهُمۡ يَتَّقُونَ

69. እነዚያም በሚጠነቀቁት ህዝቦች ላይ በሂሳባቸው ምንም የለባቸዉም:: ግን ይጠነቀቁ ዘንድ መገሰጽ አለባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
70 : 6

وَذَرِ ٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُواْ دِينَهُمۡ لَعِبٗا وَلَهۡوٗا وَغَرَّتۡهُمُ ٱلۡحَيَوٰةُ ٱلدُّنۡيَاۚ وَذَكِّرۡ بِهِۦٓ أَن تُبۡسَلَ نَفۡسُۢ بِمَا كَسَبَتۡ لَيۡسَ لَهَا مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلِيّٞ وَلَا شَفِيعٞ وَإِن تَعۡدِلۡ كُلَّ عَدۡلٖ لَّا يُؤۡخَذۡ مِنۡهَآۗ أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ أُبۡسِلُواْ بِمَا كَسَبُواْۖ لَهُمۡ شَرَابٞ مِّنۡ حَمِيمٖ وَعَذَابٌ أَلِيمُۢ بِمَا كَانُواْ يَكۡفُرُونَ

70. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያንም ሃይማኖታቸውን ጨዋታና ቀልድ አድርገው የያዙትንና ቅርቢቱ ሕይወት ያታለለቻቸውን ተዋቸው:: ነፍስ ሁሉ በሰራችው ስራ እንዳትጠፋ በእርሱ (በቁርአን) አስታውስ:: ለእርሷ ከአላህ ሌላ ወዳጅም ሆነ አማላጅ ማንም የላትም:: ፊዳ የተባለን ሁሉ ብትከፍል እንኳን ተቀባይነት የላትም:: እነዚያ በሰሩት ስራ የተጠፉት ናቸው:: በክህደታቸው ምክንያት ከፈላ ውሃ መጠጥና አሳማሚ ቅጣት አለባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
71 : 6

قُلۡ أَنَدۡعُواْ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَنفَعُنَا وَلَا يَضُرُّنَا وَنُرَدُّ عَلَىٰٓ أَعۡقَابِنَا بَعۡدَ إِذۡ هَدَىٰنَا ٱللَّهُ كَٱلَّذِي ٱسۡتَهۡوَتۡهُ ٱلشَّيَٰطِينُ فِي ٱلۡأَرۡضِ حَيۡرَانَ لَهُۥٓ أَصۡحَٰبٞ يَدۡعُونَهُۥٓ إِلَى ٱلۡهُدَى ٱئۡتِنَاۗ قُلۡ إِنَّ هُدَى ٱللَّهِ هُوَ ٱلۡهُدَىٰۖ وَأُمِرۡنَا لِنُسۡلِمَ لِرَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

71. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከአላህ ሌላ የማይጠቅምንና የማይጎዳን እንገዛለን? አላህ በቀናው መንገድ ከመራን በኋላ የኋሊት እንመለሳለን? እንደዚያ በምድር ላይ የዋለለ ሲሆን ሰይጣናት አሳስተውት ለእርሱ ‹ወደ እኛ ና› እያሉ ወደ ቅን መንገድ የሚጠሩ ወዳጆች ቢኖሩትም (እንደማይከተላቸው) እንሆናለንን?» በላቸው:: «የአላህ መንገድ ቀጥተኛው መንገድ ነው:: ለዓለማት ጌታ ልንገዛም ታዘዝን።» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
72 : 6

وَأَنۡ أَقِيمُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَٱتَّقُوهُۚ وَهُوَ ٱلَّذِيٓ إِلَيۡهِ تُحۡشَرُونَ

72. «ሶላትን በትክክል ስገዱ አላህን ፍሩትም።» (ተብለን ታዘናል በላቸው።) እርሱ ወደ እርሱ የምትሰበሰቡበት አምላክ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
73 : 6

وَهُوَ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ بِٱلۡحَقِّۖ وَيَوۡمَ يَقُولُ كُن فَيَكُونُۚ قَوۡلُهُ ٱلۡحَقُّۚ وَلَهُ ٱلۡمُلۡكُ يَوۡمَ يُنفَخُ فِي ٱلصُّورِۚ عَٰلِمُ ٱلۡغَيۡبِ وَٱلشَّهَٰدَةِۚ وَهُوَ ٱلۡحَكِيمُ ٱلۡخَبِيرُ

73. እርሱም ያ ሰማያትንና ምድርን በትክክል የፈጠረ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሁን» የሚልበትንና ወዲያዉም የሚሆንበትን ቀን አስታውስ:: ቃሉም እውነት ነው:: በቀንዱ በሚነፋበት ቀንም ንግስናው የእርሱ ብቻ ነው:: ሩቁንና ቅርቡን አዋቂ ነው:: እርሱም ጥበበኛውና ውስጠ አዋቂው ነው:: info
التفاسير: