クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー

ページ番号:close

external-link copy
45 : 6

فَقُطِعَ دَابِرُ ٱلۡقَوۡمِ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْۚ وَٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

45. የእነዚያ የበደሉት ሕዝቦች መጨረሻ ተቆረጠ:: ምስጋና ሁሉ ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ይገባው:: info
التفاسير:

external-link copy
46 : 6

قُلۡ أَرَءَيۡتُمۡ إِنۡ أَخَذَ ٱللَّهُ سَمۡعَكُمۡ وَأَبۡصَٰرَكُمۡ وَخَتَمَ عَلَىٰ قُلُوبِكُم مَّنۡ إِلَٰهٌ غَيۡرُ ٱللَّهِ يَأۡتِيكُم بِهِۗ ٱنظُرۡ كَيۡفَ نُصَرِّفُ ٱلۡأٓيَٰتِ ثُمَّ هُمۡ يَصۡدِفُونَ

46.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እስቲ ንገሩኝ አላህ መስሚያችሁንና ማያዎቻችሁን ቢወሰድባችሁና በልቦቻችሁ ላይ ቢያትም ከአላህ ሌላ እርሱኑ የሚያመጣላችሁ አምላክ ማን ነው?» በላቸው:: አናቅጽን እንዴት እንደምናብራራና ከዚያም እነርሱ እንዴት መንገዱን እንደሚስቱ ተመልከት:: info
التفاسير:

external-link copy
47 : 6

قُلۡ أَرَءَيۡتَكُمۡ إِنۡ أَتَىٰكُمۡ عَذَابُ ٱللَّهِ بَغۡتَةً أَوۡ جَهۡرَةً هَلۡ يُهۡلَكُ إِلَّا ٱلۡقَوۡمُ ٱلظَّٰلِمُونَ

47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እስቲ ንገሩኝ የአላህ ቅጣት ድንገት ወይም በይፋ ቢመጣባችሁ ከአመጸኛ ህዝቦች ሌላ ይጠፋልን?» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
48 : 6

وَمَا نُرۡسِلُ ٱلۡمُرۡسَلِينَ إِلَّا مُبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَۖ فَمَنۡ ءَامَنَ وَأَصۡلَحَ فَلَا خَوۡفٌ عَلَيۡهِمۡ وَلَا هُمۡ يَحۡزَنُونَ

48. መልዕክተኞችንም በመልካም አብሳሪና ከመጥፎ አስፈራሪ አድርገን እንጂ አንልክም:: እናም በእነርሱ ያመኑና በጎ ተግባርን የሰሩ ሁሉ ስጋት የለባቸዉም። አይተክዙምም። info
التفاسير:

external-link copy
49 : 6

وَٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا يَمَسُّهُمُ ٱلۡعَذَابُ بِمَا كَانُواْ يَفۡسُقُونَ

49. እነዚያ አናቅጻችንን ያስተባበሉት ደግሞ በአመፃቸው ምክንያት ቅጣት ያገኛቸዋል። info
التفاسير:

external-link copy
50 : 6

قُل لَّآ أَقُولُ لَكُمۡ عِندِي خَزَآئِنُ ٱللَّهِ وَلَآ أَعۡلَمُ ٱلۡغَيۡبَ وَلَآ أَقُولُ لَكُمۡ إِنِّي مَلَكٌۖ إِنۡ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَيَّۚ قُلۡ هَلۡ يَسۡتَوِي ٱلۡأَعۡمَىٰ وَٱلۡبَصِيرُۚ أَفَلَا تَتَفَكَّرُونَ

50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልላችሁም:: ሩቅ ሚስጥርንም አላውቅም:: መልዓክ ነኝም አልልም:: ወደ እኔ የሚወርድልኝን መልዕክት ብቻ እንጂ ሌላን አልከተልም።» በላቸው። «እውርና የሚያይ ይስተካከላሉን? አታስተነትኑምን!» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
51 : 6

وَأَنذِرۡ بِهِ ٱلَّذِينَ يَخَافُونَ أَن يُحۡشَرُوٓاْ إِلَىٰ رَبِّهِمۡ لَيۡسَ لَهُم مِّن دُونِهِۦ وَلِيّٞ وَلَا شَفِيعٞ لَّعَلَّهُمۡ يَتَّقُونَ

51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ከአላህ ሌላ ወዳጅና አማላጅ የሌላቸው ሲሆኑ ወደ ጌታቸው መሰብሰብን የሚፈሩትን ሰዎች ይጠነቀቁ ዘንድ በእርሱ(ቁርኣን) አስፈራራ:: info
التفاسير:

external-link copy
52 : 6

وَلَا تَطۡرُدِ ٱلَّذِينَ يَدۡعُونَ رَبَّهُم بِٱلۡغَدَوٰةِ وَٱلۡعَشِيِّ يُرِيدُونَ وَجۡهَهُۥۖ مَا عَلَيۡكَ مِنۡ حِسَابِهِم مِّن شَيۡءٖ وَمَا مِنۡ حِسَابِكَ عَلَيۡهِم مِّن شَيۡءٖ فَتَطۡرُدَهُمۡ فَتَكُونَ مِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ

52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያን የጌታቸውን ፊት የሚሹ ሆነው በጧትና በማታ የሚጠሩትን አማኞች ከአጠገብህ አታባር:: እነርሱን መቆጣጠር ባንተ ላይ ምንም የለብህም:: አንተንም መቆጣጠር በእነርሱ ላይ ምንም የለባቸዉም::ታባርራቸውና ከበደለኞችም ትኾን ዘንድ (አታባር)። info
التفاسير: