Traduzione dei Significati del Sacro Corano - Traduzione Amarica - Accademia d'Africa

Numero di pagina:close

external-link copy
48 : 9

لَقَدِ ٱبۡتَغَوُاْ ٱلۡفِتۡنَةَ مِن قَبۡلُ وَقَلَّبُواْ لَكَ ٱلۡأُمُورَ حَتَّىٰ جَآءَ ٱلۡحَقُّ وَظَهَرَ أَمۡرُ ٱللَّهِ وَهُمۡ كَٰرِهُونَ

48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱ ጠይዎች ሲኾኑ እውነቱ እስከመጣና የአላህም ትዕዛዝ እስከተገለጸ ድረስ ከዚህ በፊት ሁከትን በእርግጥ ፈለጉ፡፡ ነገሮችንም ሁሉ አገላበጡልህ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
49 : 9

وَمِنۡهُم مَّن يَقُولُ ٱئۡذَن لِّي وَلَا تَفۡتِنِّيٓۚ أَلَا فِي ٱلۡفِتۡنَةِ سَقَطُواْۗ وَإِنَّ جَهَنَّمَ لَمُحِيطَةُۢ بِٱلۡكَٰفِرِينَ

49. ከእነርሱም ውስጥ «ፍቀድልኝ አትሞክረኝ» የሚል ሰው አለ። (ሙስሊሞች) አስተውሉ! እነኝህ ሰዎች በመከራ ውስጥ ወደቁ:: ገሀነም ከሓዲያንን ከባቢ ናት:: info
التفاسير:

external-link copy
50 : 9

إِن تُصِبۡكَ حَسَنَةٞ تَسُؤۡهُمۡۖ وَإِن تُصِبۡكَ مُصِيبَةٞ يَقُولُواْ قَدۡ أَخَذۡنَآ أَمۡرَنَا مِن قَبۡلُ وَيَتَوَلَّواْ وَّهُمۡ فَرِحُونَ

50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መልካም ነገር ቢያገኝህ ያስከፋቸዋል:: መከራ ቢያገኝህ ግን «ፊቱንም ይህን ፈርተን የግል ጥንቃቄያችንን ይዘናል።» ይላሉ። ተደሳቾች ሆነዉም ይሸሻሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
51 : 9

قُل لَّن يُصِيبَنَآ إِلَّا مَا كَتَبَ ٱللَّهُ لَنَا هُوَ مَوۡلَىٰنَاۚ وَعَلَى ٱللَّهِ فَلۡيَتَوَكَّلِ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ

51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ለእኛ የጻፈልን እንጂ ሌላ አይነካንም:: እርሱ ረዳታችን ነው:: ምዕምናን በአላህ ላይ ብቻ ይመኩ።» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
52 : 9

قُلۡ هَلۡ تَرَبَّصُونَ بِنَآ إِلَّآ إِحۡدَى ٱلۡحُسۡنَيَيۡنِۖ وَنَحۡنُ نَتَرَبَّصُ بِكُمۡ أَن يُصِيبَكُمُ ٱللَّهُ بِعَذَابٖ مِّنۡ عِندِهِۦٓ أَوۡ بِأَيۡدِينَاۖ فَتَرَبَّصُوٓاْ إِنَّا مَعَكُم مُّتَرَبِّصُونَ

52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእኛ ላይ ከሁለቱ መልካሞች አንደኛዋን እንጂ ሌላን ትጠባበቃላችሁን? እኛም አላህ ከእርሱ በሆነው ቅጣት ወይም በእጆቻችን የሚያጠፋችሁ መሆኑን በእናንተ ላይ እንጠባበቃለን:: ተጠባበቁ:: እኛም ከናንተው ጋር ተጠባባቂዎች ነንና።» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
53 : 9

قُلۡ أَنفِقُواْ طَوۡعًا أَوۡ كَرۡهٗا لَّن يُتَقَبَّلَ مِنكُمۡ إِنَّكُمۡ كُنتُمۡ قَوۡمٗا فَٰسِقِينَ

53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ወዳችሁም ሆነ ጠልታችሁ ለግሱ ከናንተ ተቀባይ የላችሁም:: እናንተ አመጸኞች ህዝቦች ናችሁና።» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
54 : 9

وَمَا مَنَعَهُمۡ أَن تُقۡبَلَ مِنۡهُمۡ نَفَقَٰتُهُمۡ إِلَّآ أَنَّهُمۡ كَفَرُواْ بِٱللَّهِ وَبِرَسُولِهِۦ وَلَا يَأۡتُونَ ٱلصَّلَوٰةَ إِلَّا وَهُمۡ كُسَالَىٰ وَلَا يُنفِقُونَ إِلَّا وَهُمۡ كَٰرِهُونَ

54. ልግስናዎቻቸውን ከእነርሱ ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ያደረገው በአላህና በመልዕክተኛው የካዱ፤ ሶላትንም ስልቹዎች ሆነው እንጂ የማይሰግዱ፤ እነርሱም ጠይዎች ሆነው እንጂ የማይሰጡ ከመሆናቸው በስተቀር ሌላ ነገር አልከለከላቸዉም:: info
التفاسير: