Traduzione dei Significati del Sacro Corano - Traduzione Amarica - Accademia d'Africa

Numero di pagina:close

external-link copy
41 : 9

ٱنفِرُواْ خِفَافٗا وَثِقَالٗا وَجَٰهِدُواْ بِأَمۡوَٰلِكُمۡ وَأَنفُسِكُمۡ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِۚ ذَٰلِكُمۡ خَيۡرٞ لَّكُمۡ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ

41.(አማኞች ሆይ!) ቀላሎችም ከባዶችም ኾናችሁ ዝመቱ:: በአላህ መንገድ በገንዘቦቻችሁና በነፍሶቻችሁ ታገሉ :: ይህ ተግባር የምታውቁ ከሆናችሁ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
42 : 9

لَوۡ كَانَ عَرَضٗا قَرِيبٗا وَسَفَرٗا قَاصِدٗا لَّٱتَّبَعُوكَ وَلَٰكِنۢ بَعُدَتۡ عَلَيۡهِمُ ٱلشُّقَّةُۚ وَسَيَحۡلِفُونَ بِٱللَّهِ لَوِ ٱسۡتَطَعۡنَا لَخَرَجۡنَا مَعَكُمۡ يُهۡلِكُونَ أَنفُسَهُمۡ وَٱللَّهُ يَعۡلَمُ إِنَّهُمۡ لَكَٰذِبُونَ

42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጠራህባቸው ነገር ቅርብ ጥቅምና መካከለኛ ጉዞ በሆነ ኖሮ በተከተሉህ ነበር:: ግን በእነርሱ ላይ መንገዲቱ ራቀችባቸው:: «በቻልንም ኖሮ ከናንተ ጋር በወጣን ነበር» ሲሉ በአላህ ይምላሉ:: እራሳቸውን ለጥፋት (በውሸት) ይዳርጋሉ :: አላህ እነርሱ ውሸታሞች መሆናቸውን ያውቃል:: info
التفاسير:

external-link copy
43 : 9

عَفَا ٱللَّهُ عَنكَ لِمَ أَذِنتَ لَهُمۡ حَتَّىٰ يَتَبَيَّنَ لَكَ ٱلَّذِينَ صَدَقُواْ وَتَعۡلَمَ ٱلۡكَٰذِبِينَ

43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) አላህ ይቅር ብሎሀል:: እነዚያ እውነተኞቹ እስከሚገለጹልህና ውሸታሞቹን ለይተህ እስከምታውቅ ድረስ ለእነርሱ ከዘመቻ እንዲቀሩ ለምን ፈቀድክላቸው? info
التفاسير:

external-link copy
44 : 9

لَا يَسۡتَـٔۡذِنُكَ ٱلَّذِينَ يُؤۡمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِ أَن يُجَٰهِدُواْ بِأَمۡوَٰلِهِمۡ وَأَنفُسِهِمۡۗ وَٱللَّهُ عَلِيمُۢ بِٱلۡمُتَّقِينَ

44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑት በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው ከመታገላቸው ለመቅረት ፈቃድን አይጠይቁህም:: አላህም በትክክል የሚፈሩትን ሰዎች ሁሉ አዋቂ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
45 : 9

إِنَّمَا يَسۡتَـٔۡذِنُكَ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِ وَٱرۡتَابَتۡ قُلُوبُهُمۡ فَهُمۡ فِي رَيۡبِهِمۡ يَتَرَدَّدُونَ

45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ፈቃድ የሚጠይቁህ እነዚያ በአላህና በመጨረሻው ቀን የማያምኑት፤ ልቦቻቸው የተጠራጠሩት ሰዎች ብቻ ናቸው:: እነርሱም በጥርጣሬያቸው ውስጥ ይዋልላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
46 : 9

۞ وَلَوۡ أَرَادُواْ ٱلۡخُرُوجَ لَأَعَدُّواْ لَهُۥ عُدَّةٗ وَلَٰكِن كَرِهَ ٱللَّهُ ٱنۢبِعَاثَهُمۡ فَثَبَّطَهُمۡ وَقِيلَ ٱقۡعُدُواْ مَعَ ٱلۡقَٰعِدِينَ

46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ ዘመቻ መውጣት ባሰቡ ኖሮ ለእርሱ ዝግጅትን ባሰናዱ ነበር:: ግን አላህ ለመውጣት እንቅስቃሴያቸውን ጠላውና አሰነፋቸው:: «ከተቀማጮቹ ጋር ተቀመጡ።» ተባሉም:: info
التفاسير:

external-link copy
47 : 9

لَوۡ خَرَجُواْ فِيكُم مَّا زَادُوكُمۡ إِلَّا خَبَالٗا وَلَأَوۡضَعُواْ خِلَٰلَكُمۡ يَبۡغُونَكُمُ ٱلۡفِتۡنَةَ وَفِيكُمۡ سَمَّٰعُونَ لَهُمۡۗ وَٱللَّهُ عَلِيمُۢ بِٱلظَّٰلِمِينَ

47. (አማኞች ሆይ!) ከናንተ ጋር በወጡ ኖሮ ጥፋትን እንጂ አይጨምሩላችሁም ነበር:: ሁከትንም የሚፈልጉላችሁ ሲሆኑ በመካከላችሁ ነገርን በማሳበቅ ይቻኮሉ ነበር:: በእናንተ ውስጥ ለእነርሱ አዳማጮች አሏቸው:: አላህም በዳዮችን አዋቂ ነው:: info
التفاسير: