Traduzione dei Significati del Sacro Corano - Traduzione Amarica - Muhammed Sadeq

Numero di pagina:close

external-link copy
106 : 4

وَٱسۡتَغۡفِرِ ٱللَّهَۖ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ غَفُورٗا رَّحِيمٗا

አላህንም ምሕረትን ለምን፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
107 : 4

وَلَا تُجَٰدِلۡ عَنِ ٱلَّذِينَ يَخۡتَانُونَ أَنفُسَهُمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ خَوَّانًا أَثِيمٗا

ከእነዚያም ነፍሶቻቸውን ከሚበድሉት ላይ አትከራከር፡፡ አላህ ከዳተኛ ኃጢአተኛ የኾነን ሰው አይወድምና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
108 : 4

يَسۡتَخۡفُونَ مِنَ ٱلنَّاسِ وَلَا يَسۡتَخۡفُونَ مِنَ ٱللَّهِ وَهُوَ مَعَهُمۡ إِذۡ يُبَيِّتُونَ مَا لَا يَرۡضَىٰ مِنَ ٱلۡقَوۡلِۚ وَكَانَ ٱللَّهُ بِمَا يَعۡمَلُونَ مُحِيطًا

ከሰው ይደበቃሉ፡፡ ከአላህ አይደበቁም እርሱ (በዕውቀቱ) ከእነሱ ጋር ሲኾን ከንግግር የማይወደውን ነገር (በልቦቻቸው) በሚያሳድሩ ጊዜ ፡፡ አላህም በሚሠሩት ሁሉ (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
109 : 4

هَٰٓأَنتُمۡ هَٰٓؤُلَآءِ جَٰدَلۡتُمۡ عَنۡهُمۡ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا فَمَن يُجَٰدِلُ ٱللَّهَ عَنۡهُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ أَم مَّن يَكُونُ عَلَيۡهِمۡ وَكِيلٗا

እነሆ እናንተ እነዚያ በቅርቢቱ ሕይወት ከነሱ የተከራከራችሁ ናችሁ፡፡ በትንሣኤ ቀን አላህን ስለእነሱ የሚከራከር ማን ነው ወይስ ለእነሱ ኃላፊና መመኪያ የሚኾን ማን ነው info
التفاسير:

external-link copy
110 : 4

وَمَن يَعۡمَلۡ سُوٓءًا أَوۡ يَظۡلِمۡ نَفۡسَهُۥ ثُمَّ يَسۡتَغۡفِرِ ٱللَّهَ يَجِدِ ٱللَّهَ غَفُورٗا رَّحِيمٗا

መጥፎም የሚሠራ ሰው ወይም ነፍሱን የሚበድል ከዚያም (ተጸጽቶ) አላህን ምሕረት የሚለምን አላህን መሓሪ አዛኝ ኾኖ ያገኘዋል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
111 : 4

وَمَن يَكۡسِبۡ إِثۡمٗا فَإِنَّمَا يَكۡسِبُهُۥ عَلَىٰ نَفۡسِهِۦۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمٗا

ኀጢአትንም የሚሠራ ሰው የሚሠራው ጥፋት በራሱ ላይ ነው፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፤ info
التفاسير:

external-link copy
112 : 4

وَمَن يَكۡسِبۡ خَطِيٓـَٔةً أَوۡ إِثۡمٗا ثُمَّ يَرۡمِ بِهِۦ بَرِيٓـٔٗا فَقَدِ ٱحۡتَمَلَ بُهۡتَٰنٗا وَإِثۡمٗا مُّبِينٗا

ኀጢአትን ወይም አበሳን የሚሠራም ሰው ከዚያም በእርሱ ንጹሕን ሰው የሚሰድብ ቅጥፈትንና ግልጽ አበሳን በቁርጥ ተሸከመ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
113 : 4

وَلَوۡلَا فَضۡلُ ٱللَّهِ عَلَيۡكَ وَرَحۡمَتُهُۥ لَهَمَّت طَّآئِفَةٞ مِّنۡهُمۡ أَن يُضِلُّوكَ وَمَا يُضِلُّونَ إِلَّآ أَنفُسَهُمۡۖ وَمَا يَضُرُّونَكَ مِن شَيۡءٖۚ وَأَنزَلَ ٱللَّهُ عَلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡحِكۡمَةَ وَعَلَّمَكَ مَا لَمۡ تَكُن تَعۡلَمُۚ وَكَانَ فَضۡلُ ٱللَّهِ عَلَيۡكَ عَظِيمٗا

የአላህም ችሮታና እዝነቱ ባንተ ላይ ባልነበረ ኖሮ ከእነሱ የኾኑ ጭፍሮች ሊያሳስቱህ ባሰቡ ነበር፡፡ ነፍሶቻቸውንም እንጅ ሌላን አያሳስቱም፡፡ በምንም አይጐዱህም፡፡ አላህም በአንተ ላይ መጽሐፍንና ጥበብን አወረደ፡፡ የማታውቀውንም ሁሉ አስተማረህ፡፡ የአላህም ችሮታ በአንተ ላይ ታላቅ ነው፡፡ info
التفاسير: