Traduzione dei Significati del Sacro Corano - Traduzione Amarica - Muhammed Sadeq

Numero di pagina:close

external-link copy
102 : 4

وَإِذَا كُنتَ فِيهِمۡ فَأَقَمۡتَ لَهُمُ ٱلصَّلَوٰةَ فَلۡتَقُمۡ طَآئِفَةٞ مِّنۡهُم مَّعَكَ وَلۡيَأۡخُذُوٓاْ أَسۡلِحَتَهُمۡۖ فَإِذَا سَجَدُواْ فَلۡيَكُونُواْ مِن وَرَآئِكُمۡ وَلۡتَأۡتِ طَآئِفَةٌ أُخۡرَىٰ لَمۡ يُصَلُّواْ فَلۡيُصَلُّواْ مَعَكَ وَلۡيَأۡخُذُواْ حِذۡرَهُمۡ وَأَسۡلِحَتَهُمۡۗ وَدَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَوۡ تَغۡفُلُونَ عَنۡ أَسۡلِحَتِكُمۡ وَأَمۡتِعَتِكُمۡ فَيَمِيلُونَ عَلَيۡكُم مَّيۡلَةٗ وَٰحِدَةٗۚ وَلَا جُنَاحَ عَلَيۡكُمۡ إِن كَانَ بِكُمۡ أَذٗى مِّن مَّطَرٍ أَوۡ كُنتُم مَّرۡضَىٰٓ أَن تَضَعُوٓاْ أَسۡلِحَتَكُمۡۖ وَخُذُواْ حِذۡرَكُمۡۗ إِنَّ ٱللَّهَ أَعَدَّ لِلۡكَٰفِرِينَ عَذَابٗا مُّهِينٗا

በውስጣቸውም በኾንክና ሶላትን ለእነርሱ ባስገደድካቸው ጊዜ ከእነሱ አንዲት ጭፍራ ካንተ ጋር ትቁም፡፡ መሣሪያዎቻቸውንም ይያዙ፡፡ በግንባራቸውም በተደፉ ጊዜ ከስተኋላችሁ ይኹኑ፡፡ (እነዚህ ይኺዱና) ያልሰገዱትም ሌሎቹ ጭፍሮች ይምጡ፡፡ ከአንተም ጋር ይስገዱ፡፡ ጥንቃቄያቸውንና መሣሪያዎቻቸውንም ይያዙ፡፡ እነዚያ የካዱት ከመሣሪያዎቻችሁና ከጓዞቻችሁ ብትዘነጉና በእናንተ ላይ አንዲትን መዘንበል ቢዘነበሉ ተመኙ፡፡ ከዝናብም የኾነ ችግር በእናንተ ቢኖር ወይም ሕመምተኞች ብትኾኑ መሣሪያዎቻችሁን ብታስቀምጡ በናንተ ላይ ኀጢአት የለም፡፡ ጥንቃቄያችሁንም ያዙ፡፡ አላህ ለከሓዲዎች አዋራጅን ቅጣት አዘጋጀ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
103 : 4

فَإِذَا قَضَيۡتُمُ ٱلصَّلَوٰةَ فَٱذۡكُرُواْ ٱللَّهَ قِيَٰمٗا وَقُعُودٗا وَعَلَىٰ جُنُوبِكُمۡۚ فَإِذَا ٱطۡمَأۡنَنتُمۡ فَأَقِيمُواْ ٱلصَّلَوٰةَۚ إِنَّ ٱلصَّلَوٰةَ كَانَتۡ عَلَى ٱلۡمُؤۡمِنِينَ كِتَٰبٗا مَّوۡقُوتٗا

ሶላትንም በፈጸማችሁ ጊዜ ቆማችሁም ተቀምጣችሁም በጎኖቻችሁም ላይ ተጋድማችሁ አላህን አውሱ፡፡ በረጋችሁም ጊዜ ሶላትን (አሟልታችሁ) ስገዱ፡፡ ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
104 : 4

وَلَا تَهِنُواْ فِي ٱبۡتِغَآءِ ٱلۡقَوۡمِۖ إِن تَكُونُواْ تَأۡلَمُونَ فَإِنَّهُمۡ يَأۡلَمُونَ كَمَا تَأۡلَمُونَۖ وَتَرۡجُونَ مِنَ ٱللَّهِ مَا لَا يَرۡجُونَۗ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا

ሰዎቹንም በመፈለግ አትስነፉ፡፡ (ስትቆስሉ) የምትታመሙ ብትኾኑ እናንተ እንደምትታመሙ እነሱም ይታመማሉ፡፡ የማይከጅሉትንም ከአላህ ትከጅላላችሁ፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
105 : 4

إِنَّآ أَنزَلۡنَآ إِلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ بِٱلۡحَقِّ لِتَحۡكُمَ بَيۡنَ ٱلنَّاسِ بِمَآ أَرَىٰكَ ٱللَّهُۚ وَلَا تَكُن لِّلۡخَآئِنِينَ خَصِيمٗا

እኛ በሰዎች መካከል አላህ ባሳወቀህ ልትፈርድ ወደ አንተ መጽሐፉን በእውነት አወረድን፡፡ ለከዳተኞችም ተከራካሪ አትኹን፡፡ info
التفاسير: