Fassarar Ma'anonin Alqura'ni - Fassarar Amhariyanci - Akadamar Afirka

Lambar shafi:close

external-link copy
87 : 9

رَضُواْ بِأَن يَكُونُواْ مَعَ ٱلۡخَوَالِفِ وَطُبِعَ عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ فَهُمۡ لَا يَفۡقَهُونَ

87. በቤት ከሚቀሩት ወገኖች ጋር መሆናቸውን ወደዱ:: በልቦቻቸዉም ላይ (ዝገት) ታተመባቸው:: ስለዚህ እነርሱ አያውቁም:: info
التفاسير:

external-link copy
88 : 9

لَٰكِنِ ٱلرَّسُولُ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مَعَهُۥ جَٰهَدُواْ بِأَمۡوَٰلِهِمۡ وَأَنفُسِهِمۡۚ وَأُوْلَٰٓئِكَ لَهُمُ ٱلۡخَيۡرَٰتُۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ

88. ግን መልዕክተኛውና ከእርሱ ጋር ያመኑት ሰዎች በገንዘቦቻቸዉም በነፍሶቻቸዉም ታገሉ:: እነዚያም መልካሞች ሁሉ ለእነርሱ ብቻ የተዘጋጁ ናቸው:: እነዚያም እነርሱ ምኞታቸውን ያገኙ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
89 : 9

أَعَدَّ ٱللَّهُ لَهُمۡ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَاۚ ذَٰلِكَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ

89. አላህ ለእነርሱ በሥራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶችን በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ አዘጋጅቶላቸዋል:: ይህ ታላቅ ማግኜት (እድል) ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
90 : 9

وَجَآءَ ٱلۡمُعَذِّرُونَ مِنَ ٱلۡأَعۡرَابِ لِيُؤۡذَنَ لَهُمۡ وَقَعَدَ ٱلَّذِينَ كَذَبُواْ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥۚ سَيُصِيبُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِنۡهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ

90. ከአረብ ዘላኖች መካከል ይቅርታ ፈላጊዎቹ እንዲፈቀድላቸው መጡ:: እነዚያ አላህንና መልዕክተኛውን ያስተባበሉት ግን ተቀመጡ:: እነዚያን በአላህ የካዱት ሰዎች አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ይነካቸዋል (ያገኛቸዋል):: info
التفاسير:

external-link copy
91 : 9

لَّيۡسَ عَلَى ٱلضُّعَفَآءِ وَلَا عَلَى ٱلۡمَرۡضَىٰ وَلَا عَلَى ٱلَّذِينَ لَا يَجِدُونَ مَا يُنفِقُونَ حَرَجٌ إِذَا نَصَحُواْ لِلَّهِ وَرَسُولِهِۦۚ مَا عَلَى ٱلۡمُحۡسِنِينَ مِن سَبِيلٖۚ وَٱللَّهُ غَفُورٞ رَّحِيمٞ

91. በደካሞች ላይ፤ በበሽተኞች ላይ፤ በእነዚያም ለስንቅና ለትጥቅ የሚያወጡት ገንዘብ በማያገኙት ላይ ለአላህና ለመልዕክተኛው ፍጹም ታዛዦች ከሆኑ ወደ ዘመቻ ባይወጡም ኃጢአት የለባቸዉም:: በበጎ አድራጊዎች ላይ ምንም የመወቀሻ መንገድ የለባቸዉም:: አላህ መሓሪና አዛኝ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
92 : 9

وَلَا عَلَى ٱلَّذِينَ إِذَا مَآ أَتَوۡكَ لِتَحۡمِلَهُمۡ قُلۡتَ لَآ أَجِدُ مَآ أَحۡمِلُكُمۡ عَلَيۡهِ تَوَلَّواْ وَّأَعۡيُنُهُمۡ تَفِيضُ مِنَ ٱلدَّمۡعِ حَزَنًا أَلَّا يَجِدُواْ مَا يُنفِقُونَ

92. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በነዚያም መጓጓዣያ እንድትሰጣቸው ፈልገው ወደ አንተ በመጡ ጊዜ «እናንተን የምጭንበት (አጋሰስ) አላገኝም።» ያልካቸው ስትሆን የሚያወጡት ገንዘብ ባለማግኘታቸው ለማዘናቸው ዓይኖቻቸው እንባን እያፈሰሱ በዞሩት ላይ ምንም ወቀሳ የለባቸዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
93 : 9

۞ إِنَّمَا ٱلسَّبِيلُ عَلَى ٱلَّذِينَ يَسۡتَـٔۡذِنُونَكَ وَهُمۡ أَغۡنِيَآءُۚ رَضُواْ بِأَن يَكُونُواْ مَعَ ٱلۡخَوَالِفِ وَطَبَعَ ٱللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ فَهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ

93. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሚወቀሱት እነዚያ ባለጸጋዎች ሆነው ሳሉ ለመቅረት ፈቃድ በሚጠይቁህ ሰዎች ላይ ብቻ ናቸው:: ከቀሪዎቹ ጋር መሆናቸውን ወደዱ:: አላህ በልቦቻቸው ላይ አተመባቸው:: ስለዚህ እነርሱ አያውቁም:: info
التفاسير: