Fassarar Ma'anonin Alqura'ni - Fassarar Amhariyanci - Akadamar Afirka

Lambar shafi: 164:151 close

external-link copy
121 : 7

قَالُوٓاْ ءَامَنَّا بِرَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

121. አሉም: «በዓለማት ጌታ አመንን። info
التفاسير:

external-link copy
122 : 7

رَبِّ مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ

122. «በሙሳና በሃሩን ጌታ።» info
التفاسير:

external-link copy
123 : 7

قَالَ فِرۡعَوۡنُ ءَامَنتُم بِهِۦ قَبۡلَ أَنۡ ءَاذَنَ لَكُمۡۖ إِنَّ هَٰذَا لَمَكۡرٞ مَّكَرۡتُمُوهُ فِي ٱلۡمَدِينَةِ لِتُخۡرِجُواْ مِنۡهَآ أَهۡلَهَاۖ فَسَوۡفَ تَعۡلَمُونَ

123. (ፊርዓውንም) አለ፡ «እኔ ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት በእርሱ አመናችሁን? ይህ በከተማይቱ ውስጥ ሰውን ከእርሷ ለማውጣት የተስማማችሁበት ተንኮል ነው:: ወደፊት የሚደርሰባችሁን ታውቃላችሁ። info
التفاسير:

external-link copy
124 : 7

لَأُقَطِّعَنَّ أَيۡدِيَكُمۡ وَأَرۡجُلَكُم مِّنۡ خِلَٰفٖ ثُمَّ لَأُصَلِّبَنَّكُمۡ أَجۡمَعِينَ

124. «እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን በማፈራረቅ በእርግጥ እቆራርጣለሁ:: ከዚያም ሁላችሁንም በእንጨት ላይ እስቅላችኋለሁ።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
125 : 7

قَالُوٓاْ إِنَّآ إِلَىٰ رَبِّنَا مُنقَلِبُونَ

125. እነርሱም አሉ: «እኛ ወደ ጌታችን ተመላሾች ነን። info
التفاسير:

external-link copy
126 : 7

وَمَا تَنقِمُ مِنَّآ إِلَّآ أَنۡ ءَامَنَّا بِـَٔايَٰتِ رَبِّنَا لَمَّا جَآءَتۡنَاۚ رَبَّنَآ أَفۡرِغۡ عَلَيۡنَا صَبۡرٗا وَتَوَفَّنَا مُسۡلِمِينَ

126. «የጌታችን ተዓምራት በመጡልን ጊዜ ከማመናችን በስተቀር ከእኛ አትጠላም:: ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አፍስስ:: ሙስሊሞችም ሆነን ግደለን።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
127 : 7

وَقَالَ ٱلۡمَلَأُ مِن قَوۡمِ فِرۡعَوۡنَ أَتَذَرُ مُوسَىٰ وَقَوۡمَهُۥ لِيُفۡسِدُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَيَذَرَكَ وَءَالِهَتَكَۚ قَالَ سَنُقَتِّلُ أَبۡنَآءَهُمۡ وَنَسۡتَحۡيِۦ نِسَآءَهُمۡ وَإِنَّا فَوۡقَهُمۡ قَٰهِرُونَ

127. ከፈርዖን ሰዎች ቅምጥሎቹ ለፈርዖን: «ሙሳንና ሰዎችን በምድር ላይ እንዲያበላሹና ሙሳም አንተንና አምልኮትህን እንዲተው ትተዋቸዋለህን?» አሉ:: እሱም «ወንዶች ልጆቻቸውን እንገድላለን:: ሴቶቻቸውንም እናስቀራለን:: እኛም ከበላያቸው ነን አሸናፊዎች ነን» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
128 : 7

قَالَ مُوسَىٰ لِقَوۡمِهِ ٱسۡتَعِينُواْ بِٱللَّهِ وَٱصۡبِرُوٓاْۖ إِنَّ ٱلۡأَرۡضَ لِلَّهِ يُورِثُهَا مَن يَشَآءُ مِنۡ عِبَادِهِۦۖ وَٱلۡعَٰقِبَةُ لِلۡمُتَّقِينَ

128. ሙሳም ለሰዎቹ፡- «በአላህ ታገዙ፤ ታገሱም። ምድር ለአላህ ናትና ከባሮቹ መካከል ለሚሻው ያወርሳታል:: ምስጉኗም ፍጻሜ ለጥንቁቆቹ ናት።» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
129 : 7

قَالُوٓاْ أُوذِينَا مِن قَبۡلِ أَن تَأۡتِيَنَا وَمِنۢ بَعۡدِ مَا جِئۡتَنَاۚ قَالَ عَسَىٰ رَبُّكُمۡ أَن يُهۡلِكَ عَدُوَّكُمۡ وَيَسۡتَخۡلِفَكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَيَنظُرَ كَيۡفَ تَعۡمَلُونَ

129. ህዝቦቹም «አንተ ከመምጣትህ በፊትም ሆነ ከመጣህልን በኋላ ተሰቃየን።» አሉት:: ሙሳም «ጌታችሁ ጠላቶቻችሁን ሊያጠፋና እንዴት እንደምትሰሩ ይመለከት ዘንድ በምድር ላይ ሊተካችሁ ይከጀላል።» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
130 : 7

وَلَقَدۡ أَخَذۡنَآ ءَالَ فِرۡعَوۡنَ بِٱلسِّنِينَ وَنَقۡصٖ مِّنَ ٱلثَّمَرَٰتِ لَعَلَّهُمۡ يَذَّكَّرُونَ

130. የፈርዖንንም ቤተሰቦች እንዲገሰጹ በድርቅና የፍራፍሬ ምርታቸውን በመቀነስ በእርግጥ ቀጣናቸው:: info
التفاسير: