Fassarar Ma'anonin Alqura'ni - Fassarar Amhariyanci - Akadamar Afirka

አል ቀለም

external-link copy
1 : 68

نٓۚ وَٱلۡقَلَمِ وَمَا يَسۡطُرُونَ

1. ኑን፤ በብዕር እና በዚያም በሱ በሚጽፉት ሁሉ እምላለሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 68

مَآ أَنتَ بِنِعۡمَةِ رَبِّكَ بِمَجۡنُونٖ

2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ በጌታህ ጸጋ ምክኒያት ዕብድ አይደለህም:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 68

وَإِنَّ لَكَ لَأَجۡرًا غَيۡرَ مَمۡنُونٖ

3. ላንተም ከጌታህ የማይቋረጥ ምንዳ (የልፋት ዋጋ) በእርግጥ አለህ:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 68

وَإِنَّكَ لَعَلَىٰ خُلُقٍ عَظِيمٖ

4. አንተም በታላቅ ጸባይ ላይ ነህ:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 68

فَسَتُبۡصِرُ وَيُبۡصِرُونَ

5. ወደ ፊት አንተም ታያለህ፤ እነርሱም ያያሉ፤ info
التفاسير:

external-link copy
6 : 68

بِأَييِّكُمُ ٱلۡمَفۡتُونُ

6. ዕብደት በማንኛችሁ እንዳለ (እብዱ ማን እንደሆነ):: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 68

إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعۡلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِۦ وَهُوَ أَعۡلَمُ بِٱلۡمُهۡتَدِينَ

7. ጌታህ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው አዋቂ ነው። ወደ ቀናው መንገድ ተመሪዎችንም አዋቂ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 68

فَلَا تُطِعِ ٱلۡمُكَذِّبِينَ

8. ስለዚህ ለአስተባባዩች (ሁሉ) አትታዘዝ:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 68

وَدُّواْ لَوۡ تُدۡهِنُ فَيُدۡهِنُونَ

9. (አስተባባዩች) ብትመሳሰላቸውና እነርሱም ቢመሳሰሉህ ተመኙ:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 68

وَلَا تُطِعۡ كُلَّ حَلَّافٖ مَّهِينٍ

10. መሓለኛን ወራዳን ሁሉ አትታዘዝ። info
التفاسير:

external-link copy
11 : 68

هَمَّازٖ مَّشَّآءِۭ بِنَمِيمٖ

11. ሰውን አነዋሪን፤ ነገር አሳባቂን፤ info
التفاسير:

external-link copy
12 : 68

مَّنَّاعٖ لِّلۡخَيۡرِ مُعۡتَدٍ أَثِيمٍ

12.ለበጎ ነገር በጣም ከልካይን፤ ወሰን አላፊን፤ ኃጢአተኛንም፤ info
التفاسير:

external-link copy
13 : 68

عُتُلِّۭ بَعۡدَ ذَٰلِكَ زَنِيمٍ

13. ልበ ደረቅን ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ የዝሙት ልጅ ዲቃላን (አትታዘዝ):: info
التفاسير:

external-link copy
14 : 68

أَن كَانَ ذَا مَالٖ وَبَنِينَ

14. የገንዘብና የልጆች ባለቤት በመሆኑ (ያስተባብላል)። info
التفاسير:

external-link copy
15 : 68

إِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِ ءَايَٰتُنَا قَالَ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ

15. በእርሱ ላይ እንቀፆቻችን በሚነበቡ ጊዜ «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው» ይላል:: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 68

سَنَسِمُهُۥ عَلَى ٱلۡخُرۡطُومِ

16. በአፍንጫው ላይ በእርግጥ (የሚነወርበት) ምልክትን እናደርግበታለን:: info
التفاسير: