Fassarar Ma'anonin Alqura'ni - Fassarar Amhariyanci - Akadamar Afirka

አል ሙልክ

external-link copy
1 : 67

تَبَٰرَكَ ٱلَّذِي بِيَدِهِ ٱلۡمُلۡكُ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٌ

1. ያ ንግስና በእጁ የሆነው አምላክ ችሮታው በዛ:: እርሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 67

ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلۡمَوۡتَ وَٱلۡحَيَوٰةَ لِيَبۡلُوَكُمۡ أَيُّكُمۡ أَحۡسَنُ عَمَلٗاۚ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡغَفُورُ

2. ያ የየትኛችሁ ስራ ይበልጥ ያማረ መሆኑን ሊሞክራችሁ ሞትንና ህይወትን የፈጠረ ነው:: እርሱም አሸናፊና መሀሪ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 67

ٱلَّذِي خَلَقَ سَبۡعَ سَمَٰوَٰتٖ طِبَاقٗاۖ مَّا تَرَىٰ فِي خَلۡقِ ٱلرَّحۡمَٰنِ مِن تَفَٰوُتٖۖ فَٱرۡجِعِ ٱلۡبَصَرَ هَلۡ تَرَىٰ مِن فُطُورٖ

3. ያ ሰባቱን ሰማያት የተነባበሩ ሆነው የፈጠረ ነው:: በአል ረህማን አፈጣጠርም ውስጥ ምንም ቅንጣት ያህል መዛነፍን (መቃረንና መበላሸት) አይታይም:: ዓይንህንም መልስ:: ከስንጥቆች አንዳችን ታያለህን? info
التفاسير:

external-link copy
4 : 67

ثُمَّ ٱرۡجِعِ ٱلۡبَصَرَ كَرَّتَيۡنِ يَنقَلِبۡ إِلَيۡكَ ٱلۡبَصَرُ خَاسِئٗا وَهُوَ حَسِيرٞ

4. ከዚያም ዓይንህን መላልስ:: ዓይንህ ተዋርዶ (ተናንሶ)፤ እርሱም የደከመ ሆኖ ወደ አንተ ይመለሳል:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 67

وَلَقَدۡ زَيَّنَّا ٱلسَّمَآءَ ٱلدُّنۡيَا بِمَصَٰبِيحَ وَجَعَلۡنَٰهَا رُجُومٗا لِّلشَّيَٰطِينِۖ وَأَعۡتَدۡنَا لَهُمۡ عَذَابَ ٱلسَّعِيرِ

5. ቅርቢቱን ሰማይም በእርግጥ በመብራቶች (በከዋክብት) አጌጥናት:: ለሰይጣናትም መቀጥቀጫዎች አደረግናት፤ ለእነርሱም ተንቀልቃይ የእሳትን ቅጣት አዘጋጀንላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 67

وَلِلَّذِينَ كَفَرُواْ بِرَبِّهِمۡ عَذَابُ جَهَنَّمَۖ وَبِئۡسَ ٱلۡمَصِيرُ

6. ለእነዚያም በጌታቸው ለካዱት የገሀነም ቅጣት አላቸው:: መመላሻይቱም ገሀነም ከፋች! info
التفاسير:

external-link copy
7 : 67

إِذَآ أُلۡقُواْ فِيهَا سَمِعُواْ لَهَا شَهِيقٗا وَهِيَ تَفُورُ

7. በውስጧ በተጣሉ ጊዜ እርሷ የምትፈላ ስትሆን ከእርሷ እንደ (አህያ) ማናፋትን ይሰማሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 67

تَكَادُ تَمَيَّزُ مِنَ ٱلۡغَيۡظِۖ كُلَّمَآ أُلۡقِيَ فِيهَا فَوۡجٞ سَأَلَهُمۡ خَزَنَتُهَآ أَلَمۡ يَأۡتِكُمۡ نَذِيرٞ

8. ከቁጭቷ የተነሳ ልትቆራረጥ ትቀርባለች:: በውስጧ ቡድኖች በተጣሉ ቁጥር «ዘበኞቿ (ስለዚህ ቀን) አስፈራሪ (ነብይ) አልመጣላችሁም ነበርን?» በማለት ይጠይቋቸዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 67

قَالُواْ بَلَىٰ قَدۡ جَآءَنَا نَذِيرٞ فَكَذَّبۡنَا وَقُلۡنَا مَا نَزَّلَ ٱللَّهُ مِن شَيۡءٍ إِنۡ أَنتُمۡ إِلَّا فِي ضَلَٰلٖ كَبِيرٖ

9. «አይደለም በእርግጥ አስፈራሪ መጥቶልናል:: አስተባበልንም:: አላህም ምንንም አላወረደም:: እናንተ አውርዷል ስትሉ፤ በትልቅ ስህተት ውስጥ እንጂ አይደላችሁም አልን» ይላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 67

وَقَالُواْ لَوۡ كُنَّا نَسۡمَعُ أَوۡ نَعۡقِلُ مَا كُنَّا فِيٓ أَصۡحَٰبِ ٱلسَّعِيرِ

10. «የምንሰማ ወይም የምናስብ በነበርን ኖሮ የእሳት ጓዶች ባልሆን ነበር» ይላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 67

فَٱعۡتَرَفُواْ بِذَنۢبِهِمۡ فَسُحۡقٗا لِّأَصۡحَٰبِ ٱلسَّعِيرِ

11. በኃጢአታቸዉም ያምናሉ:: ለእሳት ጓዶችም (ከእዝነት) መራቅ ተገባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 67

إِنَّ ٱلَّذِينَ يَخۡشَوۡنَ رَبَّهُم بِٱلۡغَيۡبِ لَهُم مَّغۡفِرَةٞ وَأَجۡرٞ كَبِيرٞ

12. እነዚያ ጌታቸውን በሩቁ የሚፈሩ ለእነርሱ ምህረትንና ታላቅ ምንዳ አለላቸው:: info
التفاسير: