Fassarar Ma'anonin Alqura'ni - Fassarar Amhariyanci - Akadamar Afirka

external-link copy
4 : 60

قَدۡ كَانَتۡ لَكُمۡ أُسۡوَةٌ حَسَنَةٞ فِيٓ إِبۡرَٰهِيمَ وَٱلَّذِينَ مَعَهُۥٓ إِذۡ قَالُواْ لِقَوۡمِهِمۡ إِنَّا بُرَءَٰٓؤُاْ مِنكُمۡ وَمِمَّا تَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ كَفَرۡنَا بِكُمۡ وَبَدَا بَيۡنَنَا وَبَيۡنَكُمُ ٱلۡعَدَٰوَةُ وَٱلۡبَغۡضَآءُ أَبَدًا حَتَّىٰ تُؤۡمِنُواْ بِٱللَّهِ وَحۡدَهُۥٓ إِلَّا قَوۡلَ إِبۡرَٰهِيمَ لِأَبِيهِ لَأَسۡتَغۡفِرَنَّ لَكَ وَمَآ أَمۡلِكُ لَكَ مِنَ ٱللَّهِ مِن شَيۡءٖۖ رَّبَّنَا عَلَيۡكَ تَوَكَّلۡنَا وَإِلَيۡكَ أَنَبۡنَا وَإِلَيۡكَ ٱلۡمَصِيرُ

4. ኢብራሂምና እነዚያ ከእርሱ ጋር አብረው የነበሩት አማኞች ለእናንተ መልካም አርአያ ናቸው:: ይኸዉም ለህዝቦቻቸው «እኛ ከናንተና ከዚያ ከአላህ ሌላ ከምትገዙት ጣዖታት ሁሉ ንጹሆች ነን:: በእናንተም ካድን:: በአላህ አንድነት እስከምታምኑ ድረስ በእኛና በእናንተ መካከል ጠብና ጥላቻ ዘወትር ተገለጸ::» ባሉ ጊዜ ኢብራሂም ለአባቱ፡- «ላንተ ከአላህ ቅጣት ምንም የማልጠቅምህ (የማላድንህ) ስሆን ላንተ በእርግጥ ምህረትን እለምንልሃለሁ::» ማለቱ ብቻ ሲቀር «ጌታችን ሆይ ባንተ ላይ ተመካን ወደ አንተም ተመለስን መመለሻም ወደ አንተ ብቻ ነው::» (ባለው ተከተሉ።) info
التفاسير: