Fassarar Ma'anonin Alqura'ni - Fassarar Amhariyanci - Akadamar Afirka

አል-አንዓም

external-link copy
1 : 6

ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ وَجَعَلَ ٱلظُّلُمَٰتِ وَٱلنُّورَۖ ثُمَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِرَبِّهِمۡ يَعۡدِلُونَ

1.ምስጋና ሁሉ ለዚያ ሰማያትንና ምድርን ለፈጠረ ጨለማዎችንና ብርሃንን ላደረገው ለአላህ የተገባ ነው:: ከዚያም እነዚያ በእርሱ የካዱ ሁሉ ጣዖታትን ከጌታቸው ጋር ያስተካክላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 6

هُوَ ٱلَّذِي خَلَقَكُم مِّن طِينٖ ثُمَّ قَضَىٰٓ أَجَلٗاۖ وَأَجَلٞ مُّسَمًّى عِندَهُۥۖ ثُمَّ أَنتُمۡ تَمۡتَرُونَ

2. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ ያ ከጭቃ የፈጠራችሁ ከዚያም የሞት ጊዜን የወሰነ ነው:: እርሱም ዘንድ ለትንሳኤ የተወሰነ ጊዜ አለ:: ከዚያም እናንተ በመቀስቀሳችሁ ትጠራጠራላችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
3 : 6

وَهُوَ ٱللَّهُ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَفِي ٱلۡأَرۡضِ يَعۡلَمُ سِرَّكُمۡ وَجَهۡرَكُمۡ وَيَعۡلَمُ مَا تَكۡسِبُونَ

3. እርሱም ያ በሰማያትም በምድርም ሊገዙት የሚገባው አላህ ነው:: (ሰዎች ሆይ!) ሚስጥራችሁንም ሆነ ግልፃችሁን ጠንቅቆ ያውቃል። የምትሰሩትን ሁሉ ጠንቅቆ ያውቃል:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 6

وَمَا تَأۡتِيهِم مِّنۡ ءَايَةٖ مِّنۡ ءَايَٰتِ رَبِّهِمۡ إِلَّا كَانُواْ عَنۡهَا مُعۡرِضِينَ

⒋ ከጌታቸው አናቅጽ አንዱም አይመጣላቸዉም ከእርሱ የሚሸሹ ቢሆኑ እንጂ:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 6

فَقَدۡ كَذَّبُواْ بِٱلۡحَقِّ لَمَّا جَآءَهُمۡ فَسَوۡفَ يَأۡتِيهِمۡ أَنۢبَٰٓؤُاْ مَا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ

5. ቁርኣን በመጣላቸው ጊዜም በእርግጥ አስተባበሉ:: ግን የእዚያ በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ነገር ዜናዎች ቅጣት ይመጣባቸዋል። info
التفاسير:

external-link copy
6 : 6

أَلَمۡ يَرَوۡاْ كَمۡ أَهۡلَكۡنَا مِن قَبۡلِهِم مِّن قَرۡنٖ مَّكَّنَّٰهُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ مَا لَمۡ نُمَكِّن لَّكُمۡ وَأَرۡسَلۡنَا ٱلسَّمَآءَ عَلَيۡهِم مِّدۡرَارٗا وَجَعَلۡنَا ٱلۡأَنۡهَٰرَ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهِمۡ فَأَهۡلَكۡنَٰهُم بِذُنُوبِهِمۡ وَأَنشَأۡنَا مِنۢ بَعۡدِهِمۡ قَرۡنًا ءَاخَرِينَ

6. ከበፊታቸው ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች መካከል ብዙዎቹን ማጥፋታችንን አላዩምን? ለእናንተ ያላስመቸነውን ለእነርሱ በምድር ውስጥ አስመቸናቸው:: በእነርሱም ላይ ዝናብን የተከታተለ ሲሆን ላክን:: ወንዞችንም በስራቸው እንዲፈሱ አደረግን:: በኃጢአቶቻቸዉም ምክንያት አጠፋናቸው:: ከኋላቸዉም ሌሎችን ሰዎች በየክፍለ ዘመኑ አስገኘን:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 6

وَلَوۡ نَزَّلۡنَا عَلَيۡكَ كِتَٰبٗا فِي قِرۡطَاسٖ فَلَمَسُوهُ بِأَيۡدِيهِمۡ لَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا سِحۡرٞ مُّبِينٞ

7. በእነርሱ ላይ በወረቀት የተፃፈን መጽሐፍ ባወረድንና በእጆቻቸው በነኩት ኖሮ እነዚያ ከሓዲያን «ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም።» ባሉ ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 6

وَقَالُواْ لَوۡلَآ أُنزِلَ عَلَيۡهِ مَلَكٞۖ وَلَوۡ أَنزَلۡنَا مَلَكٗا لَّقُضِيَ ٱلۡأَمۡرُ ثُمَّ لَا يُنظَرُونَ

8. «በእርሱ (በሙሐመድ) ላይ መልአክ ለምን አይወረድለትም?» አሉ። ነገር ግን መላዕክን ባወረድንለትና (ባያምኑ ኖሮ) የጥፋታቸው ነገር በተፈረደ ነበር:: ከዚያም አይቆዩም ነበር:: info
التفاسير: