Fassarar Ma'anonin Alqura'ni - Fassarar Amhariyanci - Akadamar Afirka

Lambar shafi: 471:467 close

external-link copy
41 : 40

۞ وَيَٰقَوۡمِ مَا لِيٓ أَدۡعُوكُمۡ إِلَى ٱلنَّجَوٰةِ وَتَدۡعُونَنِيٓ إِلَى ٱلنَّارِ

41. «ወገኖቼ ሆይ! ወደ መዳን የምጠራችሁ ስሆን ወደ እሳትም የምትጠሩኝ ስትሆኑ ለእኔ ምን አለኝ! info
التفاسير:

external-link copy
42 : 40

تَدۡعُونَنِي لِأَكۡفُرَ بِٱللَّهِ وَأُشۡرِكَ بِهِۦ مَا لَيۡسَ لِي بِهِۦ عِلۡمٞ وَأَنَا۠ أَدۡعُوكُمۡ إِلَى ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡغَفَّٰرِ

42. « (እናንተ) በአላህ ልክድና በእርሱም ለእኔ እውቀቱ የሌለኝ ነገር በእርሱ እንዳጋራ ትጠሩኛላችሁ! እኔ አሸናፊና መሀሪ ወደ ሆነው አላህ እጠራችኋለሁ። info
التفاسير:

external-link copy
43 : 40

لَا جَرَمَ أَنَّمَا تَدۡعُونَنِيٓ إِلَيۡهِ لَيۡسَ لَهُۥ دَعۡوَةٞ فِي ٱلدُّنۡيَا وَلَا فِي ٱلۡأٓخِرَةِ وَأَنَّ مَرَدَّنَآ إِلَى ٱللَّهِ وَأَنَّ ٱلۡمُسۡرِفِينَ هُمۡ أَصۡحَٰبُ ٱلنَّارِ

43. «በእርግጥ ወደ እርሱ የምትጠሩኝ ጣዖት ለእርሱ በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም ተሰሚ ጥሪ የለዉም። መመለሻችንም እርግጥ ወደ አላህ ብቻ ነው:: ወሰን አላፊዎችም እነርሱ የእሳት ጓዶች ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
44 : 40

فَسَتَذۡكُرُونَ مَآ أَقُولُ لَكُمۡۚ وَأُفَوِّضُ أَمۡرِيٓ إِلَى ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ بَصِيرُۢ بِٱلۡعِبَادِ

44. «ወደ ፊትም ለእናንተ የምላችሁን ምክር (ቅጣትን በምታዩ ጊዜ) ታስታውሱታላችሁ:: ነገሬንም ሁሉ ወደ አላህ አስጠጋለሁ:: አላህ ባሮቹን ተመልካች ነውና።» info
التفاسير:

external-link copy
45 : 40

فَوَقَىٰهُ ٱللَّهُ سَيِّـَٔاتِ مَا مَكَرُواْۖ وَحَاقَ بِـَٔالِ فِرۡعَوۡنَ سُوٓءُ ٱلۡعَذَابِ

45. ካሴሯቸዉም መጥፎዎች አላህ ጠበቀው፡፡ በፈርዖን ቤተሰቦችም ላይ ክፉ ቅጣት ሰፈረባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
46 : 40

ٱلنَّارُ يُعۡرَضُونَ عَلَيۡهَا غُدُوّٗا وَعَشِيّٗاۚ وَيَوۡمَ تَقُومُ ٱلسَّاعَةُ أَدۡخِلُوٓاْ ءَالَ فِرۡعَوۡنَ أَشَدَّ ٱلۡعَذَابِ

46. እሳት በጧትና በማታ በእርሷ ላይ ይቀርባሉ፡፡ ሰዓቲቱም በምትሆንበት ቀን «የፈርዖንን ቤተሰቦች ብርቱን ቅጣት ገሀነምን አስገቧቸው» ይባላል። info
التفاسير:

external-link copy
47 : 40

وَإِذۡ يَتَحَآجُّونَ فِي ٱلنَّارِ فَيَقُولُ ٱلضُّعَفَٰٓؤُاْ لِلَّذِينَ ٱسۡتَكۡبَرُوٓاْ إِنَّا كُنَّا لَكُمۡ تَبَعٗا فَهَلۡ أَنتُم مُّغۡنُونَ عَنَّا نَصِيبٗا مِّنَ ٱلنَّارِ

47. በእሳት ውስጥ የሚከራከሩበትን ጊዜ አስታውስ: ደካማዎቹም ለነዚያ ለኮሩት «እኛ ለእናንተ ተከታዮች ነበርንና እናንተ አሁን ከእሳት ከፊሉን ከእኛ ላይ ገፍታሪዎች ናችሁን?» ይላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
48 : 40

قَالَ ٱلَّذِينَ ٱسۡتَكۡبَرُوٓاْ إِنَّا كُلّٞ فِيهَآ إِنَّ ٱللَّهَ قَدۡ حَكَمَ بَيۡنَ ٱلۡعِبَادِ

48. እነዚያም የኮሩት «እኛ ሁላችንም በውስጧ ነን አላህ በባሮቹ መካከል በእርግጥ ፈርዷል» ይላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
49 : 40

وَقَالَ ٱلَّذِينَ فِي ٱلنَّارِ لِخَزَنَةِ جَهَنَّمَ ٱدۡعُواْ رَبَّكُمۡ يُخَفِّفۡ عَنَّا يَوۡمٗا مِّنَ ٱلۡعَذَابِ

49. እነዚያም በእሳት ውስጥ ያሉት ለገሀነም ዘበኞች «ጌታችሁን ለምኑልን፤ ከእኛ ላይ ከቅጣቱ ለአንድም ቀን ያቃልልን።» ይላሉ። info
التفاسير: