Fassarar Ma'anonin Alqura'ni - Fassarar Amhariyanci - Akadamar Afirka

Lambar shafi:close

external-link copy
27 : 4

وَٱللَّهُ يُرِيدُ أَن يَتُوبَ عَلَيۡكُمۡ وَيُرِيدُ ٱلَّذِينَ يَتَّبِعُونَ ٱلشَّهَوَٰتِ أَن تَمِيلُواْ مَيۡلًا عَظِيمٗا

27. አላህ በእናንተ ላይ ጸጸትን ሊቀበል ይሻል:: እነዚያ ፍላጎታቸውን የሚከተሉ ግን ከእውነት ትልቅን መዘንበል እንድትዘነበሉ ይፈልጋሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
28 : 4

يُرِيدُ ٱللَّهُ أَن يُخَفِّفَ عَنكُمۡۚ وَخُلِقَ ٱلۡإِنسَٰنُ ضَعِيفٗا

28. አላህ ከናንተ ሊያቃልልላችሁ ይሻል። ሰው ደካማ ሆኖ የተፈጠረ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
29 : 4

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَأۡكُلُوٓاْ أَمۡوَٰلَكُم بَيۡنَكُم بِٱلۡبَٰطِلِ إِلَّآ أَن تَكُونَ تِجَٰرَةً عَن تَرَاضٖ مِّنكُمۡۚ وَلَا تَقۡتُلُوٓاْ أَنفُسَكُمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِكُمۡ رَحِيمٗا

29. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ገንዘቦቻችሁን በመካከላችሁ ያለ አግባብ አትብሉ:: በእናንተ መካከል በመስማማት የሆነችውን ንግድ ካልሆነች በስተቀር (እሷን ግን ብሉ) :: ነፍሶቻችሁን በራሳችሁ አትግደሉ። አላህ ለእናንተ አዛኝ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
30 : 4

وَمَن يَفۡعَلۡ ذَٰلِكَ عُدۡوَٰنٗا وَظُلۡمٗا فَسَوۡفَ نُصۡلِيهِ نَارٗاۚ وَكَانَ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرًا

30. ወሰን በማለፍ እና በመበደል ይህን የሰራ ሁሉ እሳት እናስገባዋለን:: ይህም በአላህ ላይ ገር ነውና። info
التفاسير:

external-link copy
31 : 4

إِن تَجۡتَنِبُواْ كَبَآئِرَ مَا تُنۡهَوۡنَ عَنۡهُ نُكَفِّرۡ عَنكُمۡ سَيِّـَٔاتِكُمۡ وَنُدۡخِلۡكُم مُّدۡخَلٗا كَرِيمٗا

31. ትክክለኛ አማኞች ሆይ! ከተከለከላችሁት ወንጀሎች መካክል ታላላቆችን ብትርቁ ትናንሽ ኃጢአቶቻችሁን እናብስላችኋለን:: የተከበረውንም መግቢያ (ገነት) እናስገባችኋለን:: info
التفاسير:

external-link copy
32 : 4

وَلَا تَتَمَنَّوۡاْ مَا فَضَّلَ ٱللَّهُ بِهِۦ بَعۡضَكُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖۚ لِّلرِّجَالِ نَصِيبٞ مِّمَّا ٱكۡتَسَبُواْۖ وَلِلنِّسَآءِ نَصِيبٞ مِّمَّا ٱكۡتَسَبۡنَۚ وَسۡـَٔلُواْ ٱللَّهَ مِن فَضۡلِهِۦٓۚ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٗا

32. አላህ ከፊላችሁን በከፊሉ ያበለጠበትን ጸጋ አትመኙ:: ለወንዶችም ከሰሩት ስራ እድል አለላቸው:: ለሴቶችም ከሰሩት ስራ እንዲሁ እድል አለላቸው:: አላህን ከችሮታው ለምኑት:: አላህ በሁሉ ነገር አዋቂ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
33 : 4

وَلِكُلّٖ جَعَلۡنَا مَوَٰلِيَ مِمَّا تَرَكَ ٱلۡوَٰلِدَانِ وَٱلۡأَقۡرَبُونَۚ وَٱلَّذِينَ عَقَدَتۡ أَيۡمَٰنُكُمۡ فَـَٔاتُوهُمۡ نَصِيبَهُمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ شَهِيدًا

33. ለሁላችሁም ወላጆችና የቅርብ ዘመዶች ከተውት ሀብት ወራሾችን አድርገናል:: እነዚያንም (ለመረዳዳትና ለመዋረስ) በመሐላዎቻችሁ የተዋዋላችኋቸውን (ከስድስት አንድ) ድርሻቸውን ስጧቸው:: አላህ በነገሩ ሁሉ አዋቂ (መስካሪ) ነው:: info
التفاسير: