Fassarar Ma'anonin Alqura'ni - Fassarar Amhariyanci - Akadamar Afirka

ሰበእ

external-link copy
1 : 34

ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِي لَهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَهُ ٱلۡحَمۡدُ فِي ٱلۡأٓخِرَةِۚ وَهُوَ ٱلۡحَكِيمُ ٱلۡخَبِيرُ

1. ምስጋና ሁሉ ለዚያ በሰማያትም ያለው በምድርም ያለው ሁሉ የእርሱ ለሆነው ለአላህ ብቻ ይገባው:: በመጨረሻይቱም ዓለም ምስጋና ሁሉ ለእርሱ ብቻ ነው:: እርሱም ጥበበኛና ውስጠ አዋቂው ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 34

يَعۡلَمُ مَا يَلِجُ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَمَا يَخۡرُجُ مِنۡهَا وَمَا يَنزِلُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ وَمَا يَعۡرُجُ فِيهَاۚ وَهُوَ ٱلرَّحِيمُ ٱلۡغَفُورُ

2. አላህ በምድር ውስጥ የሚገባውን ሁሉ ከእርሷ የሚወጣውንም ከሰማይም የሚወርደውን በእርሷ ውስጥ የሚያርገውንም ሁሉ ያውቃል:: እርሱም አዛኝና መሃሪ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 34

وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَا تَأۡتِينَا ٱلسَّاعَةُۖ قُلۡ بَلَىٰ وَرَبِّي لَتَأۡتِيَنَّكُمۡ عَٰلِمِ ٱلۡغَيۡبِۖ لَا يَعۡزُبُ عَنۡهُ مِثۡقَالُ ذَرَّةٖ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَلَا فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَآ أَصۡغَرُ مِن ذَٰلِكَ وَلَآ أَكۡبَرُ إِلَّا فِي كِتَٰبٖ مُّبِينٖ

3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በአላህ የካዱትም ሰዎች «ሰዓቲቱ አትመጣብንም» አሉ፡ «ጉዳዩ እንዳሰባችሁት አይደለም። ሩቁን ሁሉ አዋቂ በሆነው ጌታዬ እምላለሁ:: በእርግጥ ትመጣባችኋለች:: የብናኝ ክብደት ያክል እንኳ በሰማያትና በምድር ውስጥ ከእሱ አይሰወርም አይርቅም:: ከዚህ ያነሰም ሆነ የበለጠ የለም በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ ቢሆን እንጂ::» በላቸው info
التفاسير:

external-link copy
4 : 34

لِّيَجۡزِيَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِۚ أُوْلَٰٓئِكَ لَهُم مَّغۡفِرَةٞ وَرِزۡقٞ كَرِيمٞ

4. እነዚያን ያመኑትንና መልካም የሰሩትን ሊመነዳ ሰዓቲቱ ትመጣባችኋለች:: እነዚያ ለእነርሱ ምህረትና የከበረ ሲሳይ አለላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 34

وَٱلَّذِينَ سَعَوۡ فِيٓ ءَايَٰتِنَا مُعَٰجِزِينَ أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ عَذَابٞ مِّن رِّجۡزٍ أَلِيمٞ

5. እነዚያም የሚያመልጡ መስሏቸው አናቅጻችንን ለማፍረስ የጣሩ እነዚያ ለእነርሱ ከመጥፎ ቅጣት የሆነ አሳማሚ ስቃይ አለባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 34

وَيَرَى ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡعِلۡمَ ٱلَّذِيٓ أُنزِلَ إِلَيۡكَ مِن رَّبِّكَ هُوَ ٱلۡحَقَّ وَيَهۡدِيٓ إِلَىٰ صِرَٰطِ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡحَمِيدِ

6. እነዚያም እውቀትን የተሰጡት ያንን ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን እውነትና አሸናፊ ምስጉን ወደ ሆነው የአላህ መንገድ የሚመራ መሆኑን ያውቃሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 34

وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ هَلۡ نَدُلُّكُمۡ عَلَىٰ رَجُلٖ يُنَبِّئُكُمۡ إِذَا مُزِّقۡتُمۡ كُلَّ مُمَزَّقٍ إِنَّكُمۡ لَفِي خَلۡقٖ جَدِيدٍ

7. እነዚያም በአላህ የካዱት አሉ: «(ሙታችሁ) ሙሉ መበጣጠስን በተበጣጠሳችሁ ጊዜ በአዲስ መፈጠር ውስጥ ትሆናላችሁ ብሎ የሚነግራችሁን ሰው እናሳያችሁን? info
التفاسير: