Fassarar Ma'anonin Alqura'ni - Fassarar Amhariyanci - Akadamar Afirka

external-link copy
249 : 2

فَلَمَّا فَصَلَ طَالُوتُ بِٱلۡجُنُودِ قَالَ إِنَّ ٱللَّهَ مُبۡتَلِيكُم بِنَهَرٖ فَمَن شَرِبَ مِنۡهُ فَلَيۡسَ مِنِّي وَمَن لَّمۡ يَطۡعَمۡهُ فَإِنَّهُۥ مِنِّيٓ إِلَّا مَنِ ٱغۡتَرَفَ غُرۡفَةَۢ بِيَدِهِۦۚ فَشَرِبُواْ مِنۡهُ إِلَّا قَلِيلٗا مِّنۡهُمۡۚ فَلَمَّا جَاوَزَهُۥ هُوَ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مَعَهُۥ قَالُواْ لَا طَاقَةَ لَنَا ٱلۡيَوۡمَ بِجَالُوتَ وَجُنُودِهِۦۚ قَالَ ٱلَّذِينَ يَظُنُّونَ أَنَّهُم مُّلَٰقُواْ ٱللَّهِ كَم مِّن فِئَةٖ قَلِيلَةٍ غَلَبَتۡ فِئَةٗ كَثِيرَةَۢ بِإِذۡنِ ٱللَّهِۗ وَٱللَّهُ مَعَ ٱلصَّٰبِرِينَ

249. ጧሉትም በሰራዊቱ ታጅቦ በመጣ ጊዜ ‹‹አላህ በወንዝ ውሃ ይፈትናችኃል:: እናም ከእርሱ የጠጣ ሰው ሁሉ ከእኔ አይደለም:: እሱን ያልቀመሰው ሰው ግን በእጁ አንድ እፍኝ ያህል የዘገነ ሰው ብቻ ሲቀር እርሱ ከእኔ ነው›› አለ:: ከእነርሱም መካከል ጥቂቶች ሲቀሩ ከእርሱ ጠጡ:: እርሱና እነዚያ ከእርሱ ጋር ያመኑት ወንዙን ባለፉት ጊዜ፡- «ጃሉትን (ጎልያድን) እና ሰራዊቱን ለመዋጋት በቂ ችሎታና ጥንካሬ የለንም።» አሉት:: እነዚያ ከአላህ ጋር እንደሚገናኙ የሚያረጋግጡትም «ጥቂት ቡድን በአላህ ፈቃድ ብዙውን ቡድን ያሸነፈበት አጋጣሚ ብዙ ነው:: አላህ ከታጋሾች ጋር ነውና።» አሉ። info
التفاسير: