Fassarar Ma'anonin Alqura'ni - Fassarar Amhariyanci - Akadamar Afirka

Lambar shafi:close

external-link copy
39 : 17

ذَٰلِكَ مِمَّآ أَوۡحَىٰٓ إِلَيۡكَ رَبُّكَ مِنَ ٱلۡحِكۡمَةِۗ وَلَا تَجۡعَلۡ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ فَتُلۡقَىٰ فِي جَهَنَّمَ مَلُومٗا مَّدۡحُورًا

39. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ጌታህ ከጥበብ ወደ አንተ ካወረደው ነገር ነው:: ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ አታድርግ:: የተወቀስክ፤ የተባረርክ ሆነህ በገሀነም ውስጥ ትጣላለህና:: info
التفاسير:

external-link copy
40 : 17

أَفَأَصۡفَىٰكُمۡ رَبُّكُم بِٱلۡبَنِينَ وَٱتَّخَذَ مِنَ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ إِنَٰثًاۚ إِنَّكُمۡ لَتَقُولُونَ قَوۡلًا عَظِيمٗا

40. (ጣኦታዊያን ሆይ!) ጌታችሁ በወንዶች ልጆች መረጣችሁና ከመላዕክት ሴቶችን ልጆች ለራሱ ያዘን? እናንተ ከባድ ቃልን በእርግጥ ትናገራላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
41 : 17

وَلَقَدۡ صَرَّفۡنَا فِي هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانِ لِيَذَّكَّرُواْ وَمَا يَزِيدُهُمۡ إِلَّا نُفُورٗا

41. ይገሰጹ ዘንድ በዚህ ቁርኣን ውስጥ ደጋግመን በእርግጥ ገለጽን:: ለእነርሱ ግን ከትክክለኛው መንገድ መበርገግን እንጂ ሌላን አይጨምርላቸዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
42 : 17

قُل لَّوۡ كَانَ مَعَهُۥٓ ءَالِهَةٞ كَمَا يَقُولُونَ إِذٗا لَّٱبۡتَغَوۡاْ إِلَىٰ ذِي ٱلۡعَرۡشِ سَبِيلٗا

42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነርሱ እንደሚሉት ከእርሱ ጋር ሌላ አማልክት በነበሩ ኖሮ ያን ጊዜ ወደ ዐርሹ ባለቤት መንገድን በፈለጉ ነበር።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
43 : 17

سُبۡحَٰنَهُۥ وَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يَقُولُونَ عُلُوّٗا كَبِيرٗا

43. ጥራት ይገባው:: አላህ እነርሱ ከሚሉት ነገር ሁሉ ከፍ ያለን ልቅና ላቀ:: info
التفاسير:

external-link copy
44 : 17

تُسَبِّحُ لَهُ ٱلسَّمَٰوَٰتُ ٱلسَّبۡعُ وَٱلۡأَرۡضُ وَمَن فِيهِنَّۚ وَإِن مِّن شَيۡءٍ إِلَّا يُسَبِّحُ بِحَمۡدِهِۦ وَلَٰكِن لَّا تَفۡقَهُونَ تَسۡبِيحَهُمۡۚ إِنَّهُۥ كَانَ حَلِيمًا غَفُورٗا

44. ሰባቱ ሰማያትና ምድር እንዲሁም በውስጣቸውም ያለው ሁሉ እርሱን ያጠራሉ:: ከነገሩ ሁሉ እሱን ከማመስገን ጋር የሚያጠራው እንጂ አንድም የለም:: ማጥራታቸውን ግን አታውቁትም:: እርሱ ታጋሽና መሓሪ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
45 : 17

وَإِذَا قَرَأۡتَ ٱلۡقُرۡءَانَ جَعَلۡنَا بَيۡنَكَ وَبَيۡنَ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ حِجَابٗا مَّسۡتُورٗا

45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቁርኣንን ባነበብክ ጊዜ ባንተና በእነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም በማያምኑት ሰዎች መካከል የሚሸሸግን ግርዶሽ አድርገናል:: info
التفاسير:

external-link copy
46 : 17

وَجَعَلۡنَا عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ أَكِنَّةً أَن يَفۡقَهُوهُ وَفِيٓ ءَاذَانِهِمۡ وَقۡرٗاۚ وَإِذَا ذَكَرۡتَ رَبَّكَ فِي ٱلۡقُرۡءَانِ وَحۡدَهُۥ وَلَّوۡاْ عَلَىٰٓ أَدۡبَٰرِهِمۡ نُفُورٗا

46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንዳያውቁትም በልቦቻቸው ላይ ሽፋንን፤ በጆሮቻቸዉም ውስጥ ድንቁርናን አደረግን:: ጌታህንም ብቻውን ሆኖ በቁርኣን ባወሳሀው ጊዜ የሚሸሹ ሆነው በጀርባዎቻቸዉ ላይ ይዞራሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
47 : 17

نَّحۡنُ أَعۡلَمُ بِمَا يَسۡتَمِعُونَ بِهِۦٓ إِذۡ يَسۡتَمِعُونَ إِلَيۡكَ وَإِذۡ هُمۡ نَجۡوَىٰٓ إِذۡ يَقُولُ ٱلظَّٰلِمُونَ إِن تَتَّبِعُونَ إِلَّا رَجُلٗا مَّسۡحُورًا

47. እኛ ወደ አንተ በሚያዳምጡ፤ በሚንሾካሸኩ፤ በዳዮችም እርስ በእርሳቸው «የተደገመበትን ሰው እንጂ አትከተሉም።» በሚሉ ጊዜ የሚያዳምጡበትን ምክንያት አዋቂ ነን። info
التفاسير:

external-link copy
48 : 17

ٱنظُرۡ كَيۡفَ ضَرَبُواْ لَكَ ٱلۡأَمۡثَالَ فَضَلُّواْ فَلَا يَسۡتَطِيعُونَ سَبِيلٗا

48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ላንተ ምሳሌዎችን እንዴት እንዳደረጉልህና ከዚያም እንዴት እንደ ተሳሳቱ ተመልከት:: ወደ እውነቱ ለመድረስ ትክክለኛውን መንገድ መከተል አይችሉም። info
التفاسير:

external-link copy
49 : 17

وَقَالُوٓاْ أَءِذَا كُنَّا عِظَٰمٗا وَرُفَٰتًا أَءِنَّا لَمَبۡعُوثُونَ خَلۡقٗا جَدِيدٗا

49. አሉም፡- «አጥንቶችና ብስብሶች በሆን ጊዜ እኛ እንዴት እንደገና አዲስ ፍጥረት ሆነን በእርግጥ ተቀስቃሾች እንሆናለን?» info
التفاسير: