Fassarar Ma'anonin Alqura'ni - Fassarar Amhariyanci - Muhammad Sadiq

Lambar shafi:close

external-link copy
16 : 22

وَكَذَٰلِكَ أَنزَلۡنَٰهُ ءَايَٰتِۭ بَيِّنَٰتٖ وَأَنَّ ٱللَّهَ يَهۡدِي مَن يُرِيدُ

እንደዚሁም (ቁርኣንን) የተብራሩ አንቀጾች አድርገን አወረድነው፡፡ አላህም የሚሻውን ሰው ይመራል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
17 : 22

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَٱلَّذِينَ هَادُواْ وَٱلصَّٰبِـِٔينَ وَٱلنَّصَٰرَىٰ وَٱلۡمَجُوسَ وَٱلَّذِينَ أَشۡرَكُوٓاْ إِنَّ ٱللَّهَ يَفۡصِلُ بَيۡنَهُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ شَهِيدٌ

እነዚያ ያመኑት፣ እነዚያም ይሁዳውያን የሆኑ፣ ሳቢያኖችም፣ ክርስቲያኖችም፣ መጁሶችም እነዚያም (ጣዖታትን በአላህ) ያጋሩ አላህ በትንሣኤ ቀን በመካከላቸው በፍርድ ይለያል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ በእርግጥ ዐዋቂ ነውና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
18 : 22

أَلَمۡ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ يَسۡجُدُۤ لَهُۥۤ مَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَن فِي ٱلۡأَرۡضِ وَٱلشَّمۡسُ وَٱلۡقَمَرُ وَٱلنُّجُومُ وَٱلۡجِبَالُ وَٱلشَّجَرُ وَٱلدَّوَآبُّ وَكَثِيرٞ مِّنَ ٱلنَّاسِۖ وَكَثِيرٌ حَقَّ عَلَيۡهِ ٱلۡعَذَابُۗ وَمَن يُهِنِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِن مُّكۡرِمٍۚ إِنَّ ٱللَّهَ يَفۡعَلُ مَا يَشَآءُ۩

አላህ በሰማያት ያለው ሁሉ፣ በምድርም ያለው ሁሉ፣ ፀሐይና ጨረቃም፣ ከዋክብትም፣ ተራራዎችም፣ ዛፎችም፣ ተንቀሳቃሾችም ከሰዎች ብዙዎችም፣ ለርሱ የሚሰግዱለት መሆኑን አታውቁምን? ብዙውም በርሱ ላይ ቅጣት ተረጋገጠበት፡፡ አላህ የሚያዋርደውም ሰው ለእርሱ ምንም አክባሪ የለውም፡፡ አላህ የሻውን ይሠራልና፡፡ {1} info

{1} እዚህ አንድ ሱጁድ ትደረጋለች የንባብ ሱጁድ ነች።

التفاسير:

external-link copy
19 : 22

۞ هَٰذَانِ خَصۡمَانِ ٱخۡتَصَمُواْ فِي رَبِّهِمۡۖ فَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ قُطِّعَتۡ لَهُمۡ ثِيَابٞ مِّن نَّارٖ يُصَبُّ مِن فَوۡقِ رُءُوسِهِمُ ٱلۡحَمِيمُ

እነዚህ በጌታቸው የተከራከሩ ሁለት ባላጋራዎች ናቸው፡፡ እነዚያም የካዱት ለእነርሱ የእሳት ልብሶች ተለክተውላቸዋል፡፡ ከራሶቻቸው በላይ የፈላ ውሃ ይምቧቧቸዋል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
20 : 22

يُصۡهَرُ بِهِۦ مَا فِي بُطُونِهِمۡ وَٱلۡجُلُودُ

በሆዶቻቸው ውስጥ ያሉና ቆዳዎቻቸውም በእርሱ ይቀለጣሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
21 : 22

وَلَهُم مَّقَٰمِعُ مِنۡ حَدِيدٖ

ለእነሱም (መቅጫ) ከብረት የሆኑ መዶሻዎች አልሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
22 : 22

كُلَّمَآ أَرَادُوٓاْ أَن يَخۡرُجُواْ مِنۡهَا مِنۡ غَمٍّ أُعِيدُواْ فِيهَا وَذُوقُواْ عَذَابَ ٱلۡحَرِيقِ

ከጭንቀት ብርታት የተነሳ ከእርሷ ለመውጣት በፈለጉ ቁጥር በእርሷ ውስጥ እንዲመለሱ ይደረጋሉ፡፡ «በጣም የሚያቃጥልንም ቅጣት ቅመሱ» (ይባላሉ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
23 : 22

إِنَّ ٱللَّهَ يُدۡخِلُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ يُحَلَّوۡنَ فِيهَا مِنۡ أَسَاوِرَ مِن ذَهَبٖ وَلُؤۡلُؤٗاۖ وَلِبَاسُهُمۡ فِيهَا حَرِيرٞ

አላህ እነዚያን ያመኑትንና መልካም ሥራዎችን የሠሩትን ሰዎች በሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈስሱባቸውን ገነቶች ያገባቸዋል፡፡ በእርሷ ውስጥ ከወርቅ የሆኑን አንባሮችና ሉልን ይሸለማሉ፡፡ በእርሷ ውስጥ ልብሶቻቸውም ሐር ናቸው፡፡ info
التفاسير: