કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી

પેજ નંબર:close

external-link copy
34 : 14

وَءَاتَىٰكُم مِّن كُلِّ مَا سَأَلۡتُمُوهُۚ وَإِن تَعُدُّواْ نِعۡمَتَ ٱللَّهِ لَا تُحۡصُوهَآۗ إِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ لَظَلُومٞ كَفَّارٞ

34. ከለመናችሁትም ሁሉ የሰጣችሁ ነው:: የአላህንም ጸጋ ብትቆጥሩ እንኳ አትዘልቁትም:: ሰው በጣም በደለኛና ከሓዲ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
35 : 14

وَإِذۡ قَالَ إِبۡرَٰهِيمُ رَبِّ ٱجۡعَلۡ هَٰذَا ٱلۡبَلَدَ ءَامِنٗا وَٱجۡنُبۡنِي وَبَنِيَّ أَن نَّعۡبُدَ ٱلۡأَصۡنَامَ

35. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂም ባለ ጊዜ አስታውስ: «ጌታዬ ሆይ! ይህንን ሀገር መካን ጸጥተኛ አድርገው:: እኔንና ልጆቼንም ጣኦታትን ከመገዛት አርቀን። info
التفاسير:

external-link copy
36 : 14

رَبِّ إِنَّهُنَّ أَضۡلَلۡنَ كَثِيرٗا مِّنَ ٱلنَّاسِۖ فَمَن تَبِعَنِي فَإِنَّهُۥ مِنِّيۖ وَمَنۡ عَصَانِي فَإِنَّكَ غَفُورٞ رَّحِيمٞ

36. «ጌታዬ ሆይ! እነርሱ (ጣኦታቱ) ከሰዎች ብዙዎችን አሳስተዋልና:: የተከተለኝም ሰው እርሱ ከእኔ ነው:: ትዕዛዜን የጣሰ ሰው ግን አንተ መሓሪና አዛኝ ነህ። info
التفاسير:

external-link copy
37 : 14

رَّبَّنَآ إِنِّيٓ أَسۡكَنتُ مِن ذُرِّيَّتِي بِوَادٍ غَيۡرِ ذِي زَرۡعٍ عِندَ بَيۡتِكَ ٱلۡمُحَرَّمِ رَبَّنَا لِيُقِيمُواْ ٱلصَّلَوٰةَ فَٱجۡعَلۡ أَفۡـِٔدَةٗ مِّنَ ٱلنَّاسِ تَهۡوِيٓ إِلَيۡهِمۡ وَٱرۡزُقۡهُم مِّنَ ٱلثَّمَرَٰتِ لَعَلَّهُمۡ يَشۡكُرُونَ

37. «ጌታችን ሆይ! እኔ አዝመራ በሌለው ሸለቆ ውስጥ በተከበረው ቤትህ በካዕባ አጠገብ ከዘሮቼ አስቀመጥኩ:: ጌታችን ሆይ! ሶላትን ደንቡን ጠብቀው ይሰግዱ ዘንድ አስቀመጥኳቸው:: ከሰዎችም ልቦችን ወደ እነርሱ የሚናፍቁ አድርግ:: ያመሰግኑህም ዘንድ ከፍሬዎች ስጣቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
38 : 14

رَبَّنَآ إِنَّكَ تَعۡلَمُ مَا نُخۡفِي وَمَا نُعۡلِنُۗ وَمَا يَخۡفَىٰ عَلَى ٱللَّهِ مِن شَيۡءٖ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَا فِي ٱلسَّمَآءِ

38. «ጌታችን ሆይ! አንተ የምንደብቀውንም የምንገልጸውንም ሁሉ በእርግጥ ታውቃለህ:: በአላህ ላይ በምድርም በሰማይም ምንም ነገር አይደበቅም:: info
التفاسير:

external-link copy
39 : 14

ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِي وَهَبَ لِي عَلَى ٱلۡكِبَرِ إِسۡمَٰعِيلَ وَإِسۡحَٰقَۚ إِنَّ رَبِّي لَسَمِيعُ ٱلدُّعَآءِ

39. «ለእዚያ ከሽምግልና በኋላ ኢስማኢልንና ኢስሐቅን ለሰጠኝ አላህ ምስጋና ሁሉ ይገባው። ጌታዬ ልመናን ሰሚ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
40 : 14

رَبِّ ٱجۡعَلۡنِي مُقِيمَ ٱلصَّلَوٰةِ وَمِن ذُرِّيَّتِيۚ رَبَّنَا وَتَقَبَّلۡ دُعَآءِ

40. «ጌታዬ ሆይ! ሶላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ:: ከዘሮቼም አድርግ ጌታችን ሆይ! ጸሎቴንም ተቀበለኝ። info
التفاسير:

external-link copy
41 : 14

رَبَّنَا ٱغۡفِرۡ لِي وَلِوَٰلِدَيَّ وَلِلۡمُؤۡمِنِينَ يَوۡمَ يَقُومُ ٱلۡحِسَابُ

41. «ጌታችን ሆይ! ለእኔም ለወላጆቼም ለአማኞችም ሁሉ ምርመራ በሚደረግበት ቀን ማረን።» info
التفاسير:

external-link copy
42 : 14

وَلَا تَحۡسَبَنَّ ٱللَّهَ غَٰفِلًا عَمَّا يَعۡمَلُ ٱلظَّٰلِمُونَۚ إِنَّمَا يُؤَخِّرُهُمۡ لِيَوۡمٖ تَشۡخَصُ فِيهِ ٱلۡأَبۡصَٰرُ

42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ። የሚያቆያቸው ዓይኖች እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው:: info
التفاسير: