કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી

પેજ નંબર:close

external-link copy
6 : 14

وَإِذۡ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوۡمِهِ ٱذۡكُرُواْ نِعۡمَةَ ٱللَّهِ عَلَيۡكُمۡ إِذۡ أَنجَىٰكُم مِّنۡ ءَالِ فِرۡعَوۡنَ يَسُومُونَكُمۡ سُوٓءَ ٱلۡعَذَابِ وَيُذَبِّحُونَ أَبۡنَآءَكُمۡ وَيَسۡتَحۡيُونَ نِسَآءَكُمۡۚ وَفِي ذَٰلِكُم بَلَآءٞ مِّن رَّبِّكُمۡ عَظِيمٞ

6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳም ለህዝቦቹ «ከፈርዖን ቤተሰቦች መጥፎን ቅጣት የሚያቀምሷችሁ፤ ወንዶች ልጆቻችሁን የሚያርዱና ሴቶቻችሁንም የሚተው ሲሆን በአዳናችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ የዋለላችሁን የአላህን ጸጋ አስታውሱ:: በዚሃችሁ ከጌታችሁ የሆነ ታላቅ ፈተና አለበት።» ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 14

وَإِذۡ تَأَذَّنَ رَبُّكُمۡ لَئِن شَكَرۡتُمۡ لَأَزِيدَنَّكُمۡۖ وَلَئِن كَفَرۡتُمۡ إِنَّ عَذَابِي لَشَدِيدٞ

7. ጌታችሁም፦ «ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ:: ብትክዱም እቀጣችኋለሁ:: ቅጣቴ በእርግጥ ብርቱ ነው።» በማለት ባስታወቀ ጊዜ (የሆነዉን አስታውሱ):: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 14

وَقَالَ مُوسَىٰٓ إِن تَكۡفُرُوٓاْ أَنتُمۡ وَمَن فِي ٱلۡأَرۡضِ جَمِيعٗا فَإِنَّ ٱللَّهَ لَغَنِيٌّ حَمِيدٌ

8. ሙሳ፡- «እናንተም በምድር ያለዉም ሁሉ በመላ ብትክዱ አላህ ተብቃቂና ምስጉን ነው።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
9 : 14

أَلَمۡ يَأۡتِكُمۡ نَبَؤُاْ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِكُمۡ قَوۡمِ نُوحٖ وَعَادٖ وَثَمُودَ وَٱلَّذِينَ مِنۢ بَعۡدِهِمۡ لَا يَعۡلَمُهُمۡ إِلَّا ٱللَّهُۚ جَآءَتۡهُمۡ رُسُلُهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِ فَرَدُّوٓاْ أَيۡدِيَهُمۡ فِيٓ أَفۡوَٰهِهِمۡ وَقَالُوٓاْ إِنَّا كَفَرۡنَا بِمَآ أُرۡسِلۡتُم بِهِۦ وَإِنَّا لَفِي شَكّٖ مِّمَّا تَدۡعُونَنَآ إِلَيۡهِ مُرِيبٖ

9. (ሙስሊሞች ሆይ!) የእነዚያ ከእናንተ በፊት የነበሩት የኑህ ህዝቦች፤ የዓድ፣ የሠሙድም የእነዚያም ከእነርሱ በኋላ የነበሩት ከአላህ በስተቀር ሌላ የማያውቃቸው ህዝቦች ወሬ (ታሪክ) አልመጣላችሁምን? መልዕክተኞቻቸው በማስረጃዎች መጡላቸውና እጆቻቸውን በቁጭት ሊነክሱ ወደ አፎቻቸው መለሱ: «በተላካችሁበት ነገር ካድን እኛም ወደ እርሱ ከምትጠሩን ነገር አወላዋይ በሆነ ጥርጣሬ ውስጥ ነን።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
10 : 14

۞ قَالَتۡ رُسُلُهُمۡ أَفِي ٱللَّهِ شَكّٞ فَاطِرِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ يَدۡعُوكُمۡ لِيَغۡفِرَ لَكُم مِّن ذُنُوبِكُمۡ وَيُؤَخِّرَكُمۡ إِلَىٰٓ أَجَلٖ مُّسَمّٗىۚ قَالُوٓاْ إِنۡ أَنتُمۡ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُنَا تُرِيدُونَ أَن تَصُدُّونَا عَمَّا كَانَ يَعۡبُدُ ءَابَآؤُنَا فَأۡتُونَا بِسُلۡطَٰنٖ مُّبِينٖ

10. መልዕክተኞቻቸው «ከኃጢአቶቻችሁ እንዲሚራችሁ ወደ ተወሰነ ጊዜም ያለ ቅጣት እንዲያቆያችሁ የሚጠራችሁ ሲሆን ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ በሆነው አላህ በመኖሩ ጥርጣሬ አለን?» አሏቸው:: ህዝቦቹም፡ «እናንተ ብጤያችን ሰው እንጂ (ሌላ ፍጡር) አይደላችሁም:: አባቶቻችን ይገዙት ከነበሩት ልትከለክሉን ትሻላችሁን? ግልጽን አስረጅ ካመጣችሁት ሌላ እስቲ አምጡልን።» አሉ:: info
التفاسير: