કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી

પેજ નંબર:close

external-link copy
19 : 14

أَلَمۡ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ بِٱلۡحَقِّۚ إِن يَشَأۡ يُذۡهِبۡكُمۡ وَيَأۡتِ بِخَلۡقٖ جَدِيدٖ

19. (የሰው ልጅ ሆይ!) አላህ ሰማያትንና ምድርን በእውነት የፈጠረ መሆኑን አታይምን? ቢሻ ያጠፋችኋል:: አዲስ ፍጡርንም ያመጣል:: info
التفاسير:

external-link copy
20 : 14

وَمَا ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ بِعَزِيزٖ

20. ይህም እናንተን አጥፍቶ አዲስ ፍጥረትን ማምጣት በአላህ ላይ አስቸጋሪ ጉዳይ አይደለም:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 14

وَبَرَزُواْ لِلَّهِ جَمِيعٗا فَقَالَ ٱلضُّعَفَٰٓؤُاْ لِلَّذِينَ ٱسۡتَكۡبَرُوٓاْ إِنَّا كُنَّا لَكُمۡ تَبَعٗا فَهَلۡ أَنتُم مُّغۡنُونَ عَنَّا مِنۡ عَذَابِ ٱللَّهِ مِن شَيۡءٖۚ قَالُواْ لَوۡ هَدَىٰنَا ٱللَّهُ لَهَدَيۡنَٰكُمۡۖ سَوَآءٌ عَلَيۡنَآ أَجَزِعۡنَآ أَمۡ صَبَرۡنَا مَا لَنَا مِن مَّحِيصٖ

21. የተሰበሰቡ ሆነው ለአላህ ይገለጻሉ። ሐሳበ ደካማዎቹም ተከታዮች ለእነዚያ ለኮሩት «እኛ ለእናንተ ተከታዮች ነበርን እናንተ ከአላህ ቅጣት ከእኛ ላይ አንዳችን ነገር ተከላካዮች ናችሁን?» ይሏቸዋል። አስከታዮቹም። «አላህ ባቀናን ኖሮ በመራናችሁ ነበር።» ይሏቸዋል:: «ብንበሳጭ ወይም ብንታገሥም በእኛ ላይ ሁሉም እኩል ነው:: ለእኛ ምንም መጠጊያ የለንም።» ይላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
22 : 14

وَقَالَ ٱلشَّيۡطَٰنُ لَمَّا قُضِيَ ٱلۡأَمۡرُ إِنَّ ٱللَّهَ وَعَدَكُمۡ وَعۡدَ ٱلۡحَقِّ وَوَعَدتُّكُمۡ فَأَخۡلَفۡتُكُمۡۖ وَمَا كَانَ لِيَ عَلَيۡكُم مِّن سُلۡطَٰنٍ إِلَّآ أَن دَعَوۡتُكُمۡ فَٱسۡتَجَبۡتُمۡ لِيۖ فَلَا تَلُومُونِي وَلُومُوٓاْ أَنفُسَكُمۖ مَّآ أَنَا۠ بِمُصۡرِخِكُمۡ وَمَآ أَنتُم بِمُصۡرِخِيَّ إِنِّي كَفَرۡتُ بِمَآ أَشۡرَكۡتُمُونِ مِن قَبۡلُۗ إِنَّ ٱلظَّٰلِمِينَ لَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ

22. ነገሩም በተፈጸመ ጊዜ ሰይጣን ይላቸዋል: «አላህ እውነተኛውን ቃል ኪዳን ገባላችሁ እኔም ቃል ኪዳንም ገባሁላችሁ:: አፈረስኩባችሁም:: ለእኔም በእናንተ ላይ ምንም ሥልጣን አልነበረኝም:: ግና ጠራኋችሁና ታዘዛችሁኝ:: ስለዚህ አትውቀሱኝ ነፍሶቻችሁንም ውቀሱ:: እኔ የምረዳችሁ አይደለሁም እናንተም የምትረዱኝ አይደላችሁም። እኔ ከአሁን በፊት ለአላህ ተጋሪ በአደረጋችሁት ነገር ሁሉ ካድኩ በዳዮቹ ሁሉ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው።» info
التفاسير:

external-link copy
23 : 14

وَأُدۡخِلَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا بِإِذۡنِ رَبِّهِمۡۖ تَحِيَّتُهُمۡ فِيهَا سَلَٰمٌ

23. እነዚያ በትክክል ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ሁሉ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ በጌታቸው ፈቃድ እንዲገቡ ይደረጋሉ:: በውስጣቸው መከባበሪያቸው ሰላምታቸው «ሰላም ለእናንተ ይሁን መባባል» ነው። info
التفاسير:

external-link copy
24 : 14

أَلَمۡ تَرَ كَيۡفَ ضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلٗا كَلِمَةٗ طَيِّبَةٗ كَشَجَرَةٖ طَيِّبَةٍ أَصۡلُهَا ثَابِتٞ وَفَرۡعُهَا فِي ٱلسَّمَآءِ

24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ መልካምን ቃል ሥሯ በምድር ውስጥ የተደላደለች ቅርንጫፏም ወደ ሰማይ የረዘመች እንደሆነች መልካም ዛፍ አድርጎ ምሳሌን እንዴት እንደገለጸ አላየህምን? info
التفاسير: