Traducción de los significados del Sagrado Corán - Traducción al amárico - Academia de África

Número de página: 148:128 close

external-link copy
152 : 6

وَلَا تَقۡرَبُواْ مَالَ ٱلۡيَتِيمِ إِلَّا بِٱلَّتِي هِيَ أَحۡسَنُ حَتَّىٰ يَبۡلُغَ أَشُدَّهُۥۚ وَأَوۡفُواْ ٱلۡكَيۡلَ وَٱلۡمِيزَانَ بِٱلۡقِسۡطِۖ لَا نُكَلِّفُ نَفۡسًا إِلَّا وُسۡعَهَاۖ وَإِذَا قُلۡتُمۡ فَٱعۡدِلُواْ وَلَوۡ كَانَ ذَا قُرۡبَىٰۖ وَبِعَهۡدِ ٱللَّهِ أَوۡفُواْۚ ذَٰلِكُمۡ وَصَّىٰكُم بِهِۦ لَعَلَّكُمۡ تَذَكَّرُونَ

152. «የየቲምንም ገንዘብ አካለ መጠን እስኪድረስ ድረስ በመልካም ሁኔታ እንጂ አትቅረቡ:: ስፍርንና ሚዛንንም በትክከል ሙሉ:: ማንኛዋም ነፍስ የችሎታዋን ያህል እንጂ አናስገድድም:: በተናገራችሁ ጊዜ በዘመዶቻችሁ ላይ ቢሆንም እንኳ እውነትን በመናገር አስተካክሉ:: በአላህ ቃል ኪዳን ሙሉ:: ይሀችሁ ትገሰጹ ዘንድ አላህ በእርሱ አዘዛችሁ። info
التفاسير:

external-link copy
153 : 6

وَأَنَّ هَٰذَا صِرَٰطِي مُسۡتَقِيمٗا فَٱتَّبِعُوهُۖ وَلَا تَتَّبِعُواْ ٱلسُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمۡ عَن سَبِيلِهِۦۚ ذَٰلِكُمۡ وَصَّىٰكُم بِهِۦ لَعَلَّكُمۡ تَتَّقُونَ

153. «ይህ ቀጥተኛው መንገዴ ነው:: እናም እርሱን ብቻ ተከተሉ:: የተለያዩ የጥመት መንገዶችንም አትከተሉ:: ከቀጥተኛው የርሱ መንገድ እናንተን ይለያይዋችኋልና:: ይሀችሁ ትጠነቀቁ ዘንድ አላህ በእርሱ አዘዛችሁ።» info
التفاسير:

external-link copy
154 : 6

ثُمَّ ءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ تَمَامًا عَلَى ٱلَّذِيٓ أَحۡسَنَ وَتَفۡصِيلٗا لِّكُلِّ شَيۡءٖ وَهُدٗى وَرَحۡمَةٗ لَّعَلَّهُم بِلِقَآءِ رَبِّهِمۡ يُؤۡمِنُونَ

154. ከዚያ ለሙሳ መፅሀፍ ሰጠነው መልካም በሰራው ላይ ጸጋችንን ለማሟላት፤ ነገርንም ሁሉ ለመዘርዘር፤ ለህዝቦቹም መሪና እዝነት ይሆን ዘንድ:: እነርሱ ከጌታቸው በመገናኘት ጉዳይ ሊያምኑ ይከጀላልና:: info
التفاسير:

external-link copy
155 : 6

وَهَٰذَا كِتَٰبٌ أَنزَلۡنَٰهُ مُبَارَكٞ فَٱتَّبِعُوهُ وَٱتَّقُواْ لَعَلَّكُمۡ تُرۡحَمُونَ

155. ይህ ያወረድነው የሆነ የተባረከ መጽሐፍ ነው:: እናም ተከተሉት፤ ይታዘንላችሁም ዘንድ ከክህደት ተጠንቀቁ። info
التفاسير:

external-link copy
156 : 6

أَن تَقُولُوٓاْ إِنَّمَآ أُنزِلَ ٱلۡكِتَٰبُ عَلَىٰ طَآئِفَتَيۡنِ مِن قَبۡلِنَا وَإِن كُنَّا عَن دِرَاسَتِهِمۡ لَغَٰفِلِينَ

156. (ያወረድነውም) «መጽሐፍ የተወረደው ከፊታችን በነበሩ ሁለቱ ህዝቦች ላይ ብቻ ነው:: እኛም ከንባባቸው ዘንጊዎች ነበርን» እንዳትሉም ነው። info
التفاسير:

external-link copy
157 : 6

أَوۡ تَقُولُواْ لَوۡ أَنَّآ أُنزِلَ عَلَيۡنَا ٱلۡكِتَٰبُ لَكُنَّآ أَهۡدَىٰ مِنۡهُمۡۚ فَقَدۡ جَآءَكُم بَيِّنَةٞ مِّن رَّبِّكُمۡ وَهُدٗى وَرَحۡمَةٞۚ فَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّن كَذَّبَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَصَدَفَ عَنۡهَاۗ سَنَجۡزِي ٱلَّذِينَ يَصۡدِفُونَ عَنۡ ءَايَٰتِنَا سُوٓءَ ٱلۡعَذَابِ بِمَا كَانُواْ يَصۡدِفُونَ

157. ወይም «እኛ መጽሐፍ በእኛ ላይ በተወረደ ኖሮ ከእነርሱ ይበልጥ የተመራን እንሆን ነበር።» እንዳትሉም ነው:: ስለዚህም ከጌታችሁ ግልጽ ማስረጃ፤ መመሪያ እና እዝነት በእርግጥ መጣላችሁ:: በአላህ አናቅጽ ካስተባበለና ከእርሱም ከዞረ ሰው ይበልጥ ራሱን በዳይ ማን ነው? እነዚያን አናቅጽን የሚተውትን ይተውት በነበሩት አንቀጽ ምክንያት ብርቱ ቅጣት በእርግጥ እንቀጣቸዋለን:: info
التفاسير: