Traducción de los significados del Sagrado Corán - Traducción al amárico - Academia de África

Número de página:close

external-link copy
147 : 6

فَإِن كَذَّبُوكَ فَقُل رَّبُّكُمۡ ذُو رَحۡمَةٖ وَٰسِعَةٖ وَلَا يُرَدُّ بَأۡسُهُۥ عَنِ ٱلۡقَوۡمِ ٱلۡمُجۡرِمِينَ

147. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢያስተባብሉልህ፡- «ጌታችሁ የሰፊ ችሮታ ባለቤት ነው:: ብርቱ ቅጣቱም ከአመጸኞች ህዝቦች ላይ አይመለስም።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
148 : 6

سَيَقُولُ ٱلَّذِينَ أَشۡرَكُواْ لَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ مَآ أَشۡرَكۡنَا وَلَآ ءَابَآؤُنَا وَلَا حَرَّمۡنَا مِن شَيۡءٖۚ كَذَٰلِكَ كَذَّبَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ حَتَّىٰ ذَاقُواْ بَأۡسَنَاۗ قُلۡ هَلۡ عِندَكُم مِّنۡ عِلۡمٖ فَتُخۡرِجُوهُ لَنَآۖ إِن تَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّ وَإِنۡ أَنتُمۡ إِلَّا تَخۡرُصُونَ

148. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያ በአላህ ያጋሩት ሰዎች አላህ በሻ ኖሮ እኛም ሆነ አባቶቻችን በአላህ ባላጋራንና አንዳችንም ነገር እርም ባላደረግን ነበር።» ይላሉ:: ልክ እነዚህ እንደ አስተባበሉህ ሁሉ እነዚያ ከበፊታቸው የነበሩ ሕዝቦችም ብርቱ ቅጣታችንን እስከ ቀመሱ ድረስ አስተባበሉ:: «ለእኛ ታስተምሩን ዘንድ ማጋራታችሁን ለመውደዱ እናንተ ዘንድ እውቀት አለን? ጥርጣሬን እንጂ ሌላ አትከተሉም:: እናንተ ዋሾዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
149 : 6

قُلۡ فَلِلَّهِ ٱلۡحُجَّةُ ٱلۡبَٰلِغَةُۖ فَلَوۡ شَآءَ لَهَدَىٰكُمۡ أَجۡمَعِينَ

149. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የተሟላው ማስረጃ የአላህ ማስረጃ ብቻ ነው:: በፈለገ ኖሮ ሁላችሁንም ባቀናችሁ ነበር።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
150 : 6

قُلۡ هَلُمَّ شُهَدَآءَكُمُ ٱلَّذِينَ يَشۡهَدُونَ أَنَّ ٱللَّهَ حَرَّمَ هَٰذَاۖ فَإِن شَهِدُواْ فَلَا تَشۡهَدۡ مَعَهُمۡۚ وَلَا تَتَّبِعۡ أَهۡوَآءَ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ وَهُم بِرَبِّهِمۡ يَعۡدِلُونَ

150. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያ አላህ ይህንን እርም ማድረጉን የሚመሰክሩትን ምስክሮቻችሁን እስቲ አምጡ።» በላቸው:: ቢመሰክሩም ከእነርሱ ጋር አትመስክር:: የእነዚያን በአናቅጻችን ያስተባበሉትን፤ የእነዚያንም በጌታቸው ሌላን የሚያስተካክሉ ሲሆኑ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑትን ሰዎች ዝንባሌዎች አትከተል:: info
التفاسير:

external-link copy
151 : 6

۞ قُلۡ تَعَالَوۡاْ أَتۡلُ مَا حَرَّمَ رَبُّكُمۡ عَلَيۡكُمۡۖ أَلَّا تُشۡرِكُواْ بِهِۦ شَيۡـٔٗاۖ وَبِٱلۡوَٰلِدَيۡنِ إِحۡسَٰنٗاۖ وَلَا تَقۡتُلُوٓاْ أَوۡلَٰدَكُم مِّنۡ إِمۡلَٰقٖ نَّحۡنُ نَرۡزُقُكُمۡ وَإِيَّاهُمۡۖ وَلَا تَقۡرَبُواْ ٱلۡفَوَٰحِشَ مَا ظَهَرَ مِنۡهَا وَمَا بَطَنَۖ وَلَا تَقۡتُلُواْ ٱلنَّفۡسَ ٱلَّتِي حَرَّمَ ٱللَّهُ إِلَّا بِٱلۡحَقِّۚ ذَٰلِكُمۡ وَصَّىٰكُم بِهِۦ لَعَلَّكُمۡ تَعۡقِلُونَ

151. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸውም: «ኑ ጌታችሁ በእናተ ላይ እርም ያደረገውን ነገርና (በእርሱም ያዘዛችሁን) ላንብብላችሁ። እርሱም በአላህ ምንንም ነገር አታጋሩ:: ለወላጆቻችሁም በጎ ስራን ስሩ:: ልጆቻችሁንም ድህነትን ፈርታችሁ አትግደሉ:: እኛ እናንተንም ሆነ እነርሱን እንመግባችኋለንና:: ወደ ግልፅም ይሁን ድብቅ መጥፎ ስራ አትቅረቡ:: ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ በሀቅ ቢሆን እንጂ አትግደሉ:: ይሀችሁ! ታውቁ ዘንድ በእርሱ አዘዛችሁ። info
التفاسير: